Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 23:14 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ዳዊትም በምድረ በዳ በአምባ ውስጥ ይኖር ነበር፥ ከዚፍ ምድረ በዳም ባለው በተራራማው አገር ተቀመጠ፥ ሳኦልም ሁልጊዜ ይፈልገው ነበር፥ እግዚአብሔር ግን በእጁ አሳልፎ አልሰጠውም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ዳዊት በምድረ በዳ ባሉ ምሽጎችና በዚፍ ምድረ በዳ ኰረብቶች ተቀመጠ፤ ሳኦልም በየዕለቱ ይከታተለው ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ዳዊትን አሳልፎ አልሰጠውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ዳዊት በምድረ በዳ ባሉ ምሽጎችና በዚፍ ምድረ በዳ ኰረብታዎች ተቀመጠ፤ ሳኦልም በየዕለቱ ይከታተለው ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ዳዊትን አሳልፎ አልሰጠውም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ዳዊት በዚፍ አጠገብ ባለው ምድረ በዳ ውስጥ በኮረብታማው አገር ተሸሽጎ ኖረ፤ ሳኦልም እርሱን ለማግኘት ዘወትር ይፈልገው ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ዳዊትን ለሳኦል አሳልፎ አልሰጠውም፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ዳዊ​ትም በም​ድረ በዳ በጠ​ባቡ በማ​ሴ​ሬም ይኖር ነበር፥ በአ​ው​ክ​ሞ​ዲስ ውስ​ጥም በዚፍ ተራራ ምድረ በዳ ተቀ​መጠ፤ ሳኦ​ልም ሁል​ጊዜ ይፈ​ል​ገው ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በእጁ አሳ​ልፎ አል​ሰ​ጠ​ውም።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 23:14
19 交叉引用  

ጌትን፥ መሪሳን፥ ዚፍን፥


ንጉሡም ጸሐፊውን ባሮክንና ነቢዩን ኤርምያስን ይይዙ ዘንድ የንጉሡን ልጅ ይረሕምኤልንና የዓዝርኤልን ልጅ ሠራያን የዓብድኤልንም ልጅ ሰሌምያን አዘዘ፥ እግዚአብሔር ግን ሰወራቸው።


እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?


በአንጾኪያና በኢቆንዮን በልስጥራንም የሆነብኝን የታገሥሁትንም ስደት ታውቃለህ፤ ጌታም ከሁሉ አዳነኝ።


ዚፍ፥ ጤሌም፥ በዓሎት፥ ሐጾርሐዳታ፥ ሐጾር የምትባለውም ቂርያትሐጾር፥


ማዖን፥ ቀርሜሎስ፥ ዚፍ፥ ዩጣ፥ ኢይዝራኤል፥


ዳዊትም ሳኦል ነፍሱን ሊፈልግ እንደ ወጣ አየ፥ ዳዊትም በዚፍ ምድረ በዳ በጥሻው ውስጥ ይኖር ነበር።


ሳኦልም ዳዊት ወደ ቅዒላ እንደ መጣ ሰማ፥ ሳኦልም፦ መዝጊያና መወርወሪያ ወዳለባት ከተማ ገብቶ ተገኝቶአልና እግዚአብሔር በእጄ አሳልፎ ሰጥቶታል አለ።


ደግሞም፥ አባቴ ሆይ፥ የልብስህ ዘርፍ በእጄ እንዳለ ተመልክተህ እወቅ፥ የልብስህንም ዘርፍ በቆረጥሁ ጊዜ አልገደልሁህም፥ ስለዚህም በእጄ ክፋትና በደል እንደሌለ፥ አንተም ነፍሴን ልትወስድ ምንም ብታሳድደኝ እንዳልበደልሁህ ተመልክተህ እወቅ።


ዳዊትም በልቡ፦ አንድ ቀን በሳኦል እጅ እጠፋለሁ ወደ ፍልስጥኤማውያንም ምድር ከመሸሽ በቀር የሚሻለኝ የለም፥ ሳኦልም በእስራኤል አውራጃ ሁሉ እኔን መሻት ይተዋል፥ እንዲህም ከእጁ እድናለሁ አለ።


跟着我们:

广告


广告