Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 13:2 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ሳኦል ሦስት ሺህ ሰዎች ከእስራኤል መረጠ፥ ሁለቱም ሺህ በማክማስና በቤቴል ተራራ ከሳኦል ጋር ነበሩ፥ አንዱም ሺህ በብንያም ጊብዓ ከዮናታን ጋር ነበሩ፥ የቀረውንም ሕዝብ እያንዳንዱ ወደ ድንኳኑ አሰናበተ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ሳኦል ከእስራኤል ሦስት ሺሕ ሰዎች መረጠ። ሁለቱ ሺሕ በማክማስና በኰረብታማው አገር በቤቴል ከሳኦል ጋራ፣ አንዱ ሺሕ ደግሞ በብንያም ግዛት በጊብዓ ከዮናታን ጋራ ነበሩ። የቀሩትን ሰዎች ግን ወደ የቤታቸው እንዲሄዱ አሰናበተ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ሳኦል ሦስት ሺህ ሰዎች ከእስራኤል መረጠ፤ ሁለቱ ሺህ በማክማስና በተራራማው አገር በቤቴል ከሳኦል ጋር፥ አንዱ ሺህ ደግሞ በብንያም ግዛት በጊብዓ ከዮናታን ጋር ነበሩ። የቀሩትን ሰዎች ግን ወደ ድንኳኖቻቸው እንዲሄዱ አሰናበተ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ከእስራኤል ሕዝብ መካከል የተውጣጡ ሦስት ሺህ ሰዎችን መረጠ፤ ከእነርሱ መካከል ሁለቱን ሺህ በሚክማስና በቤትኤል በሚገኘው ኮረብታማ አገር ከእርሱ ጋር እንዲሆኑ መደበ፤ አንዱን ሺህ ሰዎች ደግሞ ከልጁ ከዮናታን ጋር በማሰለፍ በብንያም ነገድ ግዛት ውስጥ ጊብዓ ተብሎ ወደሚጠራው ኮረብታማ አገር ላከ፤ ከዚህ የተረፉትን ሌሎች ሰዎች ግን ወደየቤታቸው አሰናበተ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ያን​ጊ​ዜም ሳኦል ሦስት ሺህ ሰዎ​ችን ከእ​ስ​ራ​ኤል መረጠ፤ ሁለ​ቱም ሺህ በማ​ኪ​ማ​ስና በቤ​ቴል ተራራ ከሳ​ኦል ጋር ነበሩ፤ አን​ዱም ሺህ በብ​ን​ያም ገባ​ዖን ከልጁ ከዮ​ና​ታን ጋር ነበሩ፤ የቀ​ረ​ው​ንም ሕዝብ እያ​ን​ዳ​ን​ዱን ወደ ድን​ኳኑ አሰ​ና​በተ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 13:2
24 交叉引用  

እንዲህም ሆነ፥ አንድ ብንያማዊ የቢክሪ ልጅ ስሙ ሳቤዔ የሚባል ምናምንቴ ሰው ነበረ፥ እርሱም፦ ከዳዊት ዘንድ እድል ፈንታ የለንም፥ ከእሴይም ልጅ ዘንድ ርስት የለንም፥ እስራኤል ሆይ፥ እያንዳንድህ ወደ ድንኳንህ ተመለስ ብሎ ቀንደ መለከት ነፋ።


ካሰበው ሰው ልጆች ሰባት ሰዎች አሳልፈህ ስጠንና ከእግዚአብሔር በተመረጠው በሳኦል አገር በጊብዓ ለእግዚአብሔር እንሰቅላቸዋለን አሉት። ንጉሡም፦ እሰጣችኋለሁ አለ።


ነጦፋዊው ኖኤሬ፥ የነጦፋዊው የበዓና ልጅ ሔሌብ፥ ከብንያም ወገን ከጊብዓ የሪባይ ልጅ ኢታይ፥


የማክማስ ሰዎች፥ መቶ ሀያ ሁለት።


የብንያምም ልጆች ከጌባ ጀምሮ በማክማስ፥ በጋያ፥


ኢያሱም መረቃቸው፥ ሰደዳቸውም፥ ወደ ቤታቸውም ሄዱ።


ጌታውም፦ ከእስራኤል ወገን ወዳልሆነች ወደ እንግዳ ከተማ አንገባም፥ እኛ ወደ ጊብዓ እንለፍ አለው።


ሳኦልም ወደ ቤቱ ወደ ጊብዓ ሄደ፥ እግዚአብሔር ልባቸውን የነካ ኃያላንም ከእርሱ ጋር ሄዱ።


ከዚያም በኋላ የፍልስጥኤማውያን ጭፍራ ወዳለበት ወደ እግዚአብሔር ኮረብታ ትመጣለህ፥ ወደዚያም ወደ ከተማይቱ በደረስህ ጊዜ፥ በገናና ከበሮ እምቢልታና መሰንቆ ይዘው ትንቢት እየተናገሩ ከኮረብታው መስገጃ የሚወርዱ የነቢያት ጉባኤ ያገኙሃል።


ሳኦልም በእስራኤል ላይ ሁለት ዓመት ከነገሠ በኋላ፥


ሳሙኤልም፦ ያደረግኸው ምንድር ነው? አለ። ሳኦልም፦ ሕዝቡ ከእኔ ተለይተው እንደ ተበታተኑ፥ አንተም በቀጠሮው እንዳልመጣህ፥ ፍልስጥኤማውያንም ወደ ማክማስ እንደ ተሰበሰቡ አየሁ፥


ሳሙኤልም ከጌልገላ ተነሥቶ መንገዱን ሄደ፥ የቀሩትም ሕዝብ ሳኦልን ተከትለው ሰልፈኞቹን ሊገናኙ ሄዱ። ከጌልገላም ተነሥተው ወደ ብንያም ጊብዓ መጡ፥ ሳኦልም ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሕዝብ ቆጠረ፥ ስድስት መቶም የሚያህሉ ሰዎች ነበሩ።


ሳኦልና ልጁ ዮናታንም ከእርሱም ጋር የነበሩ ሕዝብ በብንያም ጊብዓ ተቀመጡ፥ ፍልስጥኤማውያንም በማክማስ ሰፈሩ።


ፍልስጥኤማውያንም ከእስራኤል ጋር ለመዋጋት ተሰበሰቡ፥ ሠላሳ ሺህ ሰረገሎች ስድስትም ሺህ ፈረሰኞች በባሕርም ዳር እንዳለ አሸዋ ብዙ ሕዝብ ነበሩ፥ ወጥተውም ከቤትአዌን በምሥራቅ በኩል በማክማስ ሰፈሩ።


በዚያም ቀን ፍልስጥኤማውያንን ከማክማስ እስከ ኤሎን ድረስ መቱአቸው፥ ሕዝቡም እጅግ ደከሙ።


አንዱም ሾጣጣ በማክማስ አንጻር በሰሜን በኩል፥ ሁለተኛውም በጊብዓ አንጻር በደቡብ በኩል የቆሙ ነበሩ።


በሳኦልም ዕድሜ ሁሉ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጽኑ ውጊያ ነበረ፥ ሳኦልም ጽኑ ወይም ኃያል ሰው ባየ ጊዜ ወደ እርሱ ይሰበስብ ነበር።


ሳሙኤልም ወደ አርማቴም ሄደ፥


በመንገድም አጠገብ ወዳሉት የበጎች ማደሪያዎች መጣ፥ በዚያም ዋሻ ነበረ፥ ሳኦልም ወገቡን ይሞክር ዘንድ ከዚያ ገባ፥ ዳዊትና ሰዎቹም ከዋሻው በውስጠኛው ቦታ ተቀምጠው ነበር።


ሳኦልም ተነሥቶ ዳዊትን በዚፍ ምድረ በዳ ይሻ ዘንድ ከእስራኤል የተመረጡ ሦስት ሺህ ሰዎች ይዞ ወደ ዚፍ ምድረ በዳ ወረደ።


እንዲህም አለ፦ በእናንተ ላይ የሚነግሠው የንጉሡ ወግ ይህ ነው፥ ወንዶች ልጆቻችሁን ወስዶ ሰረገለኞችና ፈረሰኞች ያደርጋቸዋል፥ በሰረገሎቹም ፊት ይሮጣሉ፥


跟着我们:

广告


广告