Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 15:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ሳኦልም ሕዝቡን ጠርቶ በጌልገላ ቆጠራቸው፥ ሁለት መቶ ሺህ እግረኞች፥ ከይሁዳም አሥር ሺህ ሰዎች ነበሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ስለዚህ ሳኦል ሰዎቹን ጥላኢም በተባለ ቦታ ሰብስቦ ቈጠራቸው፤ እነርሱም ሁለት መቶ ሺሕ እግረኛ ወታደሮችና ከይሁዳም ዐሥር ሺሕ ሰዎች ነበሩ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ስለዚህ ሳኦል ሠራዊቱን በአንድነት ጠርቶ ጤሌም በሚባል ስፍራ ቆጠራቸው፤ የእግረኛ ወታደሮቹ ብዛት ሁለት መቶ ሺህና ከይሁዳ ዐሥር ሺህ ሰዎች ሆነው ተገኙ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ሳኦልም ሠራዊቱን በአንድነት ጠርቶ ጤሌም በሚባል ስፍራ ቈጠራቸው፤ የወታደሮቹም ብዛት ከእስራኤል ሁለት መቶ ሺህ ከይሁዳ ዐሥር ሺህ ሆነው ተገኙ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ሳኦ​ልም ሕዝ​ቡን ጠርቶ በጌ​ል​ጌላ ቈጠ​ራ​ቸው፤ አራት መቶ ሺህ እግ​ረ​ኞች፥ ከይ​ሁ​ዳም ሠላሳ ሺህ ሰዎች ነበሩ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 15:4
5 交叉引用  

በዚያም ጊዜ ንጉሡ ኢዮራም ከሰማርያ ወጥቶ እስራኤልን ሁሉ አሰለፈ።


ዚፍ፥ ጤሌም፥ በዓሎት፥ ሐጾርሐዳታ፥ ሐጾር የምትባለውም ቂርያትሐጾር፥


በቤዜቅም ቆጠራቸው፥ የእስራኤልም ልጆች ሦስት መቶ ሺህ፥ የይሁዳም ሰዎች ሠላሳ ሺህ ነበሩ።


ሳሙኤልም ከጌልገላ ተነሥቶ መንገዱን ሄደ፥ የቀሩትም ሕዝብ ሳኦልን ተከትለው ሰልፈኞቹን ሊገናኙ ሄዱ። ከጌልገላም ተነሥተው ወደ ብንያም ጊብዓ መጡ፥ ሳኦልም ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሕዝብ ቆጠረ፥ ስድስት መቶም የሚያህሉ ሰዎች ነበሩ።


ሳኦልም ወደ አማሌቅ ከተማ ወጣ፥ በሸለቆውም ውስጥ ተደበቀ።


跟着我们:

广告


广告