1 ሳሙኤል 15:21 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 ሕዝቡ ግን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በጌልገላ ይሠዉ ዘንድ ከእርሙ የተመረጡትን በጎችንና በሬዎችን ከምርኮው ወሰዱ አለው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም21 ሰራዊቱ ግን ከምርኮው ከተለዩት መካከል፣ ምርጥ ምርጡን በግና በሬ፣ በጌልገላ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ይሠዉ ዘንድ ወስደዋል።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 ሕዝቡ ግን በጌልገላ ለአምላክህ ለጌታ ለመሠዋት ከምርኮው ከተለዩት መካከል፥ ምርጥ ምርጡን በግና በሬ ወስደዋል።” 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 ነገር ግን ወታደሮቼ የማረኩአቸውን ምርጥ ምርጥ የሆኑ በጎችንና የቀንድ ከብቶችን አልገደሉአቸውም፤ ይህን በማድረግ ፈንታ በጌልገላ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርገው ለማቅረብ አምጥተዋቸዋል።” 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 ሕዝቡ ግን ለአምላካችን ለእግዚአብሔር በጌልጌላ ይሠዉ ዘንድ ከእርሙ የተመረጡትን በጎችና በሬዎች ከምርኮው ወሰዱ” አለው። 参见章节 |