Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 20:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ኢይዝራኤላዊውም ናቡቴ “የአባቶቼን ርስት አልሰጥህም፤” ብሎ ስለ ተናገረው አክዓብ ተቆጥቶና ተናድዶ ወደ ቤቱ ገባ። በአልጋውም ላይ ተጋድሞ ፊቱን ተሸፋፈነ፤ እንጀራም አልበላም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 የእስራኤልም ንጉሥ፣ “ንጉሥ ጌታዬ ሆይ፤ ልክ እንዳልኸው ነው፤ እኔም ሆንሁ የእኔ የሆነው ሁሉ የአንተ ነው” ሲል መለሰለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 አክዓብም “ለጌታዬ ለንጉሥ ቤንሀዳድ አንተ ባልከው እስማማለሁ፤ እኔና የእኔ የሆነ ሁሉ የአንተ ነው።” አለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 አክዓብም “ለጌታዬ ለንጉሥ ቤንሀዳድ አንተ ባልከው እስማማለሁ፤ እኔና የእኔ የሆነ ሁሉ የአንተ ነው።” አለ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 አክ​ዓ​ብም አዝኖ ሄደ፤ በአ​ል​ጋ​ውም ላይ ተኝቶ ፊቱን ተሸ​ፋ​ፈነ፤ እን​ጀ​ራ​ንም አል​በ​ላም።

参见章节 复制




1 ነገሥት 20:4
10 交叉引用  

ሳሚም ንጉሡን “ነገሩ መልካም ነው፤ ጌታዬ ንጉሥ እንደ ተናገረ ባሪያህ እንዲሁ ያደርጋል፤” አለው፤ ሳሚም በኢየሩሳሌም ብዙ ቀን ተቀመጠ።


ናቡቴም አክዓብን “የአባቶቼን ርስት እሰጥህ ዘንድ እግዚአብሔር ያርቅልኝ፤” አለው።


ሚስቱም ኤልዛቤል ወደ እርሱ መጥታ “ልብህ የሚያዝን እንጀራስ የማትበላ ስለምንድር ነው?” አለችው።


የቤቱ አለቃ፥ የከተማይቱም አለቃ፥ ሽማግሌዎችና ልጆቹን የሚያሳድጉ “እኛ ባሪያዎችህ ነን፤ ያዘዝኸንንም ሁሉ እናደርጋለን፤ ንጉሥም በላያችን አናነግሥም፤ የምትወድደውን አድርግ፤” ብለው ወደ ኢዩ ላኩ።


በጠላቶቻቸውም ምድሮች ሳሉ ከእናንተ ተለይተው በቀሩት ላይ በልባቸው ድንጋጤን እሰድድባቸዋለሁ፤ በነፋስም የምትንቀሳቀስ የቅጠል ድምፅ ታሸብራቸዋለች፤ ከሰይፍ እንደሚሸሹ ይሸሻሉ፤ ማንም ሳያሳድዳቸው ይወድቃሉ።


በራብና በጥማት በዕራቁትነትም ሁሉንም በማጣት እግዚአብሔር ለሚልክብህ ለጠላቶችህ ትገዛለህ፤ እስኪያጠፋህም ድረስ በአንገትህ ላይ የብረት ቀንበር ይጭናል።


የአያቢስም ሰዎች፦ ነገ እንወጣላችኋለን፥ ደስ የሚያሰኛችሁንም አድርጉብን አሉ።


跟着我们:

广告


广告