Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 17:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ከፍልስጥኤማውያንም ሰፈር የጌት ሰው ጎልያድ፥ ቁመቱም ስድስት ክንድ ከስንዝር የሆነ፥ ዋነኛ ጀግና መጣ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከጋት የመጣ ቁመቱ ከዘጠኝ ጫማ በላይ የሆነ፣ ጎልያድ የተባለ አንድ ጀግና ከፍልስጥኤማውያን ሰፈር ወጣ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከጋት ከተማ የመጣ፥ ቁመቱ ስድስት ክንድ ከስንዝር የነበር ጎልያድ ተብሎ የሚጠራ አንድ ግዙፍ ዋነኛ ጀግና ሰው፥ ከፍልስጥኤማውያን ሰፈር ወጣ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከጋት ከተማ የመጣ፥ ጎልያድ ተብሎ የሚጠራ አንድ ግዙፍ ሰው፥ ከፍልስጥኤማውያን ሰፈር ወጥቶ እስራኤላውያንን መፈታተን ጀመረ፤ የዚያም ሰው ቁመት ሦስት ሜትር ያኽል ነበር፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሰፈር የጌት ሰው ጎል​ያድ፥ ቁመ​ቱም ስድ​ስት ክንድ ከስ​ን​ዝር የሆነ፥ ኀይ​ለኛ ሰው መጣ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 17:4
11 交叉引用  

ቁመቱም አምስት ክንድ የነበረውን ረጅሙን ግብጻዊውን ሰው ገደለ፤ በግብጻዊውም እጅ የሸማኔ መጠቅለያ የመሰለ ጦር ነበረ፤ እርሱ ግን በትር ይዞ ወደ እርሱ ወረደ፤ ከግብጻዊው እጅ ጦሩን ነቅሎ በገዛ ጦሩ ገደለው።


እኔ ግን ቁመቱ እንደ ዝግባ ቁመት፥ ብርታቱም እንደ ኮምበል ዛፍ የነበረውን አሞራዊውን ከፊታቸው አጠፋሁ፥ ፍሬውንም ከላዩ፥ ሥሩንም ከታቹ አጠፋሁ።


ከራፋይም ወገን የባሳን ንጉሥ ዐግ ብቻውን ቀርቶ ነበር፤ እነሆ፥ አልጋው የብረት አልጋ ነበረ፤ እርሱ በአሞን ልጆች አገር በረባት አለ፤ ርዝመቱ ዘጠኝ ክንድ ወርዱም አራት ክንድ በሰው ክንድ ልክ ነበረ።


በጋዛ በጌትም በአዛጦንም ጥቂቶች ቀሩ እንጂ በእስራኤል ልጆች ምድር ከዔናቅ ልጆች ማንም አልቀረም።


እርሱም ሲነጋገራቸው፥ እነሆ፥ ጎልያድ የተባለው ያ ዋነኛ ጀግና ፍልስጥኤማዊ የጌት ሰው ከፍልስጥኤማውያን ጭፍራ መካከል ወጣ፥ የተናገረውንም ቃል ተናገረ፥ ዳዊትም ሰማ።


ፍልስጥኤማውያንም በአንድ ወገን በተራራ ላይ ቆመው ነበር፥ እስራኤልም በሌላው ወገን በተራራ ላይ ቆመው ነበር፥ በመካከላቸውም ሸለቆ ነበረ።


በራሱም የናስ ቁር ደፍቶ ነበር፥ ጥሩርም ለብሶ ነበር፥ የጥሩሩም ሚዛን አምስት ሺህ ሰቅል ናስ ነበረ።


ሳኦልም ዳዊት ወደ ጌት እንደ ኮበለለ ሰማ፥ ከዚያም በኋላ ደግሞ አልፈለገውም።


跟着我们:

广告


广告