Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 12:17 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 የስንዴ መከር ዛሬ አይደለምን? ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፥ እርሱም ነጎድጓድና ዝናብ ይልካል፥ እናንተም ንጉሥ በመለመናችሁ በእግዚአብሔር ፊት ያደረጋችሁት ክፋት ታላቅ እንደ ሆነ ታውቃላችሁ ታያላችሁም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 አሁን የስንዴ መከር ጊዜ አይደለምን? እኔ ነጐድጓድና ዝናብ እንዲልክ ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፤ እናንተም ንጉሥ እንዲነግሥላችሁ በመጠየቃችሁ በእግዚአብሔር ፊት የቱን ያህል የከፋ ድርጊት እንደፈጸማችሁ ያን ጊዜ ታውቃላችሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 አሁን የስንዴ መከር ጊዜ አይደለምን? እኔ ነጐድጓድና ዝናብ እንዲልክ ወደ ጌታ እጮኻለሁ፤ እናንተም ንጉሥ እንዲነግሥላችሁ በመጠየቃችሁ በጌታ ፊት የቱን ያህል የከፋ ድርጊት እንደፈጸማችሁ ያንጊዜ ታውቃላችሁ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እነሆ አሁን እንደምታውቁት የፀሐይ ሙቀት የበዛበት የስንዴ መከር ወራት አይደለምን? ነገር ግን እኔ አሁን እጸልያለሁ፤ እግዚአብሔርም ነጐድጓድና ዝናብ ይልካል፤ ይህም በሚሆንበት ጊዜ ንጉሥ እንዲያነግሥላችሁ በመጠየቃችሁ ምክንያት በደል በመሥራት እግዚአብሔርን ያሳዘናችሁ መሆናችሁን ታረጋግጣላችሁ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 የስ​ንዴ መከር ዛሬ አይ​ደ​ለ​ምን? ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጮ​ኻ​ለሁ፤ እር​ሱም ነጐ​ድ​ጓ​ድ​ንና ዝና​ብን ይል​ካል፤ እና​ን​ተም ንጉሥ በመ​ለ​መ​ና​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ክፋት ታላቅ እንደ ሆነ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ታያ​ላ​ች​ሁም።”

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 12:17
13 交叉引用  

በነጋውም ሙሴ ለሕዝቡ፦ እናንተ ታላቅ ኃጢአት ሠርታችኋል፤ አሁንም ወደ እግዚአብሔር እወጣለሁ፤ ምናልባት ኃጢአታችሁን አስተሰርይላችኋለሁ አላቸው።


እግዚአብሔርም እንደዚህ አለኝ፦ ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም፥ ልቤ ወደዚህ ሕዝብ አይዘነብልም፥ ከፊቴ ጣላቸው፥ ይውጡ።


እግዚአብሔርም በእስራኤል ልጆች እጅ አሞራውያንን አሳልፎ በሰጠ ቀን ኢያሱ እግዚአብሔርን ተናገረ፥ በእስራኤልም ፊት እንዲህ አለ፦ በገባዖን ላይ ፀሐይ ትቁም፥ በኤሎንም ሸለቆ ጨረቃ፥


አሁንም የመረጣችሁትንና የፈለጋችሁትን ንጉሥ እዩ፥ እነሆም፥ እግዚአብሔር ንጉሥ አደረገላችሁ።


ሕዝቡም ሁሉ ሳሙኤልን፦ ንጉሥ በመለመናችን በኃጢአታችን ሁሉ ላይ ይህን ክፋት ጨምረናልና እንዳንሞት ስለ ባሪያዎችህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ አሉት።


ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ይደቅቃሉ፥ በሰማይም ያንጐደጕድባቸዋል፥ እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል፥ ለንጉሡም ኃይል ይሰጣል፥ የመሲሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።


ሳሙኤልም፦ እስራኤልን ሁሉ ወደ ምጽጳ ሰበስቡ፥ ስለ እናንተም ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ አለ።


የሚፈርድልንም ንጉሥ ስጠን ባሉት ጊዜ ነገሩ ሳሙኤልን አስከፋው፥ ሳሙኤልም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።


እግዚአብሔርም ሳሙኤልን አለው፦ በእነርሱ ላይ እንዳልነግሥ እኔን እንጂ አንተን አልናቁምና በሚሉህ ነገር ሁሉ የሕዝቡን ቃል ስማ።


跟着我们:

广告


广告