Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 17:6 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ቍራዎችም በየጥዋትና በየማታው እንጀራና ሥጋ ያመጡለት ነበር፤ ከወንዙም ይጠጣ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ቍራዎችም ጧትና ማታ እንጀራና ሥጋ ያመጡለት ነበር፤ ውሃም ከወንዙ ይጠጣ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ከወንዙም ውሃ ጠጣ፤ ቁራዎችም ዘወትር ጧትና ማታ እንጀራና ሥጋ ያመጡለት ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ከወንዙም ውሃ ጠጣ፤ ቊራዎችም ዘወትር ጧትና ማታ እንጀራና ሥጋ ያመጡለት ነበር፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ቁራ​ዎ​ችም በየ​ጥ​ዋ​ቱና በየ​ማ​ታው እን​ጀ​ራና ሥጋ ያመ​ጡ​ለት ነበር፤ ከፈ​ፋ​ውም ይጠጣ ነበር።

参见章节 复制




1 ነገሥት 17:6
25 交叉引用  

ሄደም፤ ሬሳውም በመንገድ ወድቆ፥ በሬሳውም አጠገብ አህያውና አንበሳው ቆመው፥ አንበሳው ሬሳውን ሳይበላው አህያውንም ሳይሰብረው አገኘ።


ሄደም፤ እንደ እግዚአብሔር ቃልም አደረገ። ሄዶም በዮርዳኖስ ትይዩ ባለው በኮራት ፈፋ ውስጥ ተቀመጠ።


ከብዙ ቀንም በኋላ በምድር ላይ ዝናብ አልነበረምና ወንዙ ደረቀ።


ሲመለከትም፥ እነሆ፥ በራሱ አጠገብ የተጋገረ እንጎቻና በማሰሮ ውሃ አገኘ። በላም፤ ጠጣም፤ ተመልሶም ተኛ።


ተነሥቶም በላ፤ ጠጣም፤ በዚያም ምግብ ኀይል እስከ እግዚአብሔር ተራራ እስከ ኮሬብ ድረስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሄደ።


የእስራኤልም ልጆች ወደሚኖሩባት ምድር እስኪመጡ ድረስ አርባ ዓመት መና በሉ፤ ወደ ከነዓን ምድር ድንበር እስኪመጡ ድረስ መና በሉ።


እርሱ ከፍ ባለ ሥፍራ ይቀመጣል፥ ጠንካራ አምባ መጠጊያው ይሆናል፥ እንጀራም ይሰጠዋል፥ ውኃውም የታመነች ትሆናለች።


ንጉሡም ሴዴቅያስ አዘዘ፥ ኤርምያስንም በግዞት ቤት አደባባይ አኖሩት፥ እንጀራም ሁሉ ከከተማ እስኪጠፋ ድረስ ዕለት ዕለት አንድ አንድ እንጀራ ከጋጋሪዎች መንገድ ይሰጡት ነበር። እንዲሁም ኤርምያስ በግዞት ቤት አደባባይ ተቀምጦ ነበር።


አሁንም፥ እነሆ፥ በእጅህ ካለችው ሰንሰለት ዛሬ ፈታሁህ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ቢታይህ፥ ና፥ እኔም በመልካም አይሃለሁ፥ ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ባይታይህ ግን፥ ተቀመጥ፥ እነሆ፥ አገሪቱ ሁሉ በፊትህ ናት፥ ትሄድ ዘንድ መልካም መስሎ ወደሚታይህ ደስ ወደሚያሰኝህም ስፍራ ሂድ።


እግዚአብሔርም ሙሴን፦ በውኑ የእግዚአብሔር እጅ አጭር ሆነ? አሁን ቃሌ ይፈጸም ወይስ አይፈጸም እንደ ሆነ አንተ ታያለህ አለው።


ኢየሱስም እነርሱን ተመልክቶ፦ ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል አላቸው።


ደግሞም፦ ያለ ኮረጆና ያለ ከረጢት ያለ ጫማም በላክኋችሁ ጊዜ፥ አንዳች ጐደለባችሁን? አላቸው። እነርሱም፦ አንዳች እንኳ አሉ።


እርሱም፦ ከበላተኛው ውስጥ መብል ወጣ፥ ከብርቱም ውስጥ ጥፍጥ ወጣ አላቸው። ሦስት ቀንም እንቈቅልሹን መተርጎም አልቻሉም።


跟着我们:

广告


广告