Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ጴጥሮስ 4:19 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ስለዚህ ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራን የሚቀበሉ፥ መልካምን እያደረጉ ነፍሳቸውን ለታመነ ፈጣሪ አደራ ይስጡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ስለዚህ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራ የሚቀበሉ ሁሉ ነፍሳቸውን ለታመነ ፈጣሪ ዐደራ ሰጥተው መልካም ማድረጋቸውን ይቀጥሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ስለዚህ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራ የሚቀበሉ ነፍሳቸውን ለታመነ ፈጣሪ አደራ ሰጥተው መልካም ማድረጋቸውን ይቀጥሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ስለዚህ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራ የሚቀበሉ ሰዎች ሁለንተናቸውን ለታማኙ ፈጣሪ ዐደራ ሰጥተው መልካም ነገርን ከማድረግ አይቈጠቡ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ስለዚህ ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራን የሚቀበሉ፥ መልካምን እያደረጉ ነፍሳቸውን ለታመነ ፈጣሪ አደራ ይስጡ።

参见章节 复制




1 ጴጥሮስ 4:19
27 交叉引用  

ሄደህ በሱሳ ያሉትን አይሁድ ሁሉ ሰብስብ፥ ለእኔም ጹሙ፥ ሦስት ቀን ሌሊቱንና ቀኑን አትብሉም፥ አትጠጡም፥ እኔና ደንገጥሮቼ ደግሞ እንዲሁ እንጾማለን፥ ምንም እንኳ ያለ ሕግ ቢሆን ወደ ንጉሡ እገባለሁ፥ ብጠፋም እጠፋለሁ።


በፊቱ ቅንነት ተገኝቶብኛልና፥ በአንተም ፊት ደግሞ፥ ንጉሥ ሆይ፥ አልበደልሁምና አምላኬ መልአኩን ልኮ የአንበሶችን አፍ ዘጋ፥ እነርሱም አልጐዱኝም አለው።


ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ፦ አባት ሆይ፥ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ አለ። ይህንም ብሎ ነፍሱን ሰጠ።


እስጢፋኖስም፦ “ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ነፍሴን ተቀበል” ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር።


በበጎ ሥራ በመጽናት ምስጋናንና ክብርን የማይጠፋንም ሕይወት ለሚፈልጉ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸዋል፤


ስለዚህም ምክንያት ይህን መከራ ደግሞ ተቀብዬአለሁ፥ ነገር ግን አላፍርበትም፤ ያመንሁትን አውቃለሁና፥ የሰጠሁትንም አደራ እስከዚያ ቀን ድረስ ሊጠብቅ እንዲችል ተረድቼአለሁ።


በጎ እያደረጋችሁ፥ የማያውቁትን ሞኞች ዝም ታሰኙ ዘንድ እንዲህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና፤


የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲህ ቢሆን፥ ክፉ ስለ ማድረግ ሳይሆን በጎ ስለ ማድረግ መከራን ብትቀበሉ ይሻላችኃልና።


ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ በውኃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ፥ የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኅ ዘመን በቍኦየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም።


跟着我们:

广告


广告