Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 14:19 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ሳኦል ከካህኑ ጋር ሲነጋገር በፍልስጥኤማውያን ሰፈር ግርግርታ እየበዛና እየጠነከረ ሄደ፥ ሳኦልም ካህኑን፦ እጅህን መልስ አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ሳኦል ለካህኑ በመናገር ላይ ሳለ፣ በፍልስጥኤማውያን ሰፈር ሁካታው እየጨመረ ሄደ። ስለዚህ ሳኦል ካህኑን፣ “እጅህን መልስ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ሳኦል ለካህኑ በመናገር ላይ ሳለ፥ በፍልስጥኤማውያን ሰፈር ሁካታው እየጨመረ ሄደ። ስለዚህ ሳኦል ካህኑን፥ “እጅህን መልስ” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ሳኦል ከካህኑ ጋር በመነጋገር ላይ ሳለ፥ በፍልስጥኤማውያን ሰፈር የተነሣው ሁከትና ሽብር እየባሰበት ሄደ፤ ሳኦልም ካህኑን “እግዚአብሔርን ለመጠየቅ አሁን ጊዜ የለንም” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ሳኦ​ልም ከካ​ህኑ ጋር ሲነ​ጋ​ገር በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መን​ደር ግር​ግ​ርታ እየ​በዛ ሄደ፤ ሳኦ​ልም ካህ​ኑን፥ “እጅ​ህን መልስ” አለው።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 14:19
8 交叉引用  

ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በጽዮን ድንጋይን ለመሠረት አስቀምጣለሁ፥ የተፈተነውን፥ የከበረውን፥ መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ፥ የሚያምንም አያፍርም።


በካህኑም በአልዓዛር ፊት ይቁም፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት በኡሪም ፍርድ ይጠይቅለት፤ እርሱ ከእርሱም ጋር የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በቃሉ ይውጡ፥ በቃሉም ይግቡ።


ሰዎቹም ከስንቃቸው ወሰዱ፥ እግዚአብሔርንም አልጠየቁም።


ሳሙኤልም፦ ያደረግኸው ምንድር ነው? አለ። ሳኦልም፦ ሕዝቡ ከእኔ ተለይተው እንደ ተበታተኑ፥ አንተም በቀጠሮው እንዳልመጣህ፥ ፍልስጥኤማውያንም ወደ ማክማስ እንደ ተሰበሰቡ አየሁ፥


ሳኦልና ከእርሱም ጋር የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተሰብስበው ወደ ውጊያው መጡ፥ እነሆም፥ የእያንዳንዱ ሰው ሰይፍ በባልንጀራው ላይ ነበረ፥ እጅግም ታላቅ ድንጋጤ ሆነ።


የእስራኤልም ሰዎች በዚያ ቀን ተጨነቁ፥ ሳኦል፦ ጠላቶቼን እስክበቀል እስከ ማታ ድረስ መብል የሚበላ ሰው ርጉም ይሁን ብሎ ሕዝቡን አምሎአቸው ነበርና። ሕዝቡም ሁሉ መብል አልቀመሱም።


ዳዊትም የአቢሜሌክን ልጅ ካህኑን አብያታርን፦ ኤፉዱን አቅርብልኝ አለው፥ አብያታርም ኤፋዱን ለዳዊት አቀረበለት።


跟着我们:

广告


广告