Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 14:28 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ከሕዝቡም አንድ ሰው መልሶ፦ አባትህ፦ ዛሬ መብል የሚበላ ሰው ርጉም ይሁን ብሎ ሕዝቡን መሐላ አምሎአቸዋል አለው፥ ሕዝቡም ደከሙ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ከዚያም አንዱ ወታደር፣ “አባትህ ሰራዊቱን፣ ‘ዛሬ እህል የሚቀምስ ማንኛውም ሰው የተረገመ ይሁን!’ በማለት በጽኑ መሐላ አስሯል። ሰው ሁሉ የተዳከመው በዚሁ ምክንያት ነው” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ከሕዝቡም አንድ ሰው፥ “አባትህ ሕዝቡን፥ ‘ዛሬ እህል የሚቀምስ ማናቸውም ሰው የተረገመ ይሁን!’ በማለት በጽኑ መሓላ አስጠንቅቆናል” አለው። ሰው ሁሉ ተዳክሞ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ነገር ግን ከወታደሮቹ አንዱ “እኛ ሁላችን በራብ ደክመን ዝለናል፤ አባትህ ግን ‘በዛሬው ዕለት ምንም ዐይነት ምግብ የሚመገብ ሰው የተረገመ ይሁን’ ሲል በብርቱ አስጠንቅቆናል” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ከሕ​ዝ​ቡም አንድ ሰው መልሶ፥ “አባ​ትህ፦ ዛሬ መብል የሚ​በላ ሰው ርጉም ይሁን ብሎ ሕዝ​ቡን መሐላ አም​ሎ​አ​ቸ​ዋል” አለው፤ ሕዝ​ቡም ደከሙ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 14:28
4 交叉引用  

የእስራኤልም ሰዎች በዚያ ቀን ተጨነቁ፥ ሳኦል፦ ጠላቶቼን እስክበቀል እስከ ማታ ድረስ መብል የሚበላ ሰው ርጉም ይሁን ብሎ ሕዝቡን አምሎአቸው ነበርና። ሕዝቡም ሁሉ መብል አልቀመሱም።


ዮናታን ግን አባቱ ሕዝቡን ባማለ ጊዜ አልሰማም ነበር፥ እርሱም በእጁ ያለችውን በትር ጫፍዋን ወደ ወለላው ነከረ፥ እጁንም ወደ አፉ አደረገ፥ ዓይኑም በራ።


ዮናታንም፦ አባቴ ምድሪቱን አስቸገረ፥ ከዚህ ማር ጥቂት ብቀምስ ዓይኔ እንደ በራ እዩ።


ሳኦልም ዮናታንን፦ ያደረግኸውን ንገረኝ አለው፥ ዮናታንም፦ በእጄ ባለው በበትሬ ጫፍ ጥቂት ማር በእርግጥ ቀምሻለሁ፥ እነሆኝ፥ እሞታለሁ ብሎ ነገረው።


跟着我们:

广告


广告