Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 2:27 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 የእግዚአብሔርም ሰው ወደ ዔሊ መጥቶ አለው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ በግብጽ በፈርዖን ቤት ባሪያ ሳለ ለአባትህ ቤት ተገለጥሁ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 በዚህ ጊዜ አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ ዔሊ መጥቶ እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የአባትህ ቤት በግብጽ ምድር በፈርዖን እጅ በነበረ ጊዜ ራሴን ገለጥሁለት?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 አንድ እግዚአብሔር ሰው ወደ ዔሊ መጥቶ እንዲህ አለው፦ “ጌታ እንዲህ ይላል፤ ‘በግብጽ በፈርዖን ቤት ባርያ ሳሉ ለአባትህ ቤት ተገለጥሁ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ከእግዚአብሔር የተላከ አንድ ነቢይ ወደ ዔሊ መጥቶ እንዲህ አለው፦ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በፈርዖን ቤት ባሪያዎች በነበሩ ጊዜ ለቀድሞ አባትህ ለአሮን ራሴን ገለጥሁለት፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው ወደ ዔሊ መጥቶ እን​ዲህ አለው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በግ​ብፅ በፈ​ር​ዖን ቤት ባሪ​ያ​ዎች ሳሉ ለአ​ባ​ትህ ቤት ተገ​ለ​ጥሁ፤

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 2:27
14 交叉引用  

ኢዮርብዓምም ዕጣን እያጠነ በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ ሳለ፥ እነሆም፥ አንድ የእግዚአብሔር ሰው በእግዚአብሔር ቃል ከይሁዳ ወደ ቤቴል መጣ፤


በሴሎም በዔሊ ቤት ላይ የተናገረው የእግዚአብሔር ቃል ይፈጸም ዘንድ ሰሎሞን አብያታርን ከእግዚአብሔር ክህነት አወጣው።


እግዚአብሔርም በግብፅ አገር ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው።


እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን አለ “ይህ የፋሲካ ሕግ ነው፤ ከእርሱ እንግዳ ሰው አይብላ።


እግዚአብሔርም አሮንን፦ “ሄደህ በምድረ በዳ ሙሴን ተገናኘው፤” አለው፤ ሄዶም በእግዚአብሔር ተራራ ተገናኘው፤ ሳመውም።


የእግዚአብሔር ሰው ሙሴ ሳይሞት የእስራኤልን ልጆች የባረከባት በረከት ይህች ናት።


አንተ ግን፥ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ከዚህ ሽሽ፤ ጽድቅንና እግዚአብሔርን መምሰል እምነትንም ፍቅርንም መጽናትንም የዋህነትንም ተከታተል።


ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።


ሴቲቱም ወደ ባልዋ መጥታ፦ አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ እኔ መጣ፥ መልኩም እንደ እግዚአብሔር መልአክ እጅግ የሚያስደነግጥ ነበረ፥ ከወዴትም እንደ መጣ አልጠየቅሁትም፥ እርሱም ስሙን አልነገረኝም።


እግዚአብሔር ወደ እስራኤል ልጆች ነቢይ ላከ፥ እርሱም አለ፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ከግብፅ ምድር አወጣኋችሁ፥ ከባርነትም ቤት አስለቀቅኋችሁ፥


በዚያም ቀን በቤቱ ላይ የተናገርሁትን ሁሉ በዔሊ አወርዳለሁ፥ እኔም ጀምሬ እፈጽምበታለሁ።


በተራራማው በኤፍሬም አገርና በሻሊሻ አለፉ፥ አላገኙአቸውምም፥ በሻዕሊም ምድርም አለፉ፥ በዚያም አልነበሩም፥ በብንያም ምድርም አለፉ፥ አላገኙአቸውምም።


እርሱም፦ እነሆ፥ አንድ የእግዚአብሔር ሰው በዚህች ከተማ አለ፥ እርሱም የተከበረ ሰው ነው፥ የሚናገረውም ሁሉ በእውነት ይፈጸማል፥ አሁን ወደዚያ እንሂድ፥ ምናልባት የምንሄድበትን መንገድ ይነግረናል አለው።


跟着我们:

广告


广告