Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 22:18 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ንጉሡም ዶይቅን፦ አንተ ዞረህ በካህናቱ ላይ ውደቅባቸው አለው። ኤዶማዊውም ዶይቅ ዞሮ በካህናቱ ላይ ወደቀ፥ በዚያም ቀን የበፍታ ኤፉድ የለበሱትን ሰማንያ አምስት ሰዎች ገደለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ንጉሡም ዶይቅን፣ “እንግዲያውስ አንተው ዙርና ካህናቱን ግደላቸው” ብሎ አዘዘው። ኤዶማዊው ዶይቅም ዞረና ገደላቸው። በዚያች ዕለት ሰማንያ ዐምስት የበፍታ ኤፉድ የለበሱ ካህናትን ገደለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ንጉሡም ኤዶማዊውን ዶይቅን፥ “እንግዲያውስ አንተው ዞረህ ካህናቱን ግደላቸው” ብሎ አዘዘው። ኤዶማዊው ዶይቅም ዞረና ገደላቸው። በዚያች ዕለት ሰማንያ አምስት የበፍታ ኤፉድ የለበሱ ካህናትን ገደለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ስለዚህም ሳኦል ዶይቅን “አንተው ግደላቸው!” አለው፤ ኤዶማዊው ዶይቅም ተነሥቶ ሁሉንም ገደለ፤ በዚያኑ ቀን የፈጃቸው ኤፉድ የሚለብሱ ካህናት ብዛት ሰማኒያ አምስት ነበር፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ንጉ​ሡም ዶይ​ቅን፥ “አንተ ዞረህ ካህ​ና​ቱን ግደ​ላ​ቸው” አለው። ሶር​ያ​ዊው ዶይ​ቅም ዞሮ ካህ​ና​ቱን ገደ​ላ​ቸው፤ በዚ​ያም ቀን የበ​ፍታ ኤፉድ የለ​በ​ሱ​ትን ሦስት መቶ ሰማ​ንያ አም​ስት ሰዎ​ችን ገደለ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 22:18
14 交叉引用  

ተማማሉበትም በንጉሡም ትእዛዝ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ውስጥ በድንጋይ ወገሩት።


ለአሮንም ልጆች ሸሚዞችን መታጠቂያዎችንም ቆቦችንም ለክብርና ለጌጥ ታደርግላቸዋለህ።


ኤፍሬም ከትእዛዝ በኋላ መሄድን ወድዶአልና የተገፋና በፍርድ የተጐዳ ሆኖአል።


ንጉሡን በክፋታቸው፥ አለቆቹንም በሐሰታቸው ደስ አሰኝተዋል።


አንተን ለጥፋት፥ በእርስዋም የሚኖሩትን ለማፍዋጫ እሰጥ ዘንድ የዘንበሪን ሥርዓትና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ጠብቃችኋል፥ በምክራቸውም ሄዳችኋል፥ የሕዝቤንም ስድብ ትሸከማላችሁ።


በውስጥዋ ያሉ አለቆችዋ እንደሚያገሡ አንበሶች ናቸው፥ ፈራጆችዋም እስከ ነገ ድረስ ምንም እንደማያስቀሩ እንደ ማታ ተኵላዎች ናቸው።


ሳሙኤል ግን ገና ብላቴና ሳለ የበፍታ ኤፋድ ለብሶ በእግዚአብሔር ፊት ያገለግል ነበር።


ከእስራኤልም ነገድ ሁሉ ካህን ይሆነኝ ዘንድ፥ በመሠዊያዬ ላይ ይሠዋ ዘንድ፥ ዕጣንንም ያጥን ዘንድ ኤፋድንም በፊቴ ይለብስ ዘንድ ለእኔ መረጥሁት፥ የእስራኤልንም ልጆች የእሳት ቍርባን ሁሉ ስለ ምግብ ለአባትህ ቤት ሰጠሁ።


ከቤትህም የቀረው ሁሉ ይመጣል፥ በፊቱም ሰግዶ፦ ቁራሽ እንጀራ እበላ ዘንድ ከካህናት ወደ አንዲቱ ዕጣ፥ እባክህ፥ ስደደኝ ብሎ አንድ ብር አንድ እንጀራም ይለምናል።


跟着我们:

广告


广告