Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 14:34 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 ሳኦልም፦ በሕዝቡ መካከል እየዞራችሁ፦ እያንዳንዱ ሰው በሬውንና በጉን ወደ እኔ ያቅርብ፥ በዚህም እረዱና ብሉ፥ ከደሙም ጋር በመብላታችሁ እግዚአብሔርን አትበድሉ በሉአቸው አለ። እያንዳንዱም ሰው ሁሉ በእጁ ያለውን በሬውን በዚያች ሌሊት አቀረበ፥ በዚያም አረደው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 እርሱም፣ “በሕዝቡ መካከል እየዞራችሁ፣ ‘እያንዳንዳችሁ በሬዎቻችሁንና በጎቻችሁን አምጡ፤ እዚሁ ዐርዳችሁ ብሉ፤ ነገር ግን ሥጋውን ከነደሙ በመብላት እግዚአብሔርን አትበድሉ’ በሏቸው” አለ። ስለዚህ በዚያች ሌሊት እያንዳንዱ ሰው በሬውን አምጥቶ በዚያ ዐረደው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ሳኦልም፥ “በሕዝቡ መካከል እየዞራችሁ፥ ‘እያንዳንዳችሁ በሬዎቻችሁንና በጎቻችሁን አምጡ፤ እዚሁ ዐርዳችሁ ብሉ፤ ነገር ግን ሥጋውን ከነደሙ በመብላት ጌታን አትበድሉ’ በሏቸው” አለ። ስለዚህ በዚያች ሌሊት እያንዳንዱ ሰው በሬውን አምጥቶ በዚያ አረደው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ከዚህም በኋላ ሌላ ትእዛዝ እንዲህ ሲል አስተላለፈ፤ “ወደ ሕዝቡ ሄዳችሁ ‘የቀንድ ከብቶቻችሁንና በጎቻችሁን ሁሉ አምጡ፤ እነርሱንም ዐርዳችሁ በዚህ ስፍራ መመገብ አለባችሁ፤ ደም ያለበትንም እርጥብ ሥጋ በመብላት በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት አትሥሩ’ ብላችሁ ንገሩአቸው።” ስለዚህም ሕዝቡ ሁሉ በዚያን ሌሊት የቀንድ ከብቶቻቸውንና በጎቻቸውን ሁሉ አምጥተው በዚያ ዐረዱ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ሳኦ​ልም፥ “በሕ​ዝቡ መካ​ከል እየ​ዞ​ራ​ችሁ፦ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው በሬ​ው​ንና በጉን ወደ እኔ ያቅ​ርብ፥ በዚ​ህም እረ​ዱና ብሉ፤ ከደ​ሙም ጋር በመ​ብ​ላ​ታ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አት​በ​ድሉ” በሉ​አ​ቸው አለ። እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ሰው ሁሉ በእጁ ያለ​ውን በዚ​ያች ሌሊት አቀ​ረበ፤ በዚ​ያም አረ​ደው።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 14:34
3 交叉引用  

ነገር ግን ነፍሱ ደሙ ያለችበትን ሥጋ አትብሉ፥


ለሳኦልም፦ እነሆ፥ ሕዝቡ ከደሙ ጋር በመብላታቸው እግዚአብሔርን በደሉ ብለው ነገሩት። ሳኦልም፦ እጅግ ተላለፋችሁ፥ አሁንም ትልቅ ድንጋይ አንከባልላችሁ አቅርቡልኝ አላቸው።


ሳኦልም ለእግዚአብሔር መሠዊያን ሠራ፥ ይኸውም ለእግዚአብሔር የሠራው መጀመሪያ መሠዊያ ነው።


跟着我们:

广告


广告