Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 18:16 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ነገር ግን በፊታቸው ይወጣና ይገባ ስለ ነበረ እስራኤልና ይሁዳ ሁሉ ዳዊትን ወደዱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 መላው እስራኤልና ይሁዳ ግን ዳዊትን ወደዱት፤ በፊታቸው እየወጣና እየገባ የሚመራቸው እርሱ ነበርና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 መላው እስራኤልና ይሁዳ ግን በፊታቸው እየወጣና እየገባ የሚመራቸው እርሱ ነበርና ዳዊትን ወደዱት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ነገር ግን ተልእኮው የሚሳካለት መሪ በመሆኑ በእስራኤልም ሆነ በይሁዳ የሚገኝ ሕዝብ ሁሉ ዳዊትን ይወድ ነበር፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ነገር ግን በፊ​ታ​ቸው ይወ​ጣና ይገባ ስለ​ነ​በረ እስ​ራ​ኤ​ልና ይሁዳ ሁሉ ዳዊ​ትን ወደዱ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 18:16
9 交叉引用  

አስቀድሞ ሳኦል በእኛ ላይ ንጉሥ ሆኖ ሳለ እስራኤልን የምታወጣና የምታገባ አንተ ነበርህ፥ እግዚአብሔርም፦ አንተ ሕዝቤን እስራኤልን ትጠብቃለህ፥ በእስራኤልም ላይ አለቃ ትሆናለህ ብሎህ ነበር አሉት።


አሁንም፥ አቤቱ አምላኬ ሆይ! እኔን ባሪያህን በአባቴ በዳዊት ፋንታ አንግሠኸኛል፤ እኔም መውጫውንና መግቢያን የማላውቅ ታናሽ ብላቴና ነኝ።


አይሁዳዊውም መርዶክዮስ ለንጉሡ ለአርጤክስስ በማዕረግ ሁለተኛ ነበረ፥ በአይሁድም ዘንድ የከበረ፥ በብዙ ወንድሞችም ዘንድ የተወደደ፥ ለሕዝቡም መልካምን የፈለገ፥ ለዘሩም ሁሉ በደኅና የተናገረ ነበረ።


የሚያደርጉበትንም አጡ፤ ሕዝቡ ሁሉ ሲሰሙት ተንጠልጥለውበት ነበርና።


የካህናት አለቆችና ጻፎችም ይህን ምሳሌ በእነርሱ ላይ እንደ ተናገረ አውቀው በዚያች ሰዓት እጃቸውን ሊጭኑበት ፈለጉ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ።


ስለዚህም ሳኦል ከእርሱ አራቀው፥ የሺህ አለቃም አደረገው፥ በሕዝቡም ፊት ይወጣና ይገባ ነበር።


ሳኦልም እጅግ ብልህ እንደ ሆነ አይቶ እጅግ ፈራው።


ዳዊትም ሳኦል ወደ ሰደደው ሁሉ ይሄድ ነበር፥ አስተውሎም ያደርግ ነበር፥ ሳኦልም በጦረኞች ላይ ሾመው፥ ይህም በሕዝብ ሁሉ ዓይንና በሳኦል ባሪያዎች ዓይን መልካም ነበረ።


跟着我们:

广告


广告