Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 22:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 የእስራኤልም ንጉሥ ባሪያዎቹን “ሬማት ዘገለዓድ የእኛ እንደ ሆነች፥ እኛም ከሶርያ ንጉሥ እጅ ሳንወስዳት ዝም እንዳልን ታውቃላችሁን?” አላቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የእስራኤልም ንጉሥ ሹማምቱን፣ “በገለዓድ የምትገኘው ራሞት የእኛ ሆና ሳለች፣ ከሶርያው ንጉሥ እጅ ለመመለስ ምንም እንዳላደረግን አታውቁምን?” አላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 አክዓብ ባለሟሎቹ የሆኑትን ባለ ሥልጣኖች “በገለዓድ የምትገኘውን ራሞትን ከሶርያ ንጉሥ ለማስመለስ ምንም ዓይነት እርምጃ ያልወሰድነው ስለምንድን ነው? ራሞት እኮ የእኛ ይዞታ ናት!” አላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 አክዓብ ባለሟሎቹ የሆኑትን ባለሥልጣኖች “በገለዓድ የምትገኘውን ራሞትን ከሶርያ ንጉሥ ለማስመለስ ምንም ዐይነት እርምጃ ያልወሰድነው ስለምንድን ነው? ራሞት እኮ የእኛ ይዞታ ናት!” አላቸው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን፥ “ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ የእኛ እንደ ሆነች፥ እኛም ከሶ​ርያ ንጉሥ እጅ ሳን​ወ​ስ​ዳት ዝም እን​ዳ​ልን ታው​ቃ​ላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው።

参见章节 复制




1 ነገሥት 22:3
10 交叉引用  

በላያችን እንዲሆን የቀባነው አቤሴሎም በሰልፍ ሞቶአል፥ አሁንም እንግዲህ ንጉሡን ለመመለስ ስለ ምን ዝም ትላላችሁ? እያለ እርስ በርሱ ይከራከር ነበር።


የእስራኤልም ንጉሥና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ወደ ሬማት ዘገለዓድ ወጡ።


በሬማት ዘገለዓድ የጌበር ልጅ ነበረ፤ ለእርሱም በገለዓድ ያሉት የምናሴ ልጅ የኢያዕር መንደሮች ነበሩ፤ ለእርሱም ደግሞ በባሳን በአርጎብ ዳርቻ ያሉት ቅጥርና የናስ መወርወሪያዎች የነበረባቸው ስድሳ ታላላቅ ከተሞች ነበሩበት፤


ከአክዓብም ልጅ ከኢዮራም ጋር የሶርያን ንጉሥ አዛሄልን በሬማት ዘገልዓድ ሊጋጠም ሄደ፤ ሶርያውያንም ኢዮራምን አቈሰሉት።


እንዲሁም የናሜሲ ልጅ የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዩ በኢዮራም ላይ ተማማለ። ኢዮራምና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ከሶርያ ንጉሥ ከአዛሄል የተነሣ ሬማት ዘገለዓድን ይጠብቁ ነበር።


ከተሞቹም ለሮቤል ነገድ በምድረ በዳ በደልዳላ ስፍራ ያለ ቦሶር፥ ለጋድም ነገድ በገለዓድ ያለ ራሞት፥ ለምናሴም ነገድ በባሳን ያለ ጎላን ነበሩ።


በዮርዳኖስም ማዶ ከኢያሪኮ ወደ ምሥራቅ ከሮቤል ነገድ በምድረ በዳው በደልዳላው ስፍራ ቦሶርን፥ ከጋድም ነገድ በገለዓድ ራሞትን፥ ከምናሴም ነገድ በባሳን ጎላንን ለዩ።


ከጋድም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገለዓድ ውስጥ ራሞትንና መሰምርያዋን፥ መሃናይምንና መሰምርያዋን፥


የጋዛ ሰዎችም ሶምሶን ወደ ከተማ ውስጥ እንደ ገባ ሰሙ፥ ከበቡትም፥ ሌሊቱንም ሁሉ በከተማይቱ በር ሸመቁበት፦ ማለዳ እንገድለዋለን ብለውም ሌሊቱን ሁሉ በዝምታ ተቀመጡ።


እነርሱም፦ ምድሪቱ እጅግ መልካም እንደ ሆነች አይተናልና ተነሡ፥ በእነርሱ ላይ እንውጣ፥ እናንተ ዝም ትላላችሁን? ትሄዱ ዘንድ ምድሪቱንም ለመውረስ ትገቡ ዘንድ ቸል አትበሉ።


跟着我们:

广告


广告