Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 23:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ዳዊትም ደግሞ እግዚአብሔርን ጠየቀ፥ እግዚአብሔርም መልሶ፦ ፍልስጥኤማውያንን በእጅህ አሳልፌ እሰጣለሁና ተነሥተህ ወደ ቅዒላ ውረድ አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ዳዊት እንደ ገና እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም፣ “ፍልስጥኤማውያንን በእጅህ አሳልፌ ስለምሰጥ፣ ወደ ቅዒላ ውረድ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ዳዊት እንደገና ጌታን ጠየቀ፤ ጌታም፥ “ፍልስጥኤማውያንን በእጅህ አሳልፌ ስለምሰጥ፥ ወደ ቅዒላ ውረድ” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከዚህም የተነሣ ዳዊት እንደገና የእግዚአብሔርን ፈቃድ ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም “እኔ በፍልስጥኤማውያን ላይ ድልን ስለማቀዳጅህ ሄደህ በቀዒላ ላይ አደጋ ጣል” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ዳዊ​ትም ደግሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መልሶ፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለ​ሁና ተነ​ሥ​ተህ ወደ ቂአላ ውረድ” አለው።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 23:4
14 交叉引用  

ከዚያም በኋላ ዳዊት፦ ከይሁዳ ከተሞች ወደ አንዲቱ ልውጣን? ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም፦ ውጣ አለው። ዳዊትም፦ ወዴት ልውጣ? አለ። እርሱም፦ ወደ ኬብሮን ውጣ አለው።


ዳዊትም፦ ወደ ፍልስጥኤማውያን ልውጣን? በእጄስ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን? ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም ዳዊትን፦ ፍልስጥኤማውያንን በእርግጥ በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና ውጣ አለው።


ይህም በእግዚአብሔር ዐይን ቀላል ነገር ነው፤ ደግሞም ሞዓባውያንን በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣል።


ዳዊትም “ወደ ፍልስጥኤማውያን ልውጣን? በእጄስ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም “በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና ውጣ፤” አለው።


እናንተም ከተደበቃችሁበት ስፍራ ተነሡ፥ አምላካችሁም እግዚአብሔር እርስዋን በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣልና ከተማይቱን ያዙ።


ጌዴዎንም እግዚአብሔርን፦ እኔ ይህን አንድ ጊዜ ስናገር አትቈጣኝ፥ እኔ ይህን አንድ ጊዜ በጠጉሩ፥ እባክህ፥ ልፈትን፥ አሁንም በጠጉሩ ብቻ ላይ ደረቅ ይሁን፥ በምድሪቱም ሁሉ ላይ ጠል ይሁን አለው።


እግዚአብሔርም ጌዴዎንን፦ በእጃቸው ውኃ በጠጡት በሦስት መቶ ሰዎች አድናችኋለሁ፥ ምድያማውያንንም በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ፥ የቀሩት ሕዝብ ሁሉ ግን ወደ ስፍራቸው ይመለሱ አለው።


በዚያም ሌሊት እግዚአብሔር፦ በእጅህ አሳልፌ ሰጥቻቸዋለሁና ተነሥተህ ወደ ሰፈር ውረድ።


ከእግዚአብሔርም፦ ገና ወደዚህ የሚመጣ ሰው አለን? ብለው ደግሞ ጠየቁት እግዚአብሔርም፦ እነሆ፥ በዕቃ መካከል ተሸሽጎአል ብሎ መለሰ።


ዳዊትም፦ ልሂድን? እነዚህንስ ፍልስጥኤማውያን ልምታን? ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ፥ እግዚአብሔርም ዳዊትን፦ ሂድ፥ ፍልስጥኤማውያንን ምታ ቅዒላንም አድን አለው።


የዳዊትም ሰዎች፦ እነሆ፥ በዚህ በይሁዳ መቀመጥ እንፈራለን፥ ይልቁንስ በፍልስጥኤማውያን ጭፍሮች ላይ ወደ ቅዒላ ብንሄድ እንዴት ነው? አሉት።


ዳዊትና ሰዎቹም ወደ ቅዒላ ሄዱ፥ ከፍልስጥኤማውያንም ጋር ተዋጉ፥ እንስሶቻቸውንም ማረኩ፥ በታላቅም አገዳደል ገደሉአቸው። ዳዊትም በቅዒላ የሚኖሩትን አዳነ።


ሳኦልም እግዚአብሔርን ጠየቀ፥ እግዚአብሔርም በሕልም ወይም በኡሪም ወይም በነቢያት አልመለሰለትም።


ዳዊትም፦ የእነዚህን ሠራዊት ፍለጋ ልከተልን? አገኛቸዋለሁን? ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ፥ እርሱም፦ ታገኛቸዋለህና፥ ፈጽመህም ምርኮውን ትመልሳለህና ፍለጋቸውን ተከተል ብሎ መለሰለት።


跟着我们:

广告


广告