Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 10:6 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የእግዚአብሔርም መንፈስ በኃይል ይወርድብሃል፥ ከእነርሱም ጋር ትንቢት ትናገራለህ፥ እንደ ሌላ ሰውም ሆነህ ትለወጣለህ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የእግዚአብሔር መንፈስ በኀይል ይወርድብሃል፤ ከእነርሱ ጋራ ትንቢት ትናገራለህ፤ እንደ ሌላ ሰውም ሆነህ ትለወጣለህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የጌታም መንፈስ በኃይል ይወርድብሃል፤ ከእነርሱም ጋር ትንቢት ትናገራለህ፤ እንደ ሌላ ሰውም ሆነህ ትለወጣለህ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 በድንገት የእግዚአብሔር መንፈስ በአንተ ላይ በኀይል ይወርዳል፤ ከእነርሱም ጋር ትንቢት መናገር ትጀምራለህ፤ ልዩ ሰውም ትሆናለህ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በአ​ንተ ይወ​ር​ዳል፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ትን​ቢት ትና​ገ​ራ​ለህ፤ እንደ ሌላም ሰው ሆነህ ትለ​ወ​ጣ​ለህ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 10:6
14 交叉引用  

እኔም እወርዳለሁ፥ በዚያም እነጋገርሃልሁ፥ በአንተ ካለውም መንፈስ ወስጄ በእነርሱ ላይ አደርገዋለሁ፤ አንተም ብቻ እንዳትሸከም የሕዝቡን ሸክም ከአንተ ጋር ይሸከማሉ።


እግዚአብሔር በደመናው ወረደ፥ ተናገረውም፥ በእርሱም ላይ ከነበረው መንፈስ ወስዶ በሰባው ሽማግሌዎች ላይ አደረገ፤ መንፈሱም በላያቸው ባደረ ጊዜ ትንቢት ተናገሩ፤ ከዚያ በኋል ግን አልተናገሩም።


ከእነርሱም ሁለት ሰዎች በሰፈር ቀርተው ነበር፥ የአንዱም ስም ኤልዳድ የሁለተኛውም ሞዳድ ነበረ፤ መንፈስም ወረደባቸው፤ እነርሱም ከተጻፉት ጋር ነበሩ ወደ ድንኳኑ ግን አልወጡም ነበር፤ በሰፈሩም ውስጥ ሳሉ ትንቢት ተናገሩ።


ሙሴም፦ የእግዚአብሔር ሕዝብ ሁሉ ነቢያት ቢሆኑ፥ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ መንፈሱን ቢያወርድ፤ አንተ ስለእኔ ትቀናለህን? አለው።


በዚያ ቀን ብዙዎች፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን? በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።


የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ በኃይል ወረደ፥ ጠቦትን እንደሚቆራርጥ በእጁ ምንም ሳይኖር ቈራረጠው፥ ያደረገውንም ለአባቱና ለእናቱ አልነገረም።


ወደ ሌሒ በመጣ ጊዜም ፍልስጥኤማውያን እልል እያሉ ተገናኙት። የእግዚአብሔርም መንፈስ በኃይል ወረደበት፥ ክንዱም የታሰረበት ገመድ በእሳት እንደ ተበላ እንደ ተልባ እግር ፈትል ሆነ፥ ማሰሪያዎቹም ከእጁ ወደቁ።


የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ መጣ፥ በእስራኤልም ላይ ይፈርድ ነበር፥ ለሰልፍ ወጣ፥ እግዚአብሔርም የመሰጴጦምያን ንጉሥ ኩሰርሰቴምን በእጁ አሳልፎ ሰጠው፥ እጁም በኩሰርሰቴም ላይ አሸነፈች።


ወደዚያም ኮረብታ በደረሰ ጊዜ፥ እነሆ፥ የነቢያት ጉባኤ አገኙት፥ የእግዚአብሔርም መንፈስ በኃይል ወረደበት፥ በመካከላቸውም ትንቢት ተናገረ።


ከሳሙኤልም ዘንድ ለመሄድ ፊቱን በመለሰ ጊዜ እግዚአብሔር ሌላ ልብ ለወጠለት፥ በዚያም ቀን እነዚህ ምልክቶች ሁሉ ደረሱለት።


ይህንም ነገር በሰማው ጊዜ በሳኦል ላይ የእግዚአብሔር መንፈስ በኃይል ወረደ፥ ቁጣውም እጅግ ነደደ።


ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ ወስዶ በወንድሞቹ መካከል ቀባው። የእግዚአብሔርም መንፈስ ከዚያ ቀን ጀምሮ በዳዊት ላይ በኃይል መጣ። ሳሙኤልም ተነሥቶ ወደ አርማቴም ሄደ።


ሳኦልም ዳዊትን ያመጡት ዘንድ መልእክተኞችን ሰደደ፥ የነቢያት ጉባኤ ትንቢት ሲናገሩ፥ ሳሙኤልም አለቃቸው ሆኖ ሲቆም ባዩ ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በሳኦል መልእክተኞች ላይ ወረደ፥ እነርሱም ትንቢት ይናገሩ ጀምር።


跟着我们:

广告


广告