Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 21:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 የእስራኤል ንጉሥ መልሶ፦ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ አንተ እንዳልህ ነው፤ እኔ ለእኔም የሆነው ሁሉ የአንተ ነው አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ኢይዝራኤላዊው ናቡቴ፣ “ዐፅመ ርስቴን አልለቅልህም” ስላለው፣ አክዓብ ተበሳጭቶና ተቈጥቶ ወደ ቤቱ ገባ፤ አኵርፎም በዐልጋው ላይ ተኛ፤ ምግብም መብላት ተወ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የእስራኤልም ንጉሥ መልሶ፦ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ አንተ እንዳልህ ነው፥ እኔ ለእኔም የሆነው ሁሉ የአንተ ነው” አለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 አክዓብ፥ የእዝራኤላዊው ናቡቴ “ከአባቶቼ የወረስኩትን ለአንተ አልሰጥህም!” ስላለው በንዴት እየተበሳጨ ወደ ቤቱ ገባ፤ ፊቱንም ወደ ግድግዳ አዙሮ በአልጋው ላይ ተጋደመ፤ ምግብ መብላትም አልፈቀደም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ንጉሡ አክ​ዓ​ብም መልሶ፥ “ጌታዬ ሆይ! አንተ እን​ዳ​ልህ፤ እኔ የአ​ንተ ነኝ፤ ለእ​ኔም የሆ​ነው ሁሉ የአ​ንተ ነው” አለ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 21:4
21 交叉引用  

አምኖንም ከእኅቱ ከትዕማር የተነሣ እጅግ ስለ ተከዘ ታመመ፥ ድንግልም ነበረችና አንዳች ያደርጋት ዘንድ በዓይኑ ፊት ጭንቅ ሆኖበት ነበር።


እርሱም፦ የንጉሥ ልጅ ሆይ፥ ስለ ምን ቀን በቀን እንዲህ ከሳህ? አትነግረኝምን? አለው። አምኖንም፦ የወንድሜን የአቤሴሎምን እኅት ትዕማርን እወድዳታለሁ አለው።


የሶርያም ንጉሥ ወልደ አዴር ጭፍራውን ሁሉ ሰበሰበ፤ ከእርሱም ጋር ሠላሳ ሁለት ነገሥት ነበሩ፥ ፈረሶችና ሰረገሎችም ነበሩ፤ ወጥቶም ሰማርያን ከበበ፥ ወጋትም።


ወልደ አዴር እንዲህ ይላል፦ ብርህና ወርቅህ ለእኔ ነው፤ ሴቶችህና መልካካሞቹም ልጆችህ ለእኔ ናቸው ብሎ ወደ ከተማይቱ መልእክተኞችን ላከ።


ደግሞም መልእክተኞች ተመልሰው፦ ወልደ አዴር እንዲህ ይላል፦ ቀድሞ ብርህንና ወርቅህን ሴቶችህንና ልጆችህንም ትሰጠኛለህ ብዬ ልኬብህ ነበር፤


ነገር ግን አይሁዳዊው መርዶክዮስ በንጉሡ በር ተቀምጦ ካየሁ ይህ ሁሉ ለእኔ ምንምን አይጠቅምም አለ።


ሰነፉን ሰው ቍጣ ይገድለዋል፥ ሰነፉንም ቅንዓት ያጠፋዋል።


በዓይን ማየት በነፍስ ከመቅበዝበዝ ይሻላል፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።


በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፥ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት።


ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል።


እርሱ ግን፦ አልበላም ብሎ እንቢ አለ፥ ነገር ግን ባሪያዎቹና ሴቲቱ አስገደዱት፥ ቃላቸውንም ሰማ ከምድርም ተነሥቶ በአልጋ ላይ ተቀመጠ።


跟着我们:

广告


广告