Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 22:15 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በውኑ ስለ እርሱ እግዚአብሔርን እጠይቅ ዘንድ ዛሬ ጀመርሁን? ይህ ከእኔ ይራቅ፥ እኔ ባሪያህ ይህን ሁሉ እጅግ ወይም ጥቂት ቢሆን አላውቅምና ንጉሡ እንደዚህ ያለውን ነገር በእኔ በባሪያውና በአባቴ ቤት ሁሉ ላይ አያኑር አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ስለ እርሱ እግዚአብሔርን ስጠይቅስ ያ ቀን የመጀመሪያ ጊዜዬ ነበርን? ፈጽሞ አልነበረም፤ ይህን ጕዳይ በተመለከተ አገልጋይህ የሚያውቀው ምንም ነገር ስለሌለ ንጉሥ እኔን አገልጋዩን ወይም ከአባቴ ቤተ ሰብ ማንንም ጥፋተኛ አያድርግ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ስለ እርሱ እግዚአብሔርን ስጠይቅስ ያ ቀን የመጀመሪያ ጊዜዬ ነበርን? ፈጽሞ አልነበረም፤ ይህን ጉዳይ በተመለከተ አገልጋይህ የሚያውቀው ምንም ነገር ስለ ሌለ ንጉሥ እኔን አገልጋዩን ወይም ከአባቴ ቤተሰብ ማንንም ጥፋተኛ አያድርግ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 በውኑ እግዚአብሔርን ስለ እርሱ መጠየቅ ይህ ዛሬ የመጀመሪያ ጊዜዬ ነውን? አይደለም! ንጉሥ ሆይ! እኔን አገልጋይህንም ሆነ ቤተሰቤን በዚህ ጉዳይ ላይ አትውቀስ፤ ስለዚህ ጉዳይ ይብዛም ይነስም እኔ የማውቀው ነገር የለም።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በውኑ ስለ እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እጠ​ይቅ ዘንድ ዛሬ ጀመ​ር​ሁን? ይህ ከእኔ ይራቅ፤ እኔ ባሪ​ያህ ይህን ሁሉ ትልቅ ወይም ጥቂት ቢሆን አላ​ው​ቅ​ምና ንጉሡ እን​ደ​ዚህ ያለ​ውን ነገር በእኔ በባ​ሪ​ያ​ውና በአ​ባቴ ቤት ሁሉ ላይ አያ​ኑር” አለ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 22:15
10 交叉引用  

የተጠሩትም ሁለት መቶ ሰዎች ከአቤሴሎም ጋር በየዋህነት ከኢየሩሳሌም ሄዱ፥ የሚሆነውንም ነገር ከቶ አያውቁም ነበር።


ታንኳውም የንጉሥን ቤተ ሰብ ያሻግር ዘንድ ንጉሡም ደስ ያሰኘውን ያደርግ ዘንድ ይሸጋገር ነበር። ንጉሡም ዮርዳኖስን ከተሻገረ በኋላ የጌራ ልጅ ሳሚ በፊቱ ተደፋ።


ንጉሡንም፦ ጌታዬ ሆይ፥ ኃጢአቴን አትቍጠርብኝ፥ ጌታዬ ንጉሡ፥ ከኢየሩሳሌም በወጣህ ቀነ ባሪያህ የበደልሁህን አታስብብኝ፥ ንጉሡም በልቡ አያኑረው።


ዳዊትም፦ ወደ ፍልስጥኤማውያን ልውጣን? በእጄስ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን? ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም ዳዊትን፦ ፍልስጥኤማውያንን በእርግጥ በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና ውጣ አለው።


ዳዊትም እግዚአብሔርን ጠየቀ፥ እርሱም፦ በኋላቸው ዞረህ በሾላው ዛፍ ፊት ለፊት ግጠማቸው እንጂ አትውጣ።


ትምክህታችን ይህ ነውና፤ በእግዚአብሔር ጸጋ እንጂ በሥጋዊ ጥበብ ሳይሆን፥ በእግዚአብሔር ቅድስናና ቅንነት በዚህ ዓለም ይልቁንም በእናንተ ዘንድ እንደኖርን የሕሊናችን ምስክርነት ነው።


ንጉሡም፦ አቢሜሌክ ሆይ፥ አንተና የአባትህ ቤት ሁሉ ፈጽማችሁ ትሞታላችሁ አለ።


አቢግያም ወደ ናባል መጣች፥ እነሆም፥ በቤቱ እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ ያደርግ ነበር፥ ናባልም እጅግ ሰክሮ ነበርና ልቡ ደስ ብሎት ነበር፥ ስለዚህም እስኪነጋ ድረስ ታናሽ ነገር ወይም ታላቅ ነገር አልነገረችውም ነበር።


跟着我们:

广告


广告