Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 9:11 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ንጉሡ ሰሎሞን በገሊላ ምድር ያሉትን ሃያ ከተሞች ለኪራም ሰጠው። የጢሮስም ንጉሥ ኪራም የሚሻውን ያህል የዝግባና የጥድ እንጨት የሚሻውንም ያህል ወርቅ ሁሉ ለሰሎሞን ሰጥቶት ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ንጉሥ ሰሎሞን በገሊላ የሚገኙትን ሃያ ከተሞች ለጢሮስ ንጉሥ ለኪራም ሰጠው፤ ንጉሡ ይህን ያደረገውም፣ የሚያስፈልገውን ሁሉ ዝግባ፣ ጥድና ወርቅ ኪራም ሰጥቶት ስለ ነበር ነው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለዚህ ሁሉ ሥራ ለሰሎሞን የሚያስፈልገውን የሊባኖስ ዛፍና ዝግባ ከብዙ ወርቅ ጋር ሰጥቶት ነበር፤ ሥራውም ሁሉ ከተፈጸመ በኋላ ሰሎሞን በገሊላ ምድር የሚገኙትን ኻያ ታናናሽ ከተሞችን ለኪራም ሰጠው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለዚህ ሁሉ ሥራ ለሰሎሞን የሚያስፈልገውን የሊባኖስ ዛፍና ዝግባ ከብዙ ወርቅ ጋር ሰጥቶት ነበር፤ ሥራውም ሁሉ ከተፈጸመ በኋላ ሰሎሞን በገሊላ ምድር የሚገኙትን ኻያ ታናናሽ ከተሞች ለኪራም ሰጠው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የጢ​ሮስ ንጉሥ ኪራም በዝ​ግ​ባና በጥድ እን​ጨት፥ በወ​ር​ቅና በሚ​ሻ​ውም ሁሉ ሰሎ​ሞ​ንን ረድ​ቶት ነበር። ያን​ጊ​ዜም ንጉሡ ሰሎ​ሞን በገ​ሊላ ምድር ያሉ​ትን ሃያ ከተ​ሞች ለኪ​ራም ሰጠው።

参见章节 复制




1 ነገሥት 9:11
9 交叉引用  

ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤትና የንጉሡን ቤት ሁለቱን ቤቶች የሠራበት ሃያ ዓመት በተፈጸመ ጊዜ፥


ኪራምም ሰሎሞን የሰጠውን ከተሞች ያይ ዘንድ ከጢሮስ ወጣ፤ ደስም አላሰኙትም።


ኪራምም መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ ለንጉሡ ላከ።


እኛም ከሊባኖስ የምትሻውን ያህል እንጨት እንቈርጣለን፤ በታንኳም አድርገን በባሕር ላይ ወደ አንተ ወደ ኢዮጴ እንሰድዳለን፤ አንተም ወደ ኢየሩሳሌም ታስወስደዋለህ።”


ኪራም ለሰሎሞን የሰጠውን ከተሞች ሰሎሞን ሠራቸው፤ የእስራኤልንም ልጆች አኖረባቸው።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ምርኮኞችን ሁሉ ለኤዶምያስ አሳልፈው ሰጥተዋልና፥ የወንድሞችንም ቃል ኪዳን አላሰቡምና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የጢሮስ ኃጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።


በንፍታሌም ባለው በተራራማው አገር በገሊላ ቃዴስን፥ በኤፍሬምም ባለው በተራራማው አገር ሴኬምን፥ በይሁዳም ባለው በተራራማው አገር ኬብሮን የምትባለውን ቂርያትአርባቅን ለዩ።


跟着我们:

广告


广告