Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 23:10 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ዳዊትም፦ የእስራኤል አምላክ አቤቱ፥ በእኔ ምክንያት ከተማይቱን ያጠፋ ዘንድ ሳኦል ወደ ቅዒላ ሊመጣ እንደሚፈልግ እኔ ባሪያህ ፈጽሜ ሰምቻለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ከዚያም ዳዊት እንዲህ አለ፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ሳኦል ወደ ቅዒላ መጥቶ፣ በእኔ ምክንያት ከተማዪቱን ለማጥፋት ማሰቡን ባሪያህ በትክክል ሰምቷል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ከዚያም ዳዊት እንዲህ አለ፤ “የእስራኤል አምላክ ጌታ ሆይ፤ ሳኦል ወደ ቅዒላ መጥቶ፥ በእኔ ምክንያት ከተማዪቱን ለማጥፋት ማሰቡን ባርያህ በትክክል ሰምቷል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ከዚህም በኋላ ዳዊት እንዲህ አለ፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! በአገልጋይህ በእኔ ሰበብ ሳኦል መጥቶ ቀዒላን ለመደምሰስ ማቀዱን ሰምቻለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ዳዊ​ትም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ አቤቱ! በእኔ ምክ​ን​ያት ከተ​ማ​ዪ​ቱን ያጠፋ ዘንድ ሳኦል ወደ ቂአላ ሊመጣ እን​ደ​ሚ​ፈ​ልግ እኔ ባሪ​ያህ ፈጽሜ ሰም​ቻ​ለሁ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 23:10
8 交叉引用  

አምሳ ጻድቃን በከተማይቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን ታጠፉለህብ? ከተማይቱንስ በእርስዋ ስለሚገኙ አምሳ ጻድቃን አትምርምን?


የመርዶክዮስን ወገን ነግረውት ነበርና በመርዶክዮስ ብቻ እጁን ይጭን ዘንድ በዓይኑ ተናቀ፥ ሐማም በአርጤክስስ መንግሥት ሁሉ የነበሩትን የመርዶክዮስን ሕዝብ አይሁድን ሁሉ ሊያጠፋ ፈለገ።


የካህናቱም ከተማ ኖብን በሰይፍ ስለት መታ፥ ወንዶችንና ሴቶችንም፥ ብላቴኖችንና ጡት የሚጠቡትን፥ በሬዎችንና አህዮችንም በጎችንም በሰይፍ ስለት ገደለ።


የቅዒላ ሰዎች በእጁ አሳልፈው ይሰጡኛልን? ባሪያህስ እንደ ሰማ ሳኦል በውኑ ይወርዳልን? የእስራኤል አምላክ አቤቱ፥ እንድትነግረኝ እለምንሃለሁ አለ። እግዚአብሔርም፦ ይወርዳል አለ።


ሳኦልም ወደ ቅዒላ ወርደው ይዋጉ ዘንድ፥ ዳዊትንና ሰዎቹንም ይከብቡ ዘንድ ሕዝቡን ሁሉ አዘዘ።


ዳዊትም ሳኦል ክፉን እንዳሰበበት አወቀ፥ ካሁኑን አብያታርንም፦ ኤፉዱን ወደዚህ አምጣ አለው።


跟着我们:

广告


广告