Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 18:27 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ዳዊትና ሰዎቹም ተነሥተው ሄዱ፥ ከፍልስጥኤማውያንም መቶ ሰዎች ገደሉ፥ ዳዊትም ለንጉሥ አማች ይሆን ዘንድ ሰለባቸውን አምጥቶ በቁጥራቸው ልክ ለንጉሡ ሰጠ። ሳኦልም ልጁን ሜልኮልን ዳረለት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ዳዊትና ዐብረውት የነበሩት ሰዎቹ ሄደው ሁለት መቶ ፍልስጥኤማውያንን ገደሉ፤ ለንጉሡ ዐማች ይሆን ዘንድ፣ ሸለፈታቸውን አምጥቶ በቍጥራቸው ልክ ለንጉሡ አቀረበ፤ ከዚያም ሳኦል ልጁን ሜልኮልን ለዳዊት ዳረለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ዳዊትና አብረውት የነበሩት ሰዎቹ ሄደው ሁለት መቶ ፍልስጥኤማውያንን ገደሉ፤ ለንጉሡ ዐማች ይሆን ዘንድ፥ ሸለፈታቸውን አምጥቶ በቁጥራቸው ልክ ለንጉሡ አቀረበ፤ ከዚያም ሳኦል ልጁን ሜልኮልን ለዳዊት ዳረለት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ዳዊትና ወታደሮቹ ዘምተው ሁለት መቶ ፍልስጥኤማውያንን ገደሉ፤ ዳዊትም የንጉሥ ዐማች መሆን ይችል ዘንድ ሸለፈታቸውን ወደ ንጉሡ በመውሰድ ቈጥሮ አስረከበ። ስለዚህም ሳኦል ልጁን ሜልኮልን ለዳዊት ዳረለት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ተነ​ሥ​ተው ሄዱ፤ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሁለት መቶ ሰዎ​ችን ገደሉ፤ ዳዊ​ትም ለን​ጉሥ አማች ይሆን ዘንድ ሰለ​ባ​ቸ​ውን አም​ጥቶ በቍ​ጥ​ራ​ቸው ልክ ለን​ጉሡ ሰጠ። ሳኦ​ልም ልጁን ሜል​ኮ​ልን ዳረ​ለት።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 18:27
8 交叉引用  

ዳዊትም፦ ይሁን፥ ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፥ ነገር ግን አንድ ነገር ከአንተ እሻለሁ፥ ፊቴን ለማየት በመጣህ ጊዜ፥ የሳኦልን ልጅ ሜልኮልን ካላመጣህልኝ ፊቴን አታይም አለ።


ዳዊትም ወደ ሳኦል ልጅ ወደ ኢያቡስቴ፦ በመቶ ፍልስጥኤማውያን ሸለፈት ያጨኋትን ሚስቴን ሜልኮልን ስጠኝ ብሎ መልእክተኞችን ሰደደ።


የእግዚአብሔርም መንፈስ በላዩ በኃይል ወረደ፥ ወደ አስቀሎናም ወረደ፥ ከዚያም ሠላሳ ሰዎችን ገደለ፥ ልብሳቸውንም ወስዶ እንቈቅልሹን ለፈቱት ሰዎች ሰጠ። ቁጣውም ነደደ፥ ወደ አባቱም ቤት ወጣ።


የሳኦልም ወንዶች ልጆች ዮናታን፥ የሱዊ፥ ሚልኪሳ ነበሩ፥ የሁለቱም ሴቶች ልጆቹ ስም ይህ ነበረ፥ የታላቂቱ ስም ሜሮብ፥ የታናሺቱም ስም ሜልኮል ነበረ።


ስለዚህም ሳኦል ከእርሱ አራቀው፥ የሺህ አለቃም አደረገው፥ በሕዝቡም ፊት ይወጣና ይገባ ነበር።


ሳኦልም ዳዊትን፦ ታላቂቱ ልጄ ሜሮብ እነኋት፥ እርስዋን እድርልሃለሁ፥ ብቻ ቀልጣፋ ልጅ ሁንልኝ፥ ስለ እግዚአብሔርም ጦርነት ተጋደል አለው። ሳኦልም፦ የፍልስጥኤማውያን እጅ በእርሱ ላይ ትሁን እንጂ የእኔ እጅ በእርሱ ላይ አትሁን ይል ነበር።


ሳኦልም እግዚአብሔር ከዳዊት ጋር እንደ ሆነ አየ፥ እስራኤልም ሁሉ ወደዱት።


跟着我们:

广告


广告