1 ሳሙኤል 1:24 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 ጡትም በተወ ጊዜ ከእርስዋ ጋር እርሱንና አንድ የሦስት ዓመት ወይፈን፥ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ዱቄት፥ አንድ አቁማዳ የወይን ጠጅ ይዛ ወደ ሴሎ ወደ እግዚአብሔር ቤት አመጣችው፥ ሕፃኑም ገና ታናሽ ነበረ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም24 ልጁ ጡት በተወ ጊዜ ከርሱ ጋራ አንድ የሦስት ዓመት ወይፈን፣ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ዱቄትና አንድ አቍማዳ የወይን ጠጅ ወስዳ፣ በሴሎ ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት አመጣችው፣ ልጁም ገና ሕፃን ነበረ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 ልጁ ጡት በተወ ጊዜ ከእርሱ ጋር አንድ የሦስት ዓመት ወይፈን፥ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ዱቄትና አንድ አቁማዳ የወይን ጠጅ ወስዳ፥ በሴሎ ወዳለው ወደ ጌታ ቤት አመጣችው፤ ልጁም ገና ሕፃን ነበረ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 ጡት ካስጣለችውም በኋላ ወደ ሴሎ ይዛው ወጣች፤ ከእርሱም ጋር የሦስት ዓመት ኰርማ ዐሥር ኪሎ ዱቄትና አንድ አቁማዳ ሙሉ የወይን ጠጅ ይዛ ሄደች፤ ሳሙኤልንም ገና በልጅነቱ በሴሎ ወደሚገኘው ወደ እግዚአብሔር ቤት ወሰደችው፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 እርስዋም ከእርሱ ጋር አንድ የሦስት ዓመት ወይፈን፥ እንጀራ፥ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ዱቄት፥ አንድ አቁማዳ የወይን ጠጅ ይዛ ወደ ሴሎ ወጣች። በሴሎም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት ገባች። ልጃቸውም ከእነርሱ ጋር ነበረ። 参见章节 |