Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 22:5 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ኢዮሣፍጥም የእስራኤልን ንጉሥ “የእግዚአብሔርን ቃል አስቀድመህ ትጠይቅ ዘንድ እለምንሃለሁ፤” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ደግሞም ኢዮሣፍጥ የእስራኤልን ንጉሥ፣ “በመጀመሪያ ግን የእግዚአብሔርን ሐሳብ ጠይቅ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 “ነገር ግን መጀመሪያ የጌታን ፈቃድ ጠይቅ” ሲል መለሰለት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “ነገር ግን መጀመሪያ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ጠይቅ” ሲል መለሰለት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ፥ “ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ ጠይ​ቁ​ልን” አለው።

参见章节 复制




1 ነገሥት 22:5
22 交叉引用  

ኢዮሣፍጥንም “በሬማት ዘገለዓድ እንዋጋ ዘንድ ከእኔ ጋር ትመጣለህን?” አለው። ኢዮሣፍጥም የእስራኤልን ንጉሥ “እኔ እንደ አንተ፥ ሕዝቤም እንደ ሕዝብህ፥ ፈረሶቼም እንደ ፈረሶችህ ናቸው አለው።


የእስራኤልም ንጉሥ ነቢያቶቹን አራት መቶ የሚያህሉትን ሰዎች ሰብስቦ “ወደ ሬማት ዘገለዓድ ለሰልፍ ልሂድን? ወይስ ልቅር?” አላቸው። እነርሱም “እግዚአብሔር በንጉሥ እጅ አሳልፎ ይሰጣታልና ውጣ፤” አሉት።


የእግዚአብሔርም መልአክ ቴስብያዊውን ኤልያስን “ተነሣ፤ የሰማርያን ንጉሥ መልእክተኞች ለመገናኘት ውጣና ‘የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ትጠይቁ ዘንድ የምትሄዱት በእስራኤል ዘንድ አምላክ ስለሌለ ነውን?


ኢዮሣፍጥም “በእርሱ እግዚአብሔርን የምንጠይቅበት የእግዚአብሔር ነቢይ በዚህ አይገኝምን?” አለ። ከእስራኤልም ንጉሥ ባሪያዎች አንዱ “በኤልያስ እጅ ላይ ውሃ ያፈስስ የነበረው የሣፋጥ ልጅ ኤልሳዕ እዚህ አለ፤” ብሎ መለሰ።


እንዲሁ ሳኦል በእግዚአብሔር ላይ ስላደረገው ኀጢአት፥ የእግዚአብሔርንም ቃል ስላልጠበቀ ሞተ።


ይህም የሆነው ንጉሡ ሴዴቅያስ፦ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ይወጋናልና ስለ እኛ፥ እባክህ፥ እግዚአብሔርን ጠይቅ፥ ከእኛም ይመለስ ዘንድ ምናልባት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንደ ተአምራቱ ሁሉ ያደርግ ይሆናል ብሎ የመልክያን ልጅ ጳስኮርንና ካህኑን የመዕሤያን ልጅ ሶፎንያስ ወደ ኤርምያስ በላከ ጊዜ ነው።


የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ ሰዎች ጣዖቶቻቸውን በልባቸው አኑረዋል። የበደላቸውንም መቅሠፍት በፊታቸው አቁመዋል፥ እኔስ ከእነርሱ ልጠየቅን?


በካህኑም በአልዓዛር ፊት ይቁም፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት በኡሪም ፍርድ ይጠይቅለት፤ እርሱ ከእርሱም ጋር የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በቃሉ ይውጡ፥ በቃሉም ይግቡ።


ሰዎቹም ከስንቃቸው ወሰዱ፥ እግዚአብሔርንም አልጠየቁም።


እንዲህም ሆነ፥ ኢያሱ ከሞተ በኋላ የእስራኤል ልጆች፦ ከነዓናውያንን ለመውጋት ማን በፊት ይወጣልናል? ብለው እግዚአብሔርን ጠየቁ።


የእስራኤልም ልጆች ተነሥተው ወደ ቤቴል ወጡ፥ እግዚአብሔርንም፦ የብንያምን ልጆች ለመውጋት አስቀድሞ ማን ይውጣልን? ብለው ጠየቁት፥ እግዚአብሔርም፦ ይሁዳ ይቅደም አለ።


የእስራኤልም ልጆች ወጥተው በእግዚአብሔር ፊት እስከ ማታ ድረስ አለቀሱ፥ እግዚአብሔርንም፦ ከወንድሞቻችን ከብንያም ልጆች ጋር ለመዋጋት ዳግመኛ እንቀርባለን? ብለው ጠየቁ። እግዚአብሔርም፦ በእነርሱ ላይ ውጡ አለ።


እስራኤልም በጊብዓ ዙሪያ የተደበቁ ሰዎች አኖሩባት።


በዚያም ቀን አኪያ በእስራኤል ልጆች ፊት ኤፉድ ለብሶ ነበርና ሳኦል፦ ኤፉድን አምጣ አለው።


ዳዊትም፦ ልሂድን? እነዚህንስ ፍልስጥኤማውያን ልምታን? ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ፥ እግዚአብሔርም ዳዊትን፦ ሂድ፥ ፍልስጥኤማውያንን ምታ ቅዒላንም አድን አለው።


ዳዊትም ደግሞ እግዚአብሔርን ጠየቀ፥ እግዚአብሔርም መልሶ፦ ፍልስጥኤማውያንን በእጅህ አሳልፌ እሰጣለሁና ተነሥተህ ወደ ቅዒላ ውረድ አለው።


ዳዊትም፦ የእነዚህን ሠራዊት ፍለጋ ልከተልን? አገኛቸዋለሁን? ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ፥ እርሱም፦ ታገኛቸዋለህና፥ ፈጽመህም ምርኮውን ትመልሳለህና ፍለጋቸውን ተከተል ብሎ መለሰለት።


跟着我们:

广告


广告