Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 17:36 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 እኔ ባሪያህ አንበሳና ድብ መታሁ፥ ይህም ያልተገረዘው ፍልስጥኤማዊ የሕያውን አምላክ ጭፍሮች ተገዳድሮአልና ከእነርሱ እንደ አንዱ ይሆናል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ባሪያህ አንበሳውንም ድቡንም ገድሏል፤ ይህም ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ የሕያው እግዚአብሔርን ሰራዊት ተገዳድሯልና መጨረሻው ከእነርሱ እንደ አንዱ ይሆናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 ባርያህ አንበሳውንም ድቡንም ገድሏል፤ ይህም ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ የሕያው እግዚአብሔርን ሠራዊት ተገዳድሯልና መጨረሻው ከእነርሱ እንደ አንዱ ይሆናል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 እኔ ያንተ አሽከር አንበሳና ድብ ገድያለሁ፤ ይህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ የሕያው እግዚአብሔርን ሠራዊት ስለ ተፈታተነ ከእነርሱ እንደ አንዱ ይሆናል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 እኔ ባሪ​ያህ አን​በ​ሳና ድብ ገደ​ልሁ፤ ይህም ያል​ተ​ገ​ረ​ዘው ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ ከእ​ነ​ርሱ እንደ አንዱ ይሆ​ናል። እን​ግ​ዲህ እገ​ድ​ለው ዘንድ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ተግ​ዳ​ሮ​ትን አስ​ወ​ግድ ዘንድ ዛሬ አል​ሄ​ድ​ምን? የሕ​ያው አም​ላክ ጭፍ​ሮ​ችን ይገ​ዳ​ደር ዘንድ ይህ ቈላፍ ምን​ድን ነው?”

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 17:36
25 交叉引用  

ደግሞም የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ለመስደብ፥ በእርሱም ላይ ለመናገር “የምድር አሕዛብ አማልክት ሕዝባቸውን ከእጄ ያድኑ ዘንድ እንዳልቻሉ፥ እንዲሁ የሕዝቅያስ አምላክ ሕዝቡን ከእጄ ያድን ዘንድ አይችልም” የሚል ደብዳቤ ጻፈ።


በውኑ መጥረቢያ በሚቈርጥበት ሰው ላይ ይመካልን? ወይስ መጋዝ በሚስበው ሰው ላይ ይጓደዳልን? ይህስ፥ በትር የሚያነሳውን እንደ መነቅነቅ ዘንግም እንጨት ያይደለውን እንደ ማንሳት ያህል ነው።


ሕዝቅያስም፦ እግዚአብሔር በእርግጥ ያድነናል ይህችም ከተማ በአሦር ንጉሥ እጅ አትሰጥም ብሎ በእግዚአብሔር እንድትታመኑ አያድርጋችሁ።


ሕዝቅያስም፦ እግዚአብሔር ያድነናል ብሎ እንዳያታልላችሁ ተጠንቀቁ። በውኑ የአሕዛብ አማልክት አገሮቻቸውን ከአሦር ንጉሥ እጅ አድነዋቸዋልን?


በእንግዶች እጅ ያልተገረዙትን ሰዎች ሞት ትሞታለህ፥ እኔ ተናግሬአለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር።


በውበት የምትበልጪው ማን ነው? ውረጂ ካልተገረዙትም ጋር ተኚ።


የመቅደሱንም ዕቃዎች በፊትህ አመጡ፥ አንተም መኳንንትህም ሚስቶችህም ቁባቶችህም የወይን ጠጅ ጠጣችሁባቸው፥ ከብርና ከወርቅም ከናስና ከብረትም ከእንጨትና ከድንጋይም የተሠሩትን የማያዩትንም የማይሰሙትንም የማያውቁትንም አማልክት አመሰገንህ፥ ትንፋሽህንና መንገድህን ሁሉ በእጁ የያዘውን አምላክ አላከበርኸውም።


በዚያም ቀን ኢየሩሳሌምን ለአሕዛብ ሁሉ ከባድ ድንጋይ አደርጋታለሁ፥ የሚሸከሙአት ሁሉ እጅግ ይቈስላሉ፥ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በላይዋ ላይ ይከማቻሉ።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ከክብሩ በኋላ ወደ በዘበዙአችሁ አሕዛብ ልኮኛል፥ የሚነካችሁ የዓይኑን ብሌን የሚነካ ነውና።


ዮናታንም ጋሻ ጃግሬውን፦ ና፥ ወደ እነዚህ ቆላፋን ጭፍራ እንለፍ፥ በብዙ ወይም በጥቂቱ ማዳን እግዚአብሔርን አያስቸግረውምና ምናልባት እግዚአብሔር ይሠራልን ይሆናል አለው።


ፍልስጥኤማዊውም፦ ዛሬ የእስራኤልን ጭፎሮች ተገዳደርኋቸው፥ እንዋጋ ዘንድ አንድ ሰው ስጡኝ አለ።


ዳዊትም በአጠገቡ ለቆሙት ሰዎች፦ ይህን ፍልስጥኤማዊ ለሚገድል፥ ከእስራኤልም ተግዳሮትን ለሚያርቅ ሰው ምን ይደረግለታል? የሕያውን አምላክ ጭፍሮች የሚገዳደር ይህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ ማን ነው? ብሎ ተናገራቸው።


በኋላውም እከተለውና እመታው ነበር፥ ከአፉም አስጥለው ነበር፥ በተነሣብኝም ጊዜ ጉሮሮውን ይዤ እመታውና እገድለው ነበር።


ዳዊትም፦ ከአንበሳና ከድብ እጅ ያስጣለኝ እግዚአብሔር ከዚህ ፍልስጥኤማዊ እጅ ያስጥለኛል አለ። ሳኦልም ዳዊትን፦ ሂድ፥ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሆናል አለው።


ሳኦልም ዳዊትን፦ ታላቂቱ ልጄ ሜሮብ እነኋት፥ እርስዋን እድርልሃለሁ፥ ብቻ ቀልጣፋ ልጅ ሁንልኝ፥ ስለ እግዚአብሔርም ጦርነት ተጋደል አለው። ሳኦልም፦ የፍልስጥኤማውያን እጅ በእርሱ ላይ ትሁን እንጂ የእኔ እጅ በእርሱ ላይ አትሁን ይል ነበር።


ሳኦልም ጋሻ ጃግሬውን፦ እነዚህ ቆላፋን መጥተው እንዳይወጉኝና እንዳይሳለቁብኝ ሰይፍህን መዝዘህ ውጋኝ አለው። ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ነበርና እንቢ አለ። ሳኦልም ሰይፉን ወስዶ በላዩ ወደቀ።


跟着我们:

广告


广告