Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 10:20 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ሳሙኤልም የእስራኤልን ነገዶች ሁሉ አቀረበ፥ ዕጣውም በብንያም ነገድ ላይ ወደቀ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ሳሙኤል የእስራኤልን ነገዶች ሁሉ ባቀረበ ጊዜ፣ የብንያም ነገድ ተመረጠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ሳሙኤል የእስራኤልን ነገዶች ሁሉ ባቀረበ ጊዜ፥ የብንያም ነገድ ተመረጠ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ከዚህ በኋላ ሳሙኤል እያንዳንዱ ነገድ ወደ ፊት እንዲቀርብ አደረገ፤ የብንያምም ነገድ በዕጣ ተመረጠ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ሳሙ​ኤ​ልም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ነገ​ዶች ሁሉ አቀ​ረበ፤ ዕጣ​ውም በብ​ን​ያም ወገን ላይ ወደቀ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 10:20
9 交叉引用  

አበኔርም ደግሞ በብንያም ወገን ጆሮ ተናገረ፥ አበኔርም ደግሞ በእስራኤልና በብንያም ቤት ሁሉ መልካም የነበረውን ለዳዊት ሊነግረው ወደ ኬብሮን ሄደ።


ስለ ብንያምም እንዲህ አለ፦ 2 በእግዚአብሔር የተወደደ በእርሱ 2 ዘንድ ተማምኖ ይኖራል፤ 2 ቀኑን ሁሉ ይጋርደዋል፥ 2 በትከሻውም መካከል ያድራል።


ዛሬ ግን ከመከራችሁና ከጭንቃችሁ ሁሉ ያዳናችሁን አምላክቻሁን ንቃችሁ፦ እንዲህ አይሁን፥ ነገር ግን ንጉሥ አንግሥልን አላችሁት። አሁንም በየነገዳችሁና በየወገናችሁ ወደ እግዚአብሔር ፊት ቅረቡ አላቸው።


የብንያምንም ነገድ በየወገናቸው አቀረበ፥ ዕጣውም በማጥሪ ወገን ላይ ወደቀ። የማጥሪንም ወገን በየሰዉ አቀረበ፥ ዕጣውም በቂስ ልጅ በሳኦል ላይ ወደቀ፥ ፈለጉትም፥ አላገኙትምም።


ሳኦልም፦ እናንተ የሕዝቡ አለቆች ሁሉ፥ ወደዚህ ቅረቡ፥ ዛሬ ይህ ኃጢአት በምን እንደ ሆነ እወቁ፥ ተመልከቱም፥ እስራኤልን የሚያድን ሕያው እግዚአብሔርን! ኃጢአቱ በልጄ በዮናታን ቢሆን ፈጽሞ ይሞታል አለ። ከሕዝቡም ሁሉ አንድ የመለሰለት ሰው አልነበረም።


ሳኦልም የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን፦ እውነትን ግለጥ አለው። ሳኦልና ዮናታንም ተያዙ፥ ሕዝቡም ነጻ ሆነ።


跟着我们:

广告


广告