Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 22:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ዳዊትም ከዚያ በሞዓብ ምድር ወዳለችው ወደ ምጽጳ ሄደ፥ የሞዓብንም ንጉሥ፦ እግዚአብሔር የሚያደርግልኝን እስካውቅ ድረስ አባቴና እናቴ ከአንተ ጋር ይቀመጡ ዘንድ እለምንሃለሁ አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ዳዊት ከዚያ ተነሥቶ፣ በሞዓብ ምድር ወዳለችው ወደ ምጽጳ ሄደ፤ ለሞዓብ ንጉሥ፣ “እግዚአብሔር የሚያደርግልኝን እስካውቅ ድረስ፣ አባቴና እናቴ መጥተው ካንተ ዘንድ እንዲቀመጡ ፈቃድህ ነውን?” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ዳዊት ከዚያ ተነሥቶ፥ በሞዓብ ምድር ወዳለችው ወደ ምጽጳ ሄደ፤ ለሞዓብ ንጉሥ፥ “እግዚአብሔር የሚያደርግልኝን እስካውቅ ድረስ፥ አባቴና እናቴ መጥተው ካንተ ዘንድ እንዲቀመጡ ፈቃድህ ነውን?” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ዳዊትም ከዚያ ተነሥቶ በሞአብ ወደምትገኘው ወደ ምጽጳ ሄደ፤ የሞአብንም ንጉሥ “እግዚአብሔር ለእኔ የሚያደርግልኝን ነገር እስካውቅ ድረስ እባክህ አባቴና እናቴ መጥተው በአንተ ዘንድ እንዲቈዩ ፍቀድላቸው” ሲል ጠየቀው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ዳዊ​ትም ከዚያ በሞ​ዓብ ምድር ወዳ​ለ​ችው ወደ መሴፋ ሄደ፤ የሞ​ዓ​ብ​ንም ንጉሥ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ደ​ር​ግ​ል​ኝን እስ​ካ​ውቅ ድረስ አባ​ቴና እናቴ ከአ​ንተ ጋር ይቀ​መጡ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለው።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 22:3
15 交叉引用  

ዮሴፍም አባቱንና ወንድሞቹን አኖረ ፈርዖን እንዳዘዘው በግብፅ ምድር በተሻለችው በራምሴ ምድር ጉልትን ሰጣቸው።


ሞዓብን መታ፥ ሞዓባውያንንም በምድር ጥሎ በገመድ ሰፈራቸው፥ በሁለትም ገመድ ለሞት፥ በአንድም ገመድ ሙሉ ለሕይወት ሰፈራቸው፥ ሞዓባውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፥ ግብርም አመጡለት።


አባትህንና እናትህን አክብር፤ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም።


ማንም ባልቴት ግን ልጆች ወይም የልጅ ልጆች ቢኖሩአት፥ እነርሱ አስቀድመው ለገዛ ቤተ ሰዎቻቸው እግዚአብሔርን መምሰል ያሳዩ ዘንድ፥ ለወላጆቻቸውም ብድራትን ይመልሱላቸው ዘንድ ይማሩ፤ ይህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና የተወደደ ነውና።


የእግዚአብሔርም መንፈስ በዮፍታሔ ላይ መጣ፥ እርሱም ገለዓድንና ምናሴን አለፈ፥ በገለዓድም ያለውን ምጽጳን አለፈ፥ ከምጽጳም ወደ አሞን ልጆች አለፈ።


ደግሞም የምዋቹ ስም ከወንድሞቹ መካከል ከአገርም ደጅ እንዳይጠፋ፥ የምዋቹን ስም በርስቱ ላይ እንዳስነሣ የመሐሎንን ሚስት ሞዓባዊቱን ሩትን ሚስት ትሆነኝ ዘንድ ወሰድሁአት፤ እናንተም ዛሬ ምስክሮች ናችሁ፤” አላቸው።


ሴቶችም ጎረቤቶችዋ፥ “ለኑኃሚን ወንድ ልጅ ተወለደላት፤” እያሉ ስም አወጡለት፤ ስሙንም ኢዮቤድ ብለው ጠሩት። እርሱም የዳዊት እባት የሆነው የእሴይ አባት ነው።


ሳኦልም መንግሥቱን በእስራኤል ላይ አጸና፥ በዙሪያውም ካሉት ከጠላቶቹ ሁሉ ጋር፥ ከሞዓብም፥ ከአሞንም ልጆች፥ ከኤዶምያስም፥ ከሱባም ነገሥታት፥ ከፍልስጥኤማውያንም ጋር ይዋጋ ነበር፥ በየሄደበትም ሁሉ ድል ይነሣ ነበር።


የተጨነቀም ሁሉ፥ ብድርም ያለበት ሁሉ፥ የተከፋም ሁሉ ወደ እርሱ ተከማቸ እርሱም በላያቸው አለቃ ሆነ፥ ከእርሱም ጋር አራት መቶ የሚያህሉ ሰዎች ነበሩ።


በሞዓብም ንጉሥ ፊት አመጣቸው፥ ዳዊትም በአምባ ውስጥ በነበረበት ወራት ሁሉ በእርሱ ዘንድ ተቀመጡ።


ሳሙኤልም ነገሩን ሁሉ ነገረው፥ አንዳችም አልሸሸገውም። ዔሊም፦ እርሱ እግዚአብሔር ነው፥ ደስ ያሰኘውን ያድርግ አለ።


跟着我们:

广告


广告