Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 23:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ዳዊትም ሳኦል ክፉን እንዳሰበበት አወቀ፥ ካሁኑን አብያታርንም፦ ኤፉዱን ወደዚህ አምጣ አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ዳዊትም ሳኦል ክፉ እንዳሰበበት ባወቀ ጊዜ፣ ካህኑን አብያታርን፣ “ኤፉዱን አምጣ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ዳዊትም ሳኦል ክፉ እንዳሰበበት ባወቀ ጊዜ፥ ካህኑን አብያታርን፥ “ኤፉዱን አምጣ” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ዳዊትም ሳኦል አደጋ ሊጥልበት ማቀዱን በሰማ ጊዜ ካህኑን አብያታርን “ኤፉዱን ይዘህ ና!” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ዳዊ​ትም ሳኦል በእ​ርሱ ለክ​ፋት ዝም እን​ደ​ማ​ይል ዐወቀ፤ ዳዊ​ትም ካህ​ኑን አብ​ያ​ታ​ርን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ኤፉድ ወደ​ዚህ አምጣ” አለው።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 23:9
15 交叉引用  

ንጉሡም ካህኑን አብያታርን “አንተ ዛሬ የሞት ሰው ነበርህ፤ ነገር ግን የአምላክን የእግዚአብሔርን ታቦት በአባቴ በዳዊት ፊት ስለ ተሸከምህ፥ አባቴም የተቀበለውን መከራ ሁሉ አንተ ስለ ተቀበልህ አልገድልህምና በዓናቶት ወዳለው ወደ እርሻህ ሂድ፤” አለው።


ወደ እኔ ጩኽ፥ እኔም እመልስልሃለሁ፥ አንተም የማታውቀውን ታላቅና ኃይለኛ ነገርን አሳይሃለሁ።


የእስራኤል ልጆች ያለ ንጉሥና ያለ አለቃ፥ ያለ መሥዋዕትና ያለ ዓምድ፥ ያለ ኤፉድና ያለ ተራፊም ብዙ ወራት ይቀመጣሉና፥


በካህኑም በአልዓዛር ፊት ይቁም፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት በኡሪም ፍርድ ይጠይቅለት፤ እርሱ ከእርሱም ጋር የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በቃሉ ይውጡ፥ በቃሉም ይግቡ።


አውቀው ልስጥራንና ደርቤን ወደሚባሉት ወደ ሊቃኦንያ ከተማዎች በእነርሱም ዙሪያ ወዳለው አገር ሸሹ፤


ሳውል ግን አሳባቸውን አወቀ። ይገድሉትም ዘንድ በሌሊትና በቀን የከተማይቱን በር ሁሉ ይጠቀብቁ ነበር፤


ከእግዚአብሔርም፦ ገና ወደዚህ የሚመጣ ሰው አለን? ብለው ደግሞ ጠየቁት እግዚአብሔርም፦ እነሆ፥ በዕቃ መካከል ተሸሽጎአል ብሎ መለሰ።


በዚያም ቀን አኪያ በእስራኤል ልጆች ፊት ኤፉድ ለብሶ ነበርና ሳኦል፦ ኤፉድን አምጣ አለው።


ከአኪጦብም ልጅ ከአቢሜሌክ ልጆች ስሙ አብያታር የሚባል አንዱ ልጅ አምልጦ ወደ ዳዊት ሸሸ።


ዳዊትም፦ የእስራኤል አምላክ አቤቱ፥ በእኔ ምክንያት ከተማይቱን ያጠፋ ዘንድ ሳኦል ወደ ቅዒላ ሊመጣ እንደሚፈልግ እኔ ባሪያህ ፈጽሜ ሰምቻለሁ።


እንዲህም ሆነ፥ የአቢሜሌክ ልጅ አብያታር ወደ ዳዊት ወደ ቅዒላ በኮበለለ ጊዜ ኤፉዱን ይዞ ወርዶ ነበር።


ሳኦልም ወደ ቅዒላ ወርደው ይዋጉ ዘንድ፥ ዳዊትንና ሰዎቹንም ይከብቡ ዘንድ ሕዝቡን ሁሉ አዘዘ።


ዳዊትም የአቢሜሌክን ልጅ ካህኑን አብያታርን፦ ኤፉዱን አቅርብልኝ አለው፥ አብያታርም ኤፋዱን ለዳዊት አቀረበለት።


跟着我们:

广告


广告