Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 12:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 አምላካቸውንም እግዚአብሔርን ረሱ፥ ለአሶር ሠራዊትም አለቃ ለሲሣራ እጅ፥ ለፍልስጥኤማውያንም እጅ፥ ለሞዓብም ንጉሥ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፥ ከእነርሱም ጋር ተዋጉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “እነርሱ ግን አምላካቸውን እግዚአብሔርን ረሱት፤ ስለዚህ ለአሦር የጦር አዛዥ ለሲሣራ፣ ለፍልስጥኤማውያንና ለሞዓብ ንጉሥ አሳልፎ ሸጣቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እነርሱ ግን አምላካቸውን ጌታን ረሱት፤ ስለዚህ ለሓጾር የጦር አዛዥ ለሲሣራ፥ ለፍልስጥኤማውያንና ለሞዓብ ንጉሥ አሳልፎ ሰጣቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ነገር ግን ሕዝቡ አምላካቸውን እግዚአብሔርን ረሱ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የሓጾር ሠራዊት አዛዥ ለነበረው ለሲሣራ፥ ለፍልስጥኤማውያን፥ ለሞአብም ንጉሥ አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም እስራኤላውያንን ድል ነሡ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 አም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረሱ፤ ለአ​ሶር ሠራ​ዊ​ትም አለቃ ለሲ​ሣራ እጅ፥ ለፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም እጅ፥ ለሞ​ዓ​ብም ንጉሥ እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ወጉ​አ​ቸው፤

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 12:9
15 交叉引用  

እተክለውማለሁ፥ በስፍራውም ይቀመጣል፥ ከዚያም በኋላ አይናወጥም፥ እንደ ቀድሞው ዘመንና በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ፈራጆች እንዳስነሣሁበት ጊዜ ግፈኞች ተመልሰው አያስጨንቁትም፥ ከጠላቶችህም አሳርፍሃለሁ። እግዚአብሔርም ደግሞ፦ ቤት እሠራልሃለሁ ብሎ ይነግርሃል።


እነርሱ ግን ዐመፁ ቅዱስ መንፈሱንም አስመረሩ፥ ስለዚህ ተመልሶ ጠላት ሆናቸው፥ እርሱም ተዋጋቸው።


በውኑ ቆንጆ ጌጥዋን ወይስ ሙሽራ ዝርግፍ ጌጥዋን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን የማይቈጠር ወራት ረስቶኛል።


የወለደህን አምላክ ተውህ፥ 2 ያሳደገህን እግዚአብሔርን ረሳህ።


እርሱ አምላካቸው ካልሸጣቸው፥ 2 እግዚአብሔርም አሳልፎ ካልሰጣቸው፥ 2 አንድ ሰው እንዴት ሺህን ያሳድድ ነበር? 2 ሁለቱሳ እንዴት አሥሩን ሺህ ያሸሹ ነበር?


የእግዚአብሔርም ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፥ በፍልስጥኤማውያንና በአሞን ልጆች እጅ አሳልፎ ሰጣቸው።


የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፥ እግዚአብሔርም በፍልስጥኤማውያን እጅ አርባ ዓመት አሳልፎ ሰጣቸው።


የእግዚአብሔርም ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፥ ወደ ማረኩአቸውም ማራኪዎች እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፥ በዙሪያቸውም ባሉት በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፥ ጠላቶቻቸውንም ከዚያ ወዲያ ሊቋቋሙ አልቻሉም።


የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፥ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ስለ ሠሩ እግዚአብሔር የሞዓብን ንጉሥ ዔግሎምን በእስራኤል ላይ አበረታባቸው።


ከእርሱም በኋላ የዓናት ልጅ ሰሜጋር ተነሣ፥ ከፍልስጥኤማውያንም ስድስት መቶ ሰው በበሬ መውጊያ ገደለ፥ እርሱም ደግሞ እስራኤልን አዳነ።


እግዚአብሔርም በአሶር በነገሠው በከነዓን ንጉሥ በኢያቢስ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፥ የሠራዊቱም አለቃ በአሕዛብ አሪሶት የተቀመጠው ሲሣራ ነበረ።


ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃል ባትሰሙ፥ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ላይ ብታምፁ፥ በእናንተና በንጉሣችሁ ላይ የእግዚአብሔር እጅ ትሆናለች።


跟着我们:

广告


广告