Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 2:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እርሱ የቅዱሳኑን እግር ይጠብቃል ኃጥአን ግን ዝም ብለው በጨለማ ይቀመጣሉ፥ ሰው በኃይሉ አይበረታምና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እርሱ የታማኝ አገልጋዮቹን እግር ይጠብቃል፤ ክፉዎች ግን በጨለማ ውስጥ ይጣላሉ። “ሰው በኀይሉ ድል አያደርግም፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እርሱ የታማኞቹን እግር ይጠብቃል ሰው በኃይሉ አይበረታምና፥ ኃጥአን ግን ዝም ብለው በጨለማ ይጣላሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 “ሰው ድልን የሚያገኘው በኀይሉ ስላልሆነ እግዚአብሔር የታማኞቹን እርምጃዎች ይጠብቃል፤ ክፉዎች ግን ወደ ጨለማ ይጣላሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ለሚ​ጸ​ልይ ጸሎ​ቱን ይሰ​ጠ​ዋል፤ የጻ​ድ​ቃ​ንን ዘመን ይባ​ር​ካል፤ የሰው ኀይል ጽኑዕ አይ​ደ​ለ​ምና።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 2:9
41 交叉引用  

ከብርሃን ወደ ጨለማ ያፈልሱታል፥ ከዓለምም ያሳድዱታል።


በአፈር ውስጥ በአንድነት ሰውራቸው፥ በተሸሸገም ስፍራ ፊታቸውን ሸፍን።


ለምስኪኑም ተስፋ አለው፥ ክፋት ግን አፍዋን ትዘጋለች።


ድንኳንህም በሰላም እንዲሆን ታውቃለህ፥ በረትህን ትጐበኛለህ አንዳችም አይጐድልብህም።


ዘመኑን ሁሉ በጨለማ በኀዘን በብስጭት በደዌና በቍጣ ነው።


እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች፥ ሰልፍም ለኃያላን፥ እንጀራም ለጠቢባን፥ ባለጠግነትም ለአስተዋዮች፥ ሞገስም ለአዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ፥ ጊዜና እድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል።


እኔ እግዚአብሔር ጠባቂው ነኝ፥ ሁልጊዜ አጠጣዋለሁ፥ ማንም እንዳይጎዳው በሌሊትና በቀን እጠብቀዋለሁ።


የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ፥ ከዚህ በኋላ፦ የመንግሥታት እመቤት አትባይምና ዝም ብለሽ ተቀመጪ ወደ ጨለማም ውስጥ ግቢ።


ዝም ብለን ለምን እንቀመጣለን? እግዚአብሔርን ስለ በደልን አምላካችን እግዚአብሔር አጥፍቶናልና፥ የሐሞትንም ውኃ አጠጥቶናልና ተሰብስባችሁ ወደ ተመሸጉ ከተሞች እንግባ በዚያም እንጥፋ።።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፥


ያ ቀን የመዓት ቀን የመከራና የጭንቀት ቀን፥ የመፍረስና የመጥፋት ቀን፥ የጨለማና የጭጋግ ቀን፥ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን፥


መልሶም፦ ለዘሩባቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፦ በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


እግዚአብሔር ይባርክህ፥ ይጠብቅህም፤


የመንግሥት ልጆች ግን በውጭ ወደ አለው ጨለማ ይጣላሉ፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።


አፍም ሁሉ ይዘጋ ዘንድ ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ሕግ የሚናገረው ሁሉ ከሕግ በታች ላሉት እንዲናገር እናውቃለን፤


ሕዝቡንም ወደዳቸው፤ 2 ቅዱሳኑ ሁሉ በእጅህ ናቸው፤ 2 በእግሮችህም አጠገብ ተቀመጡ፤ 2 ቃሎችህን ይቀበላሉ።


ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የተጠበቀላቸው እነዚህ ውኃ የሌለባቸው ምንጮች በዐውሎ ነፋስም የተነዱ ደመናዎች ናቸው።


የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ የያዕቆብም ወንድም የሆነ ይሁዳ፥ በእግዚአብሔር አብ ተወደው ለኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ፦


የገዛ ነውራቸውን አረፋ እየደፈቁ ጨካኝ የባሕር ማዕበል፥ ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የተጠበቀላቸው የሚንከራተቱ ከዋክብት ናቸው።


ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።


አሁንም፥ ጌታዬ ሆይ፥ ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህም እምላለሁ! ወደ ደም እንዳትገባ፥ እጅህም ራስህን እንዳታድን የከለከለህ እግዚአብሔር ነው፥ አሁንም ጠላቶችህና በጌታዬ ላይ ክፉ የሚሹ ሁሉ እንደ ናባል ይሁኑ።


跟着我们:

广告


广告