Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 10:22 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ከእግዚአብሔርም፦ ገና ወደዚህ የሚመጣ ሰው አለን? ብለው ደግሞ ጠየቁት እግዚአብሔርም፦ እነሆ፥ በዕቃ መካከል ተሸሽጎአል ብሎ መለሰ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ሰዎቹም፣ “ሰውየው መጥቷልን?” ሲሉ እግዚአብሔርን ጠየቁ። እግዚአብሔርም፣ “አዎን፤ ነገር ግን በዕቃ መካከል ተሸሽጓል” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ሰዎቹም፥ “ሰውየው መጥቷልን?” ሲሉ ጌታን ጠየቁ። ጌታም፥ “አዎን፤ ነገር ግን በዕቃ መካከል ተሸሽጓል” አለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ስለዚህም እነርሱ “ሌላ የቀረ ይኖር ይሆን?” ሲሉ እግዚአብሔርን ጠየቁ። እግዚአብሔርም “ሳኦል እነሆ በዕቃ መካከል ተደብቆ ይገኛል” ሲል መለሰላቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ሳሙ​ኤ​ልም፦ ያ ሰው እዚህ ይመጣ እንደ ሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “እነሆ፥ በዕቃ መካ​ከል ተሸ​ሽ​ጎ​አል” ብሎ መለሰ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 10:22
19 交叉引用  

ልጆችም በሆድዋ ውስጥ ይገፋፋ ነበር፤ እርስዋም፦ እንዲህ ከሆነ ይህ ለእኔም ምኔ ነው? አለች። ከእግዚአብሔርም ትጠይቅ ዘንድ ሄደች።


ከዚያም በኋላ ዳዊት፦ ከይሁዳ ከተሞች ወደ አንዲቱ ልውጣን? ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም፦ ውጣ አለው። ዳዊትም፦ ወዴት ልውጣ? አለ። እርሱም፦ ወደ ኬብሮን ውጣ አለው።


በዳዊትም ዘመን ሦስት ዓመት ያህል ቀጥሎ ቀጥሎ ራብ ሆነ፥ ዳዊትም የእግዚአብሔርን ፊት ጠየቀ። እግዚአብሔርም፦ የገባዖንን ሰዎች ስለ ገደለ በሳኦልና በቤቱ ላይ ደም አለበት አለ።


በካህኑም በአልዓዛር ፊት ይቁም፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት በኡሪም ፍርድ ይጠይቅለት፤ እርሱ ከእርሱም ጋር የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በቃሉ ይውጡ፥ በቃሉም ይግቡ።


ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፥ ራሱንም የሚያዋርድ ከፍ ይላል።


እንዲህም ሆነ፥ ኢያሱ ከሞተ በኋላ የእስራኤል ልጆች፦ ከነዓናውያንን ለመውጋት ማን በፊት ይወጣልናል? ብለው እግዚአብሔርን ጠየቁ።


የእስራኤልም ልጆች ተነሥተው ወደ ቤቴል ወጡ፥ እግዚአብሔርንም፦ የብንያምን ልጆች ለመውጋት አስቀድሞ ማን ይውጣልን? ብለው ጠየቁት፥ እግዚአብሔርም፦ ይሁዳ ይቅደም አለ።


የእስራኤልም ልጆች ወጥተው በእግዚአብሔር ፊት እስከ ማታ ድረስ አለቀሱ፥ እግዚአብሔርንም፦ ከወንድሞቻችን ከብንያም ልጆች ጋር ለመዋጋት ዳግመኛ እንቀርባለን? ብለው ጠየቁ። እግዚአብሔርም፦ በእነርሱ ላይ ውጡ አለ።


የብንያምንም ነገድ በየወገናቸው አቀረበ፥ ዕጣውም በማጥሪ ወገን ላይ ወደቀ። የማጥሪንም ወገን በየሰዉ አቀረበ፥ ዕጣውም በቂስ ልጅ በሳኦል ላይ ወደቀ፥ ፈለጉትም፥ አላገኙትምም።


ሳኦልም፦ ፍልስጥኤማውያንን ልከተልን? በእስራኤልስ እጅ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን? ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀው። በዚያ ቀን ግን አልመለሰለትም።


ሳሙኤልም አለ፦ በዓይንህ ምንም ታናሽ ብትሆን ለእስራኤል ነገዶች አለቃ አልሆንህምን? እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባህ።


እግዚአብሔርንም ጠየቀለት፥ ስንቅንም ሰጠው፥ የፍልስጥኤማዊውንም የጎልያድን ሰይፍ ሰጠው አለው።


ዳዊትም ሳኦል ክፉን እንዳሰበበት አወቀ፥ ካሁኑን አብያታርንም፦ ኤፉዱን ወደዚህ አምጣ አለው።


ዳዊትም የአቢሜሌክን ልጅ ካህኑን አብያታርን፦ ኤፉዱን አቅርብልኝ አለው፥ አብያታርም ኤፋዱን ለዳዊት አቀረበለት።


ዳዊትም፦ የእነዚህን ሠራዊት ፍለጋ ልከተልን? አገኛቸዋለሁን? ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ፥ እርሱም፦ ታገኛቸዋለህና፥ ፈጽመህም ምርኮውን ትመልሳለህና ፍለጋቸውን ተከተል ብሎ መለሰለት።


ሳኦልም መልሶ፦ እኔ ከእስራኤል ነገዶች ከሚያንስ ወገን የሆንሁ ብንያማዊ አይደለሁምን? ወገኔስ ከብንያም ነገድ ወገኖች ሁሉ የሚያንስ አይደለምን? እንዲህስ ያለውን ነገር ለምን ነገርኸኝ? አለ።


跟着我们:

广告


广告