Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 21:2 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ዳዊትም ካህኑን አቢሜሌክን፦ የተላክህበትን ነገርና የሰጠሁህን ትእዛዝ ማንም አይወቅ ብሎ ንጉሡ አንድ ነገር አዝዞኛል፥ ስለዚህም ብላቴኖቹን እንዲህ ባለ ስፍራ ተውኋቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ዳዊት፣ ካህኑን አቢሜሌክን እንዲህ አለው፤ “ንጉሡ፣ ‘ስለ ላክሁህ ነገርና ስለ ሰጠሁህ መመሪያ ማንም ሰው ምንም ነገር አይወቅ’ ብሎ አዞኛል። ሰዎቼንም የት እንደምንገናኝ ነግሬያቸዋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ዳዊት፥ ካህኑን አቢሜሌክን እንዲህ አለው፤ “ንጉሡ፥ ‘ስለ ላክሁህ ነገርና ስለ ሰጠሁህ መመሪያ ማንም ሰው ምንም ነገር አይወቅ’ ብሎ አዞኛል። ሰዎቼንም የት እንደምንገናኝ ነግሬያቸዋለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ዳዊትም ለካህኑ ለአቢሜሌክ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኔ እዚህ የመጣሁት የንጉሥ ሳኦልን ተልእኮ ለመፈጸም ነው፤ እኔ ወደዚህ የተላክሁበትን ጉዳይ ለማንም ሰው እንዳልገልጥ ንጉሡ አዞኛል፤ ተከታዮቼንም በአንድ ቦታ እንድንገናኝ አዝዣቸዋለሁ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ዳዊ​ትም ካህ​ኑን አቤ​ሜ​ሌ​ክን፥ “የተ​ላ​ክ​ህ​በ​ትን ነገ​ርና የሰ​ጠ​ሁ​ህን ትእ​ዛዝ ማንም አይ​ወቅ ብሎ ንጉሡ አንድ ነገር አዝ​ዞ​ኛል፤ ስለ​ዚ​ህም ‘ብላ​ቴ​ኖቼን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መታ​መን’ በሚ​ባ​ለው እን​ዲህ ባለው ስፍራ እን​ዲ​ሆኑ አዝ​ዣ​ቸ​ዋ​ለሁ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 21:2
13 交叉引用  

ይስሐቅም ልጁን፦ ልጄ ሆይ እንዴት ፈጥነህ አገኘኸው? አለው እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላክህ ወደ እኔ ስለ አቀረበው ነው አለ።


አለውም፦ አንተ ልጄ ዔሳው ነህን? እርሱም፦ እኔ ነኝ አለ።


እርሱም “እኔ ደግሞ እንደ አንተ ነቢይ ነኝ፤ መልአክም ‘እንጀራ ይበላ ዘንድ ውሃም ይጠጣ ዘንድ ከአንተ ጋር ወደ ቤትህ መልሰው፤’ ብሎ በእግዚአብሔር ቃል ተናገረኝ፤” አለው። ዋሽቶም ተናገረው።


በቤቴልና በመንደሮችዋ፥ በዓናቶት፥ በኖብ፥


ዛሬ በኖብ ይቆማል፥ በጽዮን ሴት ልጅ ተራራ በኢየሩሳሌም ኮረብታ ላይ እጁን ያንቀሳቅሳል።


አንዳንድ ከያዕቆብ ዘንድ ሳይመጡ ከአሕዛብ ጋር አብሮ ይበላ ነበርና በመጡ ጊዜ ግን ከተገረዙት ወገን ያሉትን ፈርቶ ያፈገፍግ ነበርና ከእነርሱ ተለየ።


እርስ በርሳችሁ ውሸት አትነጋገሩ፥ አሮጌውን ሰው ከሥራው ጋር ገፋችሁታልና፥


ሳኦልም ሜልኮልን፦ ስለ ምን እንዲህ አድርገሽ አታለልሽኝ? ጠላቴን አስኮበለልሽው አላት። ሜልኮልም ለሳኦል፦ እርሱ፦ አውጥተሽ ስደጂኝ፥ አለዚያም እገድልሻለሁ አለኝ ብላ መለሰችለት።


አሁንስ በእጅህ ምን አለ? አምስት እንጀራ ወይም የተገኘውን በእጄ ስጠኝ አለው።


ዳዊት አብያታርን፦ ኤዶማዊው ዶይቅ በዚያ መኖሩን ባየሁ ጊዜ፦ ለሳኦል በእርግጥ ይነግራል ብዬ በዚያው ቀን አውቄዋለሁ፥ ለአባትህ ቤት ነፍስ ሁሉ የጥፋታቸው ምክንያት እኔ ነኝ።


በሳኦልም ባሪያዎች አጠገብ የቆመው ኤዶማዊው ዶይቅ መልሶ፦ የእሴይ ልጅ ወደ ኖብ ወደ አኪጦብ ልጅ ወደ አቢሜሌክ ሲመጣ አይቼዋለሁ።


跟着我们:

广告


广告