Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 20:26 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ሳኦልም፦ አንድ ነገር ሆኖአል፥ ንጹሕም አይደለም፥ በእውነት ንጹሕ አይደለም ብሎ አስቦአልና በዚያን ቀን ምንም አልተናገረም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ሳኦልም፣ “ዳዊት በሥርዐቱ መሠረት እንዳይነጻ የሚያደርገው አንድ ነገር ገጥሞታል፤ በርግጥም አልነጻም” ብሎ ስላሰበ፣ በዚያ ቀን ምንም አልተናገረም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ሳኦልም፥ “ዳዊት በሥርዓቱ መሠረት እንዳይነጻ የሚያደርገው አንድ ነገር ገጥሞታል፤ በእርግጥም አልነጻም” ብሎ ስላሰበ፥ በዚያ ቀን ምንም አልተናገረም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ይሁን እንጂ ሳኦል በዚያን ቀን ምንም ቃል አልተናገረም፤ ሳኦል ስለ ዳዊት ሲያስብ “ምናልባት አንድ ነገር ገጥሞት ይሆናል፤ ወይም በሕጉ መሠረት በሥርዓት አልነጻም ይሆናል” በማለት ያሰላስል ነበር፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ሳኦ​ልም፥ “አንድ ነገር ሆኖ ይሆ​ናል፤ ምን​አ​ል​ባ​ትም ንጹሕ አይ​ደ​ለም ይሆ​ናል፤ በእ​ው​ነ​ትም ንጹሕ አይ​ደ​ለም” ብሎ አስ​ቦ​አ​ልና በዚያ ቀን ምንም አል​ተ​ና​ገ​ረም።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 20:26
11 交叉引用  

በእነዚህም ርኩስ ትሆናላችሁ፤ የእነርሱንም በድን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።


በአራት እግሮቹ ከሚሄድ እንስሳ ሁሉ በመዳፎቹ ላይ የሚሄድ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው፤ የእርሱን በድን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።


ከሚንቀሳቀሱት ሁሉ በእናንተ ዘንድ ርኩሶች የሚሆኑ እነዚህ ናቸው። ከእነርሱም የሞተውን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።


ከበድኑም የሚበላ ልብሱን ያጥባል፥ እስከ ማታም ርኩስ ይሆናል፤ በድኑንም የሚያነሣ ልብሱን ይጠብ፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው።


መኝታውንም የሚነካ ሁሉ ልብሱን ይጠብ፥ በውኃም ይታጠብ፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው።


በሜዳም በሰይፍ የተገደለውን ወይም የሞተውን በድን ወይም የሰውን አጥንት ወይም መቃብር የሚነካ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል።


እርሱም፦ ለደኅነት ነው፥ ለእግዚአብሔር እሠዋ ዘንድ መጣሁ፥ ቅዱሳን ሁኑ፥ ከእኔም ጋር ወደ መሥዋዕቱ ኑ አለ። እሴይንና ልጆቹንም ቀደሳቸው፥ ወደ መሥዋዕቱም ጠራቸው።


ከመባቻም በኋላ በማግሥቱ በሁለተኛው ቀን የዳዊት ስፍራ ባዶውን ነበረ፥ ሳኦልም ልጁን ዮናታንን፦ የእሴይ ልጅ ትናንትና ወይም ዛሬ ግብር ሊበላ ያልመጣ ስለ ምን ነው? አለው።


跟着我们:

广告


广告