Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 15:28 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ሳሙኤልም፦ እግዚአብሔር የእስራኤልን መንግሥት ዛሬ ከአንተ ቀደዳት፥ ከአንተም ለሚሻል ለጎረቤትህ አሳልፎ ሰጣት፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ሳሙኤልም እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር የእስራኤልን መንግሥት ዛሬ ከአንተ ቀዶታል፤ ከአንተም ለሚሻል ለጎረቤትህ አሳልፎ ሰጥቶታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ሳሙኤልም እንዲህ አለው፤ “ጌታ የእስራኤልን መንግሥት ዛሬ ከአንተ ቀዶታል፤ ከአንተም ለሚሻል ለጎረቤትህ አሳልፎ ሰጥቶታል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ሳሙኤልም ሳኦልን እንዲህ አለው፤ “ዛሬ እግዚአብሔር የእስራኤልን መንግሥት ቀዶ ከእጅህ በመውሰድ ለተሻለ ለሌላ ሰው ሰጥቶታል፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ሳሙ​ኤ​ልም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል መን​ግ​ሥ​ት​ህን ዛሬ ከእ​ጅህ ቀደ​ዳት፤ ከአ​ን​ተም ለሚ​ሻል ለባ​ል​ን​ጀ​ራህ አሳ​ልፎ ሰጣት፤

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 15:28
20 交叉引用  

እግዚአብሔር ለዳዊት እንደ ማለለት እንዲሁ ከእርሱ ጋር ባላደርግ እግዚአብሔር በአበኔር ይህን ያድርግበት ይህንም ይጨምርበት።


እግዚአብሔርም ስለ ዳዊት፦ በባሪያዬ በዳዊት እጅ ሕዝቤን እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅና ከጠላቶቻቸው ሁሉ እጅ አድናለሁ ብሎ ተናግሮአልና እንግዲህ አሁን አድርጉ ብሎ ነገራቸው።


መንግሥትን ከሳኦል ቤት ያወጣ ዘንድ የዳዊትንም ዙፋን በእስራኤልና በይሁዳ ከዳን ጀምሮ እስከ ቤርሳቤህ ድረው ከፍ ያደርግ ዘንድ


ዳዊትም ሜልኮልን፦ በእግዚአብሔር ፊት ዘፍኛለሁ፥ በእግዚአብሔር ሕዝብ በእስራኤል ላይ አለቃ እሆን ዘንድ ከአባትሽና ከቤቱ ሁሉ ይልቅ የመረጠኝ እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን ስለዚህም በእግዚአብሔር ፊት እጫወታለሁ።


እግዚአብሔርም ሰሎሞንን አለው “ይህን ሠርተሃልና፥ ያዘዝሁህንም ቃል ኪዳኔንና ሥርዐቴን አልጠበቅህምና መንግሥትህን ከአንተ ቀዳድጄ ለባሪያህ እሰጠዋለሁ።


ደግሞም መናፍስት ጠሪ ስለ ጠየቀ፥ እግዚአብሔርንም ስላልጠየቀ፥ ስለዚህ ገደለው፤ መንግሥቱንም ወደ እሴይ ልጅ ወደ ዳዊት አሳለፈው።


ታላላቆችን ያለ ምርመራ ይሰባብራል፥ በእነርሱም ፋንታ ሌሎችን ያቆማል።


ልዑሉ በሰዎች መንግሥት ላይ እንዲሠለጥን፥ ለወደደውም እንዲሰጠው፥ ከሰውም የተዋረደውን እንዲሾምበት ሕያዋን ያውቁ ዘንድ ይህ ነገር የጠባቂዎች ትእዛዝ፥ ይህም ፍርድ የቅዱሳን ቃል ነው።


ልዑሉም በሰዎች መንግሥት ላይ እንዲሠለጥን፥ ለሚወድደውም እንዲሰጠው እስክታውቅ ድረስ ከሰዎች ተለይተህ ትሰደዳለህ፥ መኖሪያህም ከምድር አራዊት ጋር ይሆናል፥ እንደ በሬም ሣር ትበላ ዘንድ ትገደዳለህ፥ ሰባት ዘመናትም ያልፉብሃል አለው።


ኢየሱስም መልሶ፦ “ከላይ ካልተሰጠህ በቀር በእኔ ላይ ምንም ሥልጣን ባልነበረህም፤ ስለዚህ ለአንተ አሳልፎ የሰጠኝ ኃጢአቱ የባሰ ነው።” አለው።


እርሱንም ከሻረው በኋላ ዳዊትን በእነርሱ ላይ እንዲነግሥ አስነሣው፥ ሲመሰክርለትም፦ እንደ ልቤ የሆነ ሰው ፈቃዴንም ሁሉ የሚያደርግ የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ አለ።


ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው።


አሁንም መንግሥትህ አይጸናም፥ እግዚአብሔር እንደ ልቡ የሆነ ሰው መርጦአል፥ እግዚአብሔርም ያዘዘህን አልጠበቅህምና እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ አለቃ ይሆን ዘንድ አዝዞታል አለው።


ልኮም አስመጣው፥ እርሱም ቀይ፥ ዓይኑም የተዋበ፥ መልኩም ያማረ ነበረ። እግዚአብሔርም፦ ይህ ነውና ተነሥተህ ቅባው አለ።


ሳኦልም እጅግ ተቆጣ፥ ይህም ነገር አስከፋው፥ እርሱም፦ ለዳዊት እልፍ ሰጡት፥ ለእኔ ግን ሺህ ብቻ ሰጡኝ፥ ከመንግሥት በቀር ምን ቀረበት? አለ።


እግዚአብሔርም ለጌታዬ የተናገረውን ቸርነት ሁሉ ባደረገልህ ጊዜ፥ በእስራኤልም ላይ አለቃ አድርጎ ባስነሣህ ጊዜ፥


跟着我们:

广告


广告