Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 23:18 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን አደረጉ፥ ዳዊትም በጥሻው ውስጥ ተቀመጠ፥ ዮናታንም ወደ ቤቱ ሄደ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን አደረጉ። ከዚያም ዮናታን ወደ ቤቱ ሄደ፤ ዳዊት ግን እዚያው ሖሬሽ ተቀመጠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ሁለቱም በጌታ ፊት ቃል ኪዳን አደረጉ። ከዚያም ዮናታን ወደ ቤቱ ሄደ፤ ዳዊት ግን እዚያው ሖሬሽ ተቀመጠ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ስለዚህ ሁለቱም እርስ በርሳቸው የወዳጅነት ቃል ኪዳን አደረጉ፤ ከዚህም በኋላ ዳዊት በሖሬሽ መኖሩን ቀጠለ፤ ዮናታንም ወደ ቤቱ ተመልሶ ሄደ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ሁለ​ቱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቃል ኪዳን አደ​ረጉ፤ ዳዊ​ትም በቄኒ ውስጥ ተቀ​መጠ፤ ዮና​ታ​ንም ወደ ቤቱ ሄደ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 23:18
8 交叉引用  

ንጉሡም በሳኦል ልጅ በዮናታንና በዳዊት መካከል ስለ ነበረው ስለ እግዚአብሔር መሐላ የሳኦልን ልጅ የዮናታንን ልጅ ሜምፊቦስቴን አዳነ።


ዳዊትም፦ ስለ ዮናታን ቸርነት አደርግለት ዘንድ ከሳኦል ቤት አንድ ሰው ቀርቶአልን? አለ።


ዳዊትም ለሳኦል መናገሩን በፈጸመ ጊዜ የዮናታን ነፍስ በዳዊት ነፍስ ታሰረች፥ ዮናታንም እንደ ነፍሱ ወደደው።


ዮናታንም እንደ ነፍሱ ስለ ወደደው ከዳዊት ጋር ቃል ኪዳን አደረገ።


ዮናታንም ዳዊትን፦ በደኅና ሂድ፥ እነሆ፥ እኛ ሁለታችን በእኔና በአንተ፥ በዘሬና በዘርህ መካከል ለዘላለም እግዚአብሔር ይሁን ብለን በእግዚአብሔር ስም ተማምለናል አለው። ዳዊትም ተነሥቶ ሄደ፥ ዮናታንም ወደ ከተማ ገባ።


እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ከባሪያህ ጋር አድርገሃልና ለባሪያህ ቸርነት አድርግ፥ በደል ግን ቢገኝብኝ አንተ ግደለኝ፥ ለምን ወደ አባትህ ታደርሰኛለህ?


ዳዊትም ወደ ካህኑ ወደ አቢሜሌክ ወደ ኖብ መጣ፥ አቢሜሌክም እየተንቀጠቀጠ ዳዊትን ሊገናኘው መጣና፦ ስለ ምን አንተ ብቻህን ነህ? ከአንተስ ጋር ስለምን ማንም የለም? አለው።


跟着我们:

广告


广告