Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 16:18 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ከብላቴኖቹም አንዱ መልሶ፦ እነሆ፥ መልካም አድርጎ በገና የሚመታ የቤተ ልሔማዊውን የእሴይን ልጅ አይቻለሁ፥ እርሱም ጽኑዕ ኃይል ነው፥ በነገርም ብልህ፥ መልኩም ያማረ ነው፥ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነው አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ከአገልጋዮቹም አንዱ፣ “መልካም አድርጎ በገና መደርደር የሚችለውን የቤተ ልሔሙን የእሴይን ልጅ አይቻለሁ፣ እርሱም ጀግናና ተዋጊ ነው፤ በአነጋገሩ አስተዋይና የደስ ደስ ያለው ነው፤ እግዚአብሔርም ከርሱ ጋራ ነው” ብሎ መለሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ከአገልጋዮቹም አንዱ፥ “መልካም አድርጎ በገና መደርደር የሚችለውን የቤተልሔሙን የእሴይን ልጅ አይቻለሁ፥ እርሱም ጀግናና ተዋጊ ነው፤ በአነጋገሩ አስተዋይና የደስ ደስ ያለው ነው፤ ጌታም ከእርሱ ጋር ነው” ብሎ መለሰ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ከአገልጋዮቹም አንዱ “የቤተልሔም ከተማ ነዋሪ የሆነው እሴይ በገና መደርደር የሚችል ልጅ እንዳለው አይቼአለሁ ይህም ብቻ ሳይሆን ጀግና፥ መልከ ቀና፥ ብርቱ ወታደርና ንግግር ዐዋቂ ነው፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነው” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም አንዱ መልሶ፥ “እነሆ፥ መል​ካም አድ​ርጎ በገና ሲመታ የቤተ ልሔ​ሙን የእ​ሴ​ይን ልጅ አይ​ቻ​ለሁ፤ ሰው​የ​ውም ጠቢብ፥ ተዋ​ጊም ነው፤ በነ​ገ​ርም ብልህ፥ መል​ኩም ያማረ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር ነው” አለ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 16:18
16 交叉引用  

እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ነበረ፥ ሥራውም የተከናወነለት ሰው ሆነ በግብፃዊው ጌታውም ቤት ነበረ።


የግዞት ቤቱን አለቃ በእጁ ያለውን ነገር ከቶ አላሰበም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና የሚያደርገውንም ሁሉ እግዚአብሔር ያቀናለት ነበር።


ባሪያህ ኢዮአብ የዚህ ነገር መልክ እንዲለውጥ አደረገ፥ ነገር ግን የእግዚአብሔር መልአክ ጠቢብ እንደ ሆነ፥ አንተም ጌታዬ በምድር ላይ ያለውን ነገር ሁሉ ታውቅ ዘንድ ጠቢብ ነህ አለች።


እስራኤልም ሁሉ አባትህ ኃያል እንደ ሆነ፥ ከእርሱም ጋር ያሉት ሰዎች ጽኑዓን እንደ ሆኑ ያውቃልና ጽኑዕ ልቡም እንደ አንበሳ ልብ የሆነው ፈጽሞ ይቀልጣል።


ኩሲ ደግሞ አለ፦ ግልገሎችዋ በዱር በተነጠቁ ጊዜ ድብ መራራ እንደ ሆነች በልባቸው መራሮች እጅግም ኃያላን መሆናቸውን አባትህንና ሰዎቹን ታውቃለህ፥ አባትህ አርበኛ ነው፥ ከሕዝብም ጋር አያድርም።


እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።


እነዚህም ምልክቶች በደረሱህ ጊዜ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና እጅህ የምታገኘውን ሁሉ አድርግ።


ልኮም አስመጣው፥ እርሱም ቀይ፥ ዓይኑም የተዋበ፥ መልኩም ያማረ ነበረ። እግዚአብሔርም፦ ይህ ነውና ተነሥተህ ቅባው አለ።


ሳኦልም ባሪያዎቹን፦ መልካም አድርጎ በገና መምታት የሚችል ሰው ፈልጋችሁ አምጡልኝ አላቸው።


ሳኦልም ወደ እሴይ መልክተኞች ልኮ፦ ከበጎች ጋር ያለውን ልጅህን ዳዊትን ላክልኝ አለ።


ዳዊትም የዚያ የኤፍራታዊው ሰው ልጅ ነበረ፥ ያም ሰው ከቤተ ልሔም ይሁዳ ስሙም እሴይ ነበረ፥ ስምንትም ልጆች ነበሩት፥ በሳኦልም ዘመን በዕድሜ አርጅቶ ሸምግሎም ነበር።


ሳሙኤልም አደገ፥ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ፥ ከቃሉም አንዳች በምድር ላይ አይወድቀም ነበር።


跟着我们:

广告


广告