Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 17:8 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እርሱም ቆሞ ወደ እስራኤል ጭፍሮች ጮኸ፦ ለሰልፍ ትሠሩ ዘንድ ለምን ወጣችሁ? እኔ ፍልስጥኤማዊ፥ እናንተም የሳኦል ባሪያዎች አይደላችሁምን? ለእናንተ አንድ ሰው ምረጡ፥ ወደ እኔም ይውረድ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ጎልያድ ቆሞ ለተሰለፈው የእስራኤል ሰራዊት እንዲህ ሲል ጮኾ ተናገረ፤ “ለውጊያ ተሰልፋችሁ መውጣታችሁ ስለ ምንድን ነው? እኔ ፍልስጥኤማዊ፣ እናንተም የሳኦል አገልጋዮች አይደላችሁምን? አንድ ሰው ምረጡና እኔ ወደ አለሁበት ይውረድ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ጎልያድ ቆሞ ለተሰለፈው የእስራኤል ሠራዊት እንዲህ ሲል ጮኾ ተናገረ፤ “ለውጊያ ተሰልፋችሁ መውጣታችሁ ስለ ምንድነው? እኔ ፍልስጥኤማዊ፥ እናንተም የሳኦል አገልጋዮች አይደላችሁምን? አንድ ሰው ምረጡና እኔ ወደ አለሁበት ይውረድ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ጎልያድ ተነሥቶ በመቆም በእስራኤል ሠራዊት ላይ እንዲህ እያለ ይደነፋባቸው ጀመር፦ “አሁን በዚያ ቦታ ለጦርነት የተሰለፋችሁት ከቶ ምን ልታደርጉ ነው? እኔ ፍልስጥኤማዊ ነኝ፤ እናንተ ደግሞ የሳኦል ባሪያዎች ናችሁ፤ እንግዲህ ከእኔ ጋር የሚዋጋ አንድ ሰው ከወታደሮቻችሁ መካከል ምረጡና ወደ እኔ መጥቶ ይግጠመኝ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እር​ሱም ቆሞ ወደ እስ​ራ​ኤል ጭፍ​ሮች ጮኸ፥ “ከእኛ ጋር ትዋጉ ዘንድ ለምን ወጣ​ችሁ? እኔ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? እና​ን​ተስ የሳ​ኦል አገ​ል​ጋ​ዮች ዕብ​ራ​ው​ያን አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምን? ከእ​ና​ንተ አንድ ሰው ምረጡ፤ ወደ እኔም ይው​ረድ፤

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 17:8
5 交叉引用  

ኦርዮም ዳዊትን፦ ታቦቱና እስራኤል ይሁዳም በጎጆ ተቀምጠዋል፥ ጌታዬ ኢዮአብና የጌታዬም ባሪያዎች በሰፊ ሜዳ ሰፍረዋል እኔ ልበላና ልጠጣ ወይስ ከሚስቴ ጋር ልተኛ ወደ ቤቴ እሄዳላሁን? በሕይወትህና በሕያው ነፍስህ እምላለሁ! ይህን ነገር አላደርገውም አለው።


ኢዮአብም “እግዚአብሔር ሕዝቡን በአሁኑ ላይ መቶ እጥፍ ይጨምር፤ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! ሁሉ የጌታዬ ባሪያዎች አይደሉምን? ይህን ነገር ጌታዬ ለምን ይሻል? በእስራኤል ላይ በደል ስለ ምን ያመጣል?” አለ።


እርሱም ሲነጋገራቸው፥ እነሆ፥ ጎልያድ የተባለው ያ ዋነኛ ጀግና ፍልስጥኤማዊ የጌት ሰው ከፍልስጥኤማውያን ጭፍራ መካከል ወጣ፥ የተናገረውንም ቃል ተናገረ፥ ዳዊትም ሰማ።


ዳዊትም በአጠገቡ ለቆሙት ሰዎች፦ ይህን ፍልስጥኤማዊ ለሚገድል፥ ከእስራኤልም ተግዳሮትን ለሚያርቅ ሰው ምን ይደረግለታል? የሕያውን አምላክ ጭፍሮች የሚገዳደር ይህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ ማን ነው? ብሎ ተናገራቸው።


ከበጎቻችሁና ከፍየሎቻችሁ አሥራት ይወስዳል፥ እናንተም ባሪያዎች ትሆኑታላችሁ።


跟着我们:

广告


广告