Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 23:28 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ሳኦልም ዳዊትን ማሳደድ ትቶ ተመለስ፥ ከፍልስጥኤማውያንም ጋር ሊዋጋ ሄደ። ስለዚህ የዚህ ስፍራ ስም የማምለጥ ዓለት ተባለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ከዚያም ሳኦል ዳዊትን ማሳደዱን ትቶ፣ ከፍልስጥኤማውያን ጋራ ሊዋጋ ሄደ። ከዚህ የተነሣም የዚያን ቦታ ስም ሐማለኮዝ ብለው ጠሩት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ከዚያም ሳኦል ዳዊትን ማሳደዱን ትቶ፥ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሊዋጋ ሄደ። ከዚህ የተነሣም የዚያ ቦታ ስም “የመለያያ ዓለት” ብለው ጠሩት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ስለዚህም ሳኦል ዳዊትን የማሳደድ ተግባሩን አቁሞ ፍልስጥኤማውያንን ለመውጋት ሄደ፤ ያም ቦታ “የማምለጥ አለት” ተብሎ የተጠራበት ምክንያት ይኸው ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን ማሳ​ደ​ድን ትቶ ተመ​ለሰ። ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጋር ሊዋጋ ሄደ። ስለ​ዚህ የዚያ ስፍራ ስም የመ​ለ​ያ​የት ዓለት ተባለ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 23:28
6 交叉引用  

ሳኦልና ሰዎቹም ሊፈልጉት ሄዱ፥ ዳዊትም በሰማ ጊዜ ወደ ዓለቱ ወርዶ በማዖን ምድረ በዳ ተቀመጠ፥ ሳኦልም ያንን በሰማ ጊዜ ዳዊትን በማዖን ምድረ በዳ አሳደደው።


ወደ ሳኦልም መልእክተኛ መጥቶ፦ ፍልስጥኤማውያን አገሩን ወርረውታልና ፈጥነህ ና አለው።


ዳዊትም ከዚያ ወጥቶ በዓይንጋዲ አምባዎች ተቀመጠ።


እንዲህም ሆነ፥ ሳኦል ፍልስጥኤማውያንን ከማሳደድ ከተመለሰ በኋላ፦ እነሆ፥ ዳዊት በዓይንጋዲ ምድረ በዳ አለ የሚል ወሬ ደረሰለት።


ሳኦልም ከእስራኤል ሁሉ የተመረጡትን ሦስት ሺህ ሰዎች ወሰደ፥ ዳዊትንና ሰዎቹንም ለመፈለግ የበረሀ ፍየሎች ወደ ነበሩባቸው ዓለቶች ሄደ።


跟着我们:

广告


广告