Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 2:22 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ንጉሡም ሰሎሞን ለእናቱ መልሶ “ሱነማይቱን አቢሳን ለአዶንያስ ለምን ትለምኝለታለሽ? ታላቅ ወንድሜ ነውና መንግሥትን ደግሞ ለምኚለት፤ ካህኑም አብያታርና የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ ደግሞ ከእርሱ ጋር ናቸው፤” አላት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ንጉሥ ሰሎሞንም እናቱን፣ “ስለ ምን ሱነማዪቱን አቢሳን ብቻ ለአዶንያስ ትጠይቂለታለሽ? ታላቅ ወንድሜ ስለ ሆነ መንግሥቱንም ጠይቂለት እንጂ፤ ለርሱ ብቻ ሳይሆን እንዲሁም ለካህኑ ለአብያታርና ለጽሩያ ልጅ ለኢዮአብ ጠይቂላቸው” አላት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ንጉሡም “አቢሻግን በሚስትነት እንድድርለት ብቻ ለምን ትጠይቂኛለሽ? መንግሥቴንም ጭምር እንድለቅለት ለምን አልጠየቅሽኝም? እርሱ እኮ ታላቅ ወንድሜ ነው፤ ለምን ለካህኑ አብያታርና ለኢዮአብም ልዩ አስተያየት እንዳደርግላቸው አትጠይቂላቸውም!” አላት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ንጉሡም “አቢሻግን በሚስትነት እንድድርለት ብቻ ለምን ትጠይቂኛለሽ? መንግሥቴንም ጭምር እንድለቅለት ለምን አልጠየቅሽኝም? እርሱ እኮ ታላቅ ወንድሜ ነው፤ ለምን ለካህኑ አብያታርና ለኢዮአብም ልዩ አስተያየት እንዳደርግላቸው አትጠይቂላቸውም!” አላት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን ለእ​ናቱ መልሶ፥ “ሱነ​ማ​ዪ​ቱን አቢ​ሳን ለአ​ዶ​ን​ያስ ለምን ትለ​ም​ኚ​ለ​ታ​ለሽ? ታላቅ ወን​ድሜ ነውና መን​ግ​ሥ​ትን ደግሞ ለም​ኚ​ለት፤ ካህ​ኑም አብ​ያ​ታ​ርና የሶ​ር​ህያ ልጅ የጭ​ፍ​ሮች አለቃ ኢዮ​አብ ደግሞ ከእ​ርሱ ጋር ናቸው” አላት።

参见章节 复制




1 ነገሥት 2:22
11 交叉引用  

የጌታህን ቤት ሰጠሁህ፥ የጌታህንም ሚስቶች በብብትህ ጣልሁልህ፥ የእስራኤልንና የይሁዳን ቤት ሰጠሁህ ይህም አንሶ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የበለጠ እጨምርልህ ነበር።


አኪጦፌልም አቤሴሎምን፦ ቤት ሊጠብቁ ወደ ተዋቸው ወደ አባትህ ቁባቶች ግባ፥ እስራኤልም ሁሉ አባትህን እንዳሳፈረኸው ይሰማሉ፥ ከአንተም ጋር ያሉት ሁሉ እጃቸው ይበረታል አለው።


ናታንም የሰሎሞንን እናት ቤርሳቤህን እንዲህ ብሎ ተናገራት “ጌታችን ዳዊት ሳያውቅ የአጊት ልጅ አዶንያስ እንደ ነገሠ አልሰማሽምን?


እርሱም “መንግሥቱ ለእኔ እንደ ነበረ፥ እስራኤልም ሁሉ ንጉሥ እሆን ዘንድ ፊታቸውን ወደ እኔ አድርገው እንደ ነበረ አንቺ ታውቂያለሽ፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆኖለታልና መንግሥቱ ከእኔ አልፎ ለወንድሜ ሆኖአል።


ሦስተኛው አቤሴሎም ከጌሹር ንጉሥ ከተልማይ ልጅ ከመዓካ፥ አራተኛው አዶንያስ ከአጊት፥


እነዚህ ደግሞ በኢየሩሳሌም ተወለዱለት፤ ከዓሚኤል ልጅ ከቤርሳቤህ፥ ሳሙስ፥ ሶባብ፥ ናታን፥ ሰሎሞን፥ አራት።


ኢየሱስ ግን መልሶ፦ የምትለምኑትን አታውቁም። እኔ ልጠጣው ያለውን ጽዋ ልትጠጡ እኔም የምጠመቀውን ጥምቀት ልትጠመቁ ትችላላችሁን? አለ። እንችላለን አሉት።


ኢየሱስ ግን፦ የምትለምኑትን አታውቁም። እኔ የምጠጣውን ጽዋ ልትጠጡ፥ እኔ የምጠመቀውንስ ጥምቀት ልትጠመቁ ትችላላችሁን? አላቸው።


ትለምናላችሁ፥ በምቾቶቻችሁም ትከፍሉ ዘንድ በክፉ ትለምናላችሁና አትቀበሉም።


跟着我们:

广告


广告