Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 15:6 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ሳኦል ቄናውያንን፦ ተነሥታችሁ ሂዱ፥ ከግብጽ በወጡ ጊዜ ለእስራኤል ልጆች ቸርነት አድርጋችኋልና ከአማሌቅ ጋር እንዳላጠፋችሁ ከመካከላቸው ውረዱ አላቸው፥ ቄናውያንም ከአማሌቃውያን መካከል ሄዱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 እርሱም፣ ቄናውያንን፣ “ከእነርሱ ጋራ እንዳላጠፋችሁ ከአማሌቃውያን ራቁ፤ ተለዩአቸውም፤ እስራኤላውያን ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ፣ ቸርነት አድርጋችሁላቸዋልና” አላቸው። ስለዚህ ቄናውያን ከአማሌቃውያን ተለዩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እርሱም ቄናውያንን፥ “ከእነርሱ ጋር እንዳላጠፋችሁ ከአማሌቃውያን ራቁ፤ ተለዩአቸውም፤ ምክንያቱም እናንተ እስራኤላውያን ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ ቸርነት አድርጋችሁላቸዋልና” አላቸው። ስለዚህ ቄናውያን ከአማሌቃውያን ተለዩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 “እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ ጊዜ ቸርነት ስላደረጋችሁላቸው እናንተን ከአማሌቃውያን ጋር እንዳላጠፋ ከዐማሌቃውያን ተለይታችሁ ሂዱ” ብሎ ሳኦል ለቄናውያን ነገራቸው። እነርሱም ከዐማሌቃውያን ተለይተው ሄዱ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ሳኦ​ልም ቄኔ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን፥ “ከእ​ነ​ርሱ ጋር እን​ዳ​ላ​ጠ​ፋ​ችሁ ከአ​ማ​ሌ​ቃ​ው​ያን መካ​ከል ተነ​ሥ​ታ​ችሁ ሂዱ፤ ከግ​ብፅ በወጡ ጊዜ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ቸር​ነት አድ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልና” አላ​ቸው። ቄኔ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ከአ​ማ​ሌ​ቃ​ው​ያን መካ​ከል ወጡ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 15:6
21 交叉引用  

ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ፤


ይህ ከአንተ ይራቅ፤ ጻድቁም እንደ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ እንደዚህ ያለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ። የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅን ፍርስ አይፈርድምን?


በያቤጽም የተቀመጡ የጸሐፊዎች ወገኖች፤ ቲርዓውያን፥ ሺምዓታውያን፥ ሡካታውያን ነበሩ፤ እነዚህ ከሬካብ ቤት አባት ከሐማት የወጡ ቄናውያን ናቸው።


አሁንም እመክርሃለሁና ቃሌን ስማ፥ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሆናል፤ አንተ በእግዚአብሔር ፊት ለሕዝቡ ሁን፥ ነገራቸውንም ወደ እግዚአብሔር አድርስ፤


በዙሪያቸው የነበሩ የእስራኤል ልጆች ሁሉ ከጩኸታቸው የተነሣ፦ ምድሪቱ እንዳትውጠን ብለው በረሩ።


በብዙ ሌላ ቃልም መሰከረና፦ “ከዚህ ጠማማ ትውልድ ዳኑ” ብሎ መከራቸው።


ስለዚህም ጌታ፦ ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ ርኵስንም አትንኩ ይላል፤ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ፦ እኔም እቀበላችኋለሁ፥ ለእናንተም አባት እሆናለሁ እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች ትሆናላችሁ ይላል።


ጌታ ልሄኔሲፎሩ ቤተ ሰዎች ምሕረትን ይስጥ፥ ብዙ ጊዜ አሳርፎኛልና፤


ነፍስሽም የጎመጀችው ፍሬ ከአንቺ ዘንድ አልፎአል፥ የሚቀማጠልና የሚያጌጥም ነገር ሁሉ ጠፍቶብሻል፥ ሰዎችም ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አያገኙአቸውም።


የቄናዊው የሙሴ አማት ልጆችም ከይሁዳ ልጆች ጋር ዘንባባ ካለበት ከተማ ተነሥተው ከዓራድ በደቡብ በኩል ወዳለው ወደ ይሁዳ ምድረ በዳ ወጡ፥ ሄደውም ከሕዝቡ ጋር ተቀመጡ።


ቄናዊውም ሔቤር ከሙሴ አማት ከኦባብ ልጆች ከቄናውያን ተለይቶ ድንኳኑን በቃዴስ አጠገብ በጻዕናይም እስከ ነበረው እስከ ትልቁ ዛፍ ድረስ ተከለ።


የቄናዊው የሔቤር ሚስት ኢያዔል ከሴቶች ይልቅ የተባረከች ትሁን፥ በድንኳን ውስጥ ከሚኖሩ ሴቶች ይልቅ የተባረከች ትሁን።


ሳኦልም ወደ አማሌቅ ከተማ ወጣ፥ በሸለቆውም ውስጥ ተደበቀ።


አንኩስም፦ ዛሬ በማን ላይ ዘመታችሁ? አለ፥ ዳዊትም፦ በይሁዳ ደቡብ፥ በይረሕምኤላውያንም ደቡብ፥ በቄናውያንም ደቡብ ላይ ዘመትን አለ።


በቀርሜሎስ ለነበሩ፥ በይረሕምኤላውያንና


跟着我们:

广告


广告