Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 1:17 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ዔሊም፦ በደኅና ሂጂ፥ የእስራኤልም አምላክ የለመንሽውን ልመና ይስጥሽ ብሎ መለሰላት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ዔሊም፣ “በሰላም ሂጂ፤ የእስራኤል አምላክ የለመንሽውን ይስጥሽ” ሲል መለሰላት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ከዚያም ዔሊ፥ “በሰላም ሂጂ! የእስራኤል አምላክ የለመንሽውን ይስጥሽ!” አላት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ዔሊም “በሰላም ሂጂ! የእስራኤል አምልክ የለመንሽውን ይስጥሽ!” አላት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ዔሊም፥ “በሰ​ላም ሂጂ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ከአ​ንቺ ጋር ይሁን የለ​መ​ን​ሽ​ው​ንም ልመና ሁሉ ይስ​ጥሽ” ብሎ መለ​ሰ​ላት።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 1:17
14 交叉引用  

ይስሐቅም ስለሚስቱ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፥ መካን ነበረችና፤ እግዚአብሔርም ተለመነው፥ ርብቃም ሚስቱ ፀነሰች።


ንጉሡም፦ በደኅና ሂድ አለው፥ ተነሥቶም ወደ ኬብሮን ሄደ።


እርሱም “በደኅና ሂድ፤” አለው። ጥቂት ርቀትም ያህል ከእርሱ ራቀ።


ያቤጽም “እባክህ! መባረክን ባርከኝ፤ አገሬንም አስፋው፤ እጅህም ከእኔ ጋር ትሁን፤ እንዳያሳዝነኝም ከክፋት ጠብቀኝ፤” ብሎ የእስራኤልን አምላክ ጠራ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።


እርሱም፦ ልጄ ሆይ፥ እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ ከሥቃይሽም ተፈወሽ አላት።


ሴቲቱንም፦ እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ አላት።


እርሱም፦ ልጄ ሆይ፥ እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ አላት።


እርሱም፦ የምትሄዱበት መንገድ በእግዚአብሔር ፊት ነውና በደኅና ሂዱ አላቸው።


ኀዘኔና ጭንቀቴ ስለ በዛ እስከ አሁን ድረስ ተናግሬአለሁና ባሪያህን እንደ ምናምንቴ ሴት አትቍጠረኝ ብላ መለሰችለት።


ባልዋም ሕልቃና፦ በዓይንሽ ደስ ያሰኘሽን አድርጊ፥ ጡትም እስኪተው ድረስ ተቀመጪ፥ ብቻ እግዚአብሔር ቃሉን ያጽና አላት። ሴቲቱም ልጅዋን እያጠባች ጡት እስኪተው ድረስ በቤትዋ ተቀመጠች።


ዮናታንም ዳዊትን፦ በደኅና ሂድ፥ እነሆ፥ እኛ ሁለታችን በእኔና በአንተ፥ በዘሬና በዘርህ መካከል ለዘላለም እግዚአብሔር ይሁን ብለን በእግዚአብሔር ስም ተማምለናል አለው። ዳዊትም ተነሥቶ ሄደ፥ ዮናታንም ወደ ከተማ ገባ።


ዳዊትም ያመጣችውን ከእጅዋ ተቀብሎ፦ በደኅና ወደ ቤትሽ ሂጂ፥ እነሆ፥ ቃልሽን ሰማሁ፥ ፊትሽንም አከበርሁ አላት።


አሁንም ተመልሰህ በደኅና ሂድ፥ በፍልስጥኤማውያንም አለቆች ዓይን ክፋት አታድርግ አለው።


跟着我们:

广告


广告