Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 12:24 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ብቻ እግዚአብሔርን ፍሩ፥ ያደረገላችሁንም ታላቅ ነገር አይታችኋልና በፍጹም ልባችሁ በእውነት አምልኩት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ብቻ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ በፍጹም ልባችሁ በታማኝነት አምልኩት፤ ያደረገላችሁንም ታላላቅ ነገሮች አትርሱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ብቻ ጌታን ፍሩ፤ በፍጹም ልባችሁ በታማኝነት አምልኩት፤ ያደረገላችሁንም ታላላቅ ነገሮች አስቡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እግዚአብሔርን ብቻ ፍሩ፤ ያደረገላችሁን ድንቅ ነገሮች ተመልክታችሁ በፍጹም ልባችሁ በታማኝነት አገልግሉት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ብቻ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍሩ፤ ያደ​ረ​ገ​ላ​ች​ሁ​ንም ታላቅ ነገር አይ​ታ​ች​ኋ​ልና በፍ​ጹም ልባ​ችሁ በእ​ው​ነት አም​ል​ኩት፤

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 12:24
17 交叉引用  

አምላካችሁን እግዚአብሔርን ፍሩ፤ እርሱም ከጠላቶቻችሁ ሁሉ እጅ ያድናችኋል።


ሰውንም፦ እነሆ፥ እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፥ ከኃጢአትም መራቅ ማስተዋል ነው አለው።


ደሙም ባላችሁበት ቤቶች ምልክት ይሆንላችኋል፤ ደሙንም ባየሁ ጊዜ ከእናንተ አልፋለሁ፤ እኔም የግብፅን አገር በመታሁ ጊዜ መቅሰፍቱ ለጥፋት አይመጣባችሁም።


የነገሩን ሁሉ ፍጻሜ እንስማ፥ ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና፥ እግዚአብሔርን ፍራ፥ ትእዛዙንም ጠብቅ።


መሰንቆና በገና ከበሮና እምብልታም የወይን ጠጅም በግብዣቸው አለ፥ የእግዚአብሔርን ሥራ ግን አልተመለከቱም፥ እጁም ያደረገችውን አላስተዋሉም።


ናትናኤልም፦ ከናዝሬት መልካም ነገር ሊወጣ ይችላልን? አለው። ፊልጶስ፦ መጥተህ እይ አለው።


እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።


ዓይኖችህ ያዩትን እነዚህን ታላላቆች የሚያስፈሩትንም ነገሮች ያደረገልህ እርሱ ክብርህ ነው፥ እርሱም አምላክህ ነው።


እግዚአብሔር በኮሬብ ካደረገው ቃል ኪዳን ሌላ በሞዓብ ምድር ከእስራኤል ልጆች ጋር ያደርገው ዘንድ ሙሴን ያዘዘው የቃል ኪዳኑ ቃሎች እነዚህ ናቸው።


ሙሴም የእስራኤልን ልጆች ሁሉ ጠርቶ አላቸው፦ እግዚአብሔር በፊታችሁ በግብፅ ምድር በፈርዖንና በባሪያዎቹ ሁሉ በምድሩም ሁሉ ያደረገውን ሁሉ፥


አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና።


አሁንም እግዚአብሔርን ፍሩ፥ በፍጹምም በእውነተኛም ልብ አምልኩት፥ አባቶቻችሁም በወንዝ ማዶ በግብፅም ውስጥ ያመለኩአቸውን አማልክት ከእናንተ አርቁ፥ እግዚአብሔርንም አምልኩ።


跟着我们:

广告


广告