Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 2:25 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ንጉሡም ሰሎሞን የዮዳሄን ልጅ በናያስን ላከ፤ እርሱም ወደቀበት፤ ሞተም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ስለዚህም አዶንያስን እንዲገድለው ንጉሥ ሰሎሞን፣ የዮዳሄን ልጅ በናያስን አዘዘው፤ በናያስም አዶንያስን መትቶ ገደለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ስለዚህም አዶንያስን እንዲገድለው ንጉሥ ሰሎሞን ለዮዳሄ ልጅ ለበናያ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ በናያም ሄዶ አዶንያስን ገደለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ስለዚህም አዶንያስን እንዲገድለው ንጉሥ ሰሎሞን ለዮዳሄ ልጅ ለበናያ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ በናያም ሄዶ አዶንያስን ገደለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን የዮ​ዳ​ሄን ልጅ በና​ያ​ስን ላከ፤ እር​ሱም አረ​ደው፤ ያን​ጊ​ዜም አዶ​ን​ያስ ሞተ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 2:25
11 交叉引用  

ዳዊትም ከጕልማሶቹ አንዱን ጠርቶ፦ ወደ እርሱ ቅረብና ውደቅበት አለው። እርሱም መታው፥ ሞተም።


ስለዚህም አቃልለኽኛልና፥ የኬጢያዊውንም የኦርዮን ሚስት ለአንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስደሃልና ለዘላለም ከቤትህ ሰይፍ አይርቅም።


ዳዊትም ጕልማሶቹን አዘዘ፥ ገደሉአቸውም፥ እጃቸውንና እግራቸውን ቆርጠው በኬብሮን በውኃ መቆሚያ አጠገብ አንጠለጠሉአቸው። የኢያቡስቴንም ራስ ወስደው በአበኔር መቃብር በኬብሮን ቀበሩት።


የዮዳሄ ልጅ በናያስ በከሊታውያንና በፈሊታውያን ላይ ነበረ፥ የዳዊትም ልጆች አማካሪዎች ነበሩ።


ንጉሡም ሰሎሞን ኢዮአብ ወደ እግዚአብሔር ድንኳን ሸሽቶ መሠዊያውን እንደ ያዘ ሰማ፤ ሰሎሞንም የዮዳሄን ልጅ በናያስን “ሂድ፤ ውደቅበት፤” ብሎ አዘዘው።


ንጉሡም አለው “እንደ ነገረህ አድርግ፤ ኢዮአብም በከንቱ ያፈሰሰውን ደም ከእኔና ከአባቴ ቤት ታርቅ ዘንድ ገድለህ ቅበረው።


የዮዳሄም ልጅ በናያስ ወጥቶ ወደቀበት፤ ገደለውም፤ በምድረ በዳም ባለው በቤቱ ተቀበረ።


ንጉሡም የዮዳሄን ልጅ በናያስን አዘዘው፤ ወጥቶም ወደቀበት፤ ሞተም። መንግሥትም በሰሎሞን እጅ ጸና።


እነርሱም፦ አስረን በፍልስጥኤማውያን እጅ አሳልፈን ልንሰጥህ መጥተናል አሉት። ሶምሶንም፦ እናንተ እንዳትገሉኝ ማሉልኝ አላቸው።


ሳሙኤልም፦ ሰይፍህ ሴቶችን ልጆች አልባ እንዳደረገቻቸው እንዲሁ እናትህ በሴቶች መካከል ልጅ አልባ ትሆናለች አለ፥ ሳሙኤልም አጋግን በእግዚአብሔር ፊት በጌልገላ ቆራረጠው።


跟着我们:

广告


广告