Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 21:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ካህኑም፦ በኤላ ሸለቆ የገደልኸው የፍልስጥኤማዊው የጎልያድ ሰይፍ፥ እነሆ፥ በመጎናጸፊያ ተጠቅልሎ ከዚህ ከኤፉዱ በኋላ አለ፥ ትወድደውም እንደ ሆነ ውሰደው፥ ሌላ ከዚህ የለም አለ። ዳዊትም፦ እንደ እርሱ ያለ የለምና እርሱን ስጠኝ አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ካህኑም፣ “በኤላ ሸለቆ አንተ የገደልኸው የፍልስጥኤማዊው የጎልያድ ሰይፍ እዚህ አለ፤ ከኤፉዱ በስተኋላ በጨርቅ ተጠቅልሏል ከፈለግህ ውሰደው፤ ከርሱ በቀር ሌላ ሰይፍ እዚህ የለም” ብሎ መለሰለት። ዳዊትም “እንደ እርሱ ያለ የለምና እርሱኑ ስጠኝ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ካህኑም፥ “በኤላ ሸለቆ አንተ የገደልኸው የፍልስጥኤማዊው የጎልያድ ሰይፍ እዚህ አለ፤ ከኤፉዱ በስተ ኋላ በጨርቅ ተጠቅልሏል፥ እነሆ፥ ከፈለግህ ውሰደው፤ ከእርሱ በስተቀር ሌላ ሰይፍ እዚህ የለም” ብሎ መለሰለት። ዳዊትም “እንደ እርሱ ያለ የለምና እርሱኑ ስጠኝ” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 አቤሜሌክም “በኤላ ሸለቆ የገደልከው የፍልስጥኤማዊው የጎልያድ ሰይፍ በእኔ ዘንድ አለ፤ እርሱም ከኤፉዱ በስተኋላ በጨርቅ ተጠቅሎ ተቀምጦአል፤ የምትፈልገው ከሆነ ውሰደው፤ በዚህ የሚገኝ የጦር መሣሪያ እርሱ ብቻ ነው” አለው። ዳዊትም “እርሱኑ ስጠኝ! ከእርሱ የተሻለ ሰይፍ የትም አይገኝም” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ካህ​ኑም፥ “በኤላ ሸለቆ የገ​ደ​ል​ኸው የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊው የጎ​ል​ያድ ሰይፍ እነሆ፥ በመ​ጐ​ና​ጸ​ፊያ ተጠ​ቅ​ልላ አለች፤ የም​ት​ወ​ስ​ዳት ከሆነ ውሰ​ዳት፤ ከእ​ር​ስዋ በቀር ሌላ ከዚህ የለ​ምና” አለው። ዳዊ​ትም፥ “ከእ​ር​ስዋ በቀር ሌላ ከሌለ እር​ስ​ዋን ስጠኝ” አለው። እር​ሱም ሰጠው።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 21:9
6 交叉引用  

ሳኦልና የእስራኤል ሰዎች ተከማቹ፥ በዔላ ሸለቆም ሰፈሩ፥ ከፍልስጥኤማውያንም ጋር ሊዋጉ ተሰለፉ።


ዳዊትም አቢሜሌክን፦ የንጉሥ ጉዳይ ስላስቸኮለኝ ሰይፌንና መሣሪያዬን አላመጣሁምና በአንተ ዘንድ ጦር ወይም ሰይፍ አለ ወይ? አለው።


እግዚአብሔርንም ጠየቀለት፥ ስንቅንም ሰጠው፥ የፍልስጥኤማዊውንም የጎልያድን ሰይፍ ሰጠው አለው።


የጦር ዕቃውንም በአስታሮት መቅደስ ውስጥ አኖሩት፥ ሬሳውንም በቤትሳን ቅጥር ላይ አንጠለጠሉት።


跟着我们:

广告


广告