Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 1:1 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በተራራማው በኤፍሬም አገር ከአርማቴም መሴፋ የሆነ ስሙ ሕልቃና የተባለ ኤፍሬማዊ ሰው ነበረ፥ እርሱም የኢያሬምኤል ልጅ የኢሊዮ ልጅ የቶሑ ልጅ የናሲብ ልጅ ነበረ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በተራራማው በኤፍሬም አገር በአርማቴም መሴፋ የሚኖር ሕልቃና የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም ኤፍሬማዊ ሲሆን፣ የኤያሬምኤል ልጅ፣ የኢሊዩ ልጅ፣ የቶሑ ልጅ፣ የናሲብ ልጅ፣ ነበረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በተራራማው በኤፍሬም አገር በአርማቴም መሴፋ የሚኖር ሕልቃና የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም የይሮሐም ልጅ፥ የኤሊዩ ልጅ፥ የቶሑ ልጅ፥ የናሲብ ልጅ ሲሆን ከኤፍሬም ነገድ ነበረ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ራማ ተብላ በምትጠራ ትንሽ ከተማ የሚኖር ትውልዱ ከኤፍሬም ነገድ የሆነ፥ ሕልቃና ተብሎ የሚጠራ አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም የይሮሐም ልጅ የኤሊሁ የልጅ ልጅ ሲሆን፥ ኤሊሁ ደግሞ የቶሑ ልጅ የጹፍ የልጅ ልጅ ነበር፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በተ​ራ​ራ​ማው በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ከአ​ር​ማ​ቴም መሴፋ የሆነ አንድ ሰው ነበረ። ስሙም፥ የና​ሲብ ልጅ የቴቆ ልጅ፥ የኤ​ልዩ ልጅ ፥ የኢ​ያ​ር​ም​ያል ልጅ፥ ኤፍ​ራ​ታ​ዊው ሕል​ቃና ነበረ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 1:1
21 交叉引用  

ከሳሪራ አገር የሆነ የሰሎሞን ባሪያ የኤፍሬማዊው የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም በንጉሡ ላይ ዐመፀ፤ እናቱም ጽሩዓ የተባለች ባልቴት ሴት ነበረች።


አኪጦብም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም ሰሎምን ወለደ፤


የቀዓት ልጆች፤ ልጁ አሚናዳብ፥ ልጁ ቆሬ፥ ልጁ አሴር፥


አገልጋዮቹና ልጆቹ እነዚህ ናቸው፤ ከቀዓት ልጆች ዘማሪው ኤማን ነበረ፤ እርሱም የኢዮኤል ልጅ፥ የሳሙኤል ልጅ፥


የሕልቃና ልጅ፥ የይሮሐም ልጅ፥ የኤሊኤል ልጅ፥ የቶዋ ልጅ፥


በመሸም ጊዜ ዮሴፍ የተባለው ባለ ጠጋ ሰው ከአርማትያስ መጣ፥ እርሱም ደግሞ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ነበረ፤


የአሮንም ልጅ አልዓዛር ሞተ፥ በተራራማውም በኤፍሬም አገር ለልጁ ለፊንሐስ በተሰጠችው በጊብዓ መሬት ቀበሩት።


ገለዓዳውያንም ኤፍሬም የሚያልፍበትን የዮርዳኖስን መሻገርያ ያዙባቸው፥ የሸሸም የኤፍሬም ሰው፦ ልለፍ ባለ ጊዜ፥ የገለዓድ ሰዎች፦ አንተ ኤፍሬማዊ ነህን? አሉት፥ እርሱም፦ አይደለሁም ቢል፥


በተራራማውም በኤፍሬም አገር ሚካ የተባለ አንድ ሰው ነበረ።


በዚያም ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉሥ በሌለበት ጊዜ በተራራማው በኤፍሬም አገር ማዶ የተቀመጠ ሌዋዊ ነበረ፥ ከቤተ ልሔምም ይሁዳ ቁባት አገባ።


እርስዋም በተራራማው በኤፍሬም አገር በራማና በቤቴል መካከል ካለው የዲቦራ ዛፍ ከሚባለው ከዘንባባው በታች ተቀምጣ ነበር፥ የእስራኤልም ልጆች ወደ እርስዋ ለፍርድ ይወጡ ነበር።


የሰውዮውም ስም አቤሜሌክ፥ የሚስቱም ስም ኑኃሚን፥ የሁለቱም ልጆች ስም መሐሎንና ኬሌዎን ነበረ፤ የቤተ ልሔም ይሁዳም የኤፍራታ ሰዎች ነበሩ። ወደ ሞዓብም ምድር መጡ በዚያም ተቀመጡ።


ቦዔዝም ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤ እሴይም ዳዊትን ወለደ።


ማልደው ተነሥተው በእግዚአብሔር ፊት ሰገዱ፥ ተመልሰውም ወደ አርማቴም ወደ ቤታቸው መጡ። ሕልቃናም ሚስቱን ሐናን አወቃት፥ እግዚአብሔርም አሰባት፥


ዳዊትም የዚያ የኤፍራታዊው ሰው ልጅ ነበረ፥ ያም ሰው ከቤተ ልሔም ይሁዳ ስሙም እሴይ ነበረ፥ ስምንትም ልጆች ነበሩት፥ በሳኦልም ዘመን በዕድሜ አርጅቶ ሸምግሎም ነበር።


ሕልቃናም ወደ ቤቱ ወደ አርማቴም ሄደ፥ ብላቴናውም በካሁኑ በዔሊ ፊት እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር።


ቤቱም በዚያ ነበረና ወደ አርማቴም ይመለስ ነበር፥ በዚያም በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር፥ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ።


በተራራማው በኤፍሬም አገርና በሻሊሻ አለፉ፥ አላገኙአቸውምም፥ በሻዕሊም ምድርም አለፉ፥ በዚያም አልነበሩም፥ በብንያም ምድርም አለፉ፥ አላገኙአቸውምም።


ወደ ጹፍ ምድር በመጡ ጊዜም ሳኦል ከእርሱ ጋር የነበረውን ብላቴና፦ አባቴ ስለ አህዮች ማሰብ ትቶ ስለ እኛ እንዳይጨነቅ፥ ና፥ እንመለስ አለው።


跟着我们:

广告


广告