Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 17:55 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

55 ሳኦልም ዳዊትን ወደ ፍልስጥኤማዊው ሲወጣ ባየው ጊዜ ለሠራዊቱ አለቃ ለአበኔር፦ አበኔር ሆይ፥ ይህ ብላቴና የማን ልጅ ነው? አለው። አበኔርም፦ ንጉሥ ሆይ፥ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ፥ አላውቅም አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

55 ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ለመግጠም በሚሄድበት ጊዜ ሳኦል ተመልክቶ የሰራዊቱን አዛዥ አበኔርን፣ “አበኔር ሆይ፤ ይህ ልጅ የማን ነው?” ሲል ጠየቀው። አበኔርም፣ “ንጉሥ ሆይ፤ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ፤ አላውቅም” ብሎ መለሰለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

55 ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ለመግጠም ሲሄድ ሳኦል ተመልክቶ የሠራዊቱን አዛዥ አበኔርን፥ “አበኔር ሆይ፤ ይህ ልጅ የማን ነው?” ሲል ጠየቀው። አበኔርም፥ “ንጉሥ ሆይ፤ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ፤ አላውቅም” ብሎ መለሰለት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

55 ዳዊት ጎልያድን ለመውጋት በሚሄድበት ጊዜ ሳኦል ተመልክቶ የጦሩን አዛዥ አበኔርን “ይህ የማን ልጅ ነው?” ሲል ጠየቀው። አበኔርም “ንጉሥ ሆይ! በሕይወትህ እምላለሁ፤ የማን ልጅ እንደ ሆነ ገና አላወቅሁም” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

55 ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውን ሊዋጋ ሲወጣ ባየ ጊዜ ለሠ​ራ​ዊቱ አለቃ ለአ​ቤ​ኔር፥ “አቤ​ኔር ሆይ፥ ይህ ብላ​ቴና የማን ልጅ ነው?” አለው። አቤ​ኔ​ርም፥ “ንጉሥ ሆይ፥ በሕ​ያው ነፍ​ስህ እም​ላ​ለሁ አላ​ው​ቅም” አለ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 17:55
9 交叉引用  

በዚህ ትፈተናላችሁ ታናሽ ወንድማችሁ ካልመጣ በቀር የፈርዖንን ሕይወት ከዚህ አትወጡም።


እርስዋም አለች፦ ጌታዬ ሆይ፥ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ! ጌታ ሆይ፥ ወደ እግዚአብሔር ለመጸለይ በዚህ በአንተ ዘንድ ቆማ የነበረች ሴት እኔ ነኝ።


የሳኦልም ሚስት ስም የአኪማአስ ልጅ አኪናሆም ነበረ፥ የሠራዊቱም አለቃ ስም የሳኦል አጎት የኔር ልጅ አበኔር ነበረ።


ልኮም አስመጣው፥ እርሱም ቀይ፥ ዓይኑም የተዋበ፥ መልኩም ያማረ ነበረ። እግዚአብሔርም፦ ይህ ነውና ተነሥተህ ቅባው አለ።


ዳዊትም የፍልስጥኤማዊውን ራስ ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው፥ ጋሻ ጦሩን ግን በድንኳኑ ውስጥ አኖረው።


ንጉሡም፦ ይህ ብላቴና የማን ልጅ እንደ ሆነ አንተ ጠይቅ አለ።


ሳኦልም፦ አንተ ብላቴና፥ የማን ልጅ ነህ? አለው። ዳዊትም፦ እኔ የቤተ ልሔሙ የባሪያህ የእሴይ ልጅ ነኝ ብሎ መለሰ።


ዳዊትም ተነሥቶ ሳኦል ወደ ሰፈረበት ቦታ መጣ፥ ሳኦልና የሠራዊቱ አለቃ የኔር ልጅ አበኔርም የተኙበትን ስፍራ አየ፥ ሳኦልም በሰፈሩ ውስጥ ተኝቶ ነበር፥ ሕዝቡም በዙሪያው ሰፍሮ ነበር።


跟着我们:

广告


广告