Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 2:5 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 አንተም ደግሞ የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ! ሁለቱን የእስራኤልን ጭፍራ አለቆች የኔር ልጅ አበኔርን የዬቴሩንም ልጅ አሜሳይን ገድሎ፥ በእኔ ላይ ያደረገውን ታውቃለህ፤ የሰልፉንም ደም በሰላም አፈሰሰ፤ በወገቡም ባለው ድግና በእግሩ ባለው ጫማ ንጹሕ ደም አኖረ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 “የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ በእኔ ላይ ያደረገውን፣ እንዲሁም በእስራኤል ሰራዊት አዛዦች በኔር ልጅ በአበኔርና በዬቴር ልጅ በአሜሳይ ላይ የፈጸመውን አንተው ራስህ ታውቃለህ፤ ጦርነት ሳይኖር በሰላሙ ጊዜ ደማቸውን አፍስሷል፤ በዚህም ደም ወገቡ ላይ የታጠቀውን ቀበቶና በእግሩ ላይ ያደረገውን ጫማ በክሏል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 “የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ የእስራኤል ሕዝብ የጦር መሪዎች ከነበሩት በኔር ልጅ አበኔርና በይቴር ልጅ ዐማሣ ላይ ያደረገውን ታስታውሳለህ፤ ሁለት በጦርነት ጊዜ ላፈሰሱት ደም በቀል በሰላም ጊዜ እነርሱን ገድሎ የወገቡን መታጠቂያ የእግሩን ጫማ በደም በክሎ በእኔ ላይ ምን እንዳደረገ ታውቃለህ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ የእስራኤል ሕዝብ የጦር መሪዎች ከነበሩት በኔር ልጅ አበኔርና በይቴር ልጅ ዐማሣ ላይ ያደረገውን ታስታውሳለህ፤ ሁለት በጦርነት ጊዜ ላፈሰሱት ደም በቀል በሰላም ጊዜ እነርሱን ገድሎ የወገቡን ድግና የእግሩን ጫማ በደም በክሎ በእኔ ላይ ምን እንዳደረገ ታውቃለህ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 አን​ተም ደግሞ የሶ​ር​ህያ ልጅ ኢዮ​አብ፥ ሁለ​ቱን የእ​ስ​ራ​ኤል ሠራ​ዊት አለ​ቆች የኔር ልጅ አበ​ኔ​ርን የኢ​ያ​ቴ​ር​ንም ልጅ አሜ​ሳ​ይን ገድሎ፥ በእኔ ላይ ያደ​ረ​ገ​ውን ታው​ቃ​ለህ፤ የጦ​ር​ነ​ት​ንም ደም በሰ​ላም አፈ​ሰሰ፤ በወ​ገ​ቡም ባለው ድግና በእ​ግ​ሩም ባለው ጫማ ንጹሕ ደም አኖረ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 2:5
18 交叉引用  

አቤሴሎምም በጭፍራው ላይ በኢዮአብ ስፍራ አሜሳይን ሾመ፥ አሜሳይም የይስማኤላዊ ሰው የዬቴር ልጅ ነበረ፥ እርሱም የኢዮአብን እናት የጽሩያን እኅት የናዖስን ልጅ አቢግያን አግብቶ ነበር።


ሰውዮውም ኢዮአብን፦ እኛ ስንሰማ ንጉሡ አንተንና አቢሳን ኢታይንም፦ ብላቴናውን አቤሴሎምን ማንም እንዳይነካው ተጠንቀቁ ብሎ አዝዞአልና ሺህ ብር በእጄ ላይ ብትመዝን እጄን በንጉሡ ልጅ ላይ ባልዘረጋሁም ነበር አለው።


ኢዮአብም፦ እኔ ከአንተ ጋር እንዲህ እዘገይ ዘንድ አልችልም ብሎ ሦስት ጦሮች በእጁ ወሰደ፥ አቤሴሎምም ገና በዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ ሕያው ሳለ በልቡ ላይ ተከላቸው።


ንጉሡም ኢዮአብንና አቢሳን ኢታይንም፦ ለብላቴናው ለአቤሴሎም ስለ እኔ ራሩለት ብሎ አዘዛቸው። ንጉሡም ስለ አቤሴሎም አለቆቹን ሁሉ ሲያዝዝ ሕዝቡ ሁሉ ሰማ።


የጽሩያ ልጅ ኢዮአብና የዳዊት ባሪያዎች ወጥተው በገባዖን ውኃ መቆሚያ አጠገብ ተገናኙአቸው፥ በውኃውም መቆሚያ በአንዱ ወገን እነዚህ፥ በሌላውም ወገን እነዚያ ሆነው ተቀመጡ።


በዚያም ሦስቱ የጽሩያ ልጆች ኢዮአብና አቢሳ አሣሄልም ነበሩ፥ አሣሄልም እንደ ዱር ሚዳቋ በሩጫ ፈጣን ነበረ።


አሜሳይ ግን በኢዮአብ እጅ ከነበረው ሰይፍ አልተጠነቀቀም ነበር፥ ኢዮአብም ሆዱን ወጋው፥ አንጀቱንም በምድር ላይ ዘረገፈው፥ ሁለተኛም አልወጋውም፥ ሞተም።


አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ ኢዮአብ በበር ውስጥ በቆይታ ይናገረው ዘንድ ወደ አጠገቡ ወሰደው፥ በዚያም ለወንድሙ ለአሣሄል ደም ተበቅሎ ሆዱን መታው፥ ሞተም።


እኔም ዛሬ ምንም ለመንገሥ የተቀባሁ ብሆን ደካማ ነኝ፥ እነዚህም ሰዎች የጽሩያም ልጆች በርትተውብኛል፥ እግዚአብሔር ክፋት በሠራ ላይ እንደ ክፋቱ ይመልስበት አላቸው።


ሴራውም ከጽሩያ ልጅ ከኢዮአብና ከካህኑ ከአብያታር ጋር ነበረ፤ እነርሱም አዶንያስን ተከትለው ይረዱት ነበር።


አባቴ ዳዊት ሳያውቅ ከእርሱ የሚሻሉትን ሁለቱን ጻድቃን ሰዎች፥ የእስራኤልን ሠራዊት አለቃ የኔርን ልጅ አበኔርን፥ የይሁዳንም ሠራዊት አለቃ የዬቴርን ልጅ አሜሳይን፥ በሰይፍ ገድሎአልና እግዚአብሔር ደሙን በራሱ ላይ ይመልሰው።


በእጆችሽም የንጹሐን ድሆች ደም ተገኝቶአል፥ በእነዚህ ሁሉ ላይ በግልጥ አገኘሁት እንጂ በስውር ፈልጌ አላገኘሁትም።


ርኩስን ነገር ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፥ እፍረትንም አላወቁም፥ ስለዚህ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ፥ በጐበኘኋቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።


ራሱም ዮሐንስ የግመል ጠጉር ልብስ ነበረው፥ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ ምግቡም አንበጣና የበረሀ ማር ነበረ።


ባልንጀራውን በስውር የሚመታ ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።


跟着我们:

广告


广告