Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 14:36 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 ሳኦልም፥ ፍልስጥኤማውያንን በሌሊት ተከትለን እስኪነጋ ድረስ እንበዝብዛቸው አንድ ሰው እንኳ አናስቀርላቸው አለ። እነርሱም፦ ደስ የሚያሰኝህን ሁሉ አድርግ አሉት። ካህኑም፦ ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ሳኦልም፣ “ፍልስጥኤማውያንን ተከትለን በሌሊት እንውረድና እስኪነጋ ድረስ እንበዝብዛቸው፤ አንድም ሰው በሕይወት አናስቀርላቸው” አለ። እነርሱም፣ “መልካም መስሎ የታየህን ሁሉ አድርግ” ብለው መለሱለት። ካህኑ ግን፣ “እዚሁ እግዚአብሔርን እንጠይቅ” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 ከዚያም በኋላ ሳኦልም፥ “ፍልስጥኤማውያንን ተከትለን በሌሊት እንውረድና እስኪ ነጋ ድረስ እንዝረፋቸው፤ አንድም ሰው በሕይወት አናስቀርላቸው” አለ። እነርሱም “መልካም መስሎ የታየህን ሁሉ አድርግ” ብለው መለሱለት። ካህኑ ግን፥ “ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ” አለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 ሳኦልም ወታደሮቹን “እንግዲህ እንውረድና በፍልስጥኤማውያን ላይ በሌሊት አደጋ እንጣልባቸው፤ እስኪነጋም ድረስ ሀብታቸውን ዘርፈን ሁሉንም እንፍጃቸው” አለ። እነርሱም “መልካም መስሎ የታየህን ሁሉ አድርግ” አሉት። ካህኑ ግን “በመጀመሪያ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንጠይቅ” አለ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 ሳኦ​ልም፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን በሌ​ሊት ተከ​ት​ለን እን​ው​ረድ፤ እስ​ኪ​ነ​ጋም ድረስ እን​በ​ዝ​ብ​ዛ​ቸው፤ አንድ ሰው እንኳ አና​ስ​ቀ​ር​ላ​ቸው” አለ። እነ​ር​ሱም፥ “ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህን ሁሉ አድ​ርግ” አሉት። ካህ​ኑም፥ “ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ቅ​ረብ” አለ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 14:36
14 交叉引用  

ነገር ግን ዕለት ዕለት ይሹኛል መንገዴንም ያውቁ ዘንድ ይወድዳሉ፥ ጽድቅን እንዳደረጉ የአምላካቸውንም ፍርድ እንዳልተዉ ሕዝብ እውነተኛውን ፍርድ ይለምኑኛል፥ ወደ እግዚአብሔርም ለመቅረብ ይወድዳሉ።


ተነሡ በሌሊትም እንውጣ፥ አዳራሾችዋንም እናፍርስ።


ካህኑ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነውና ከንፈሮቹ እውቀትን ይጠብቁ ዘንድ ይገባቸዋል፥ ሰዎችም ሕግን ከአፉ ይፈልጉ ዘንድ ይገባቸዋል።


በካህኑም በአልዓዛር ፊት ይቁም፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት በኡሪም ፍርድ ይጠይቅለት፤ እርሱ ከእርሱም ጋር የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በቃሉ ይውጡ፥ በቃሉም ይግቡ።


ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ።


እናንተ ግን አትዘግዩ፥ ጠላቶቻችሁንም አባርሩአቸው፥ በኋላም ያሉትን ግደሉ፥ አምላካችሁም እግዚአብሔር በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአቸዋልና ወደ ከተሞቻቸው እንዳይገቡ ከልክሉአቸው አለ።


የእስራኤልም ልጆች የእነዚህን ከተሞች ምርኮ ሁሉ ከብቶቹንም ለራሳቸው ዘረፉ፥ ሰዎቹን ሁሉ ግን እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍ ስለት መቱአቸው፥ እስትንፋስ ያለውንም ሁሉ አላስቀሩም።


ባልዋም ሕልቃና፦ በዓይንሽ ደስ ያሰኘሽን አድርጊ፥ ጡትም እስኪተው ድረስ ተቀመጪ፥ ብቻ እግዚአብሔር ቃሉን ያጽና አላት። ሴቲቱም ልጅዋን እያጠባች ጡት እስኪተው ድረስ በቤትዋ ተቀመጠች።


በነጋውም ሳኦል ሕዝቡን በሦስት ወገን አደረጋቸው፥ ወገግም ባለ ጊዜ ወደ ሰፈሩ መካከል ገቡ፥ ቀትርም እስኪሆን ድረስ አሞናውያንን መቱ፥ የቀሩትም ተበተኑ፥ ሁለትም በአንድ ላይ ሆነው አልቀሩላቸውም።


የኢካቦድ ወንድም የአኪጦብ ልጅ የፊንሐስ ልጅ የዔሊ ልጅ በሴሎ ለእግዚአብሔር ካህን የሆነ ኤፉድም የለበሰ አኪያ አብሮ ነበር፥ ሕዝቡ ዮናታን እንደ ሄደ አላወቁም።


跟着我们:

广告


广告