Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 16:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የእኩሌቶቹም ሠረገሎች አለቃ ዘምሪ ተማማለበት፤ ኤላም በቴርሳ ነበረ፤ በቴርሳም በነበረው በቤት አሽከሮች አለቃ በአሳ ቤት ይሰክር ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከሹማምቱ አንዱና የግማሽ ሠረገሎቹ አዛዥ የሆነው ዘምሪ ዐምፆ ተነሣበት፤ በዚያ ጊዜ ኤላ በቴርሳ ከተማ የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ በሆነው በአርጻ ቤት ጠጥቶ ሰክሮ ነበር፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 የሠረገላዎቹ እኩሌታ ኀላፊ የሆነ ዚምሪ ተብሎ የሚጠራ ከጦር መኰንኖቹ አንዱ በንጉሡ ላይ ዐደመ፤ አንድ ቀን ኤላ በቲርጻ ከተማ የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ በሆነው አርጻ ተብሎ በሚጠራው ባለሟሉ ቤት ብዙ መጠጥ ጠጥቶ ሰክሮ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 የሠረገላዎቹ እኩሌታ ኀላፊ የሆነ ዚምሪ ተብሎ የሚጠራ ከጦር መኰንኖቹ አንዱ በንጉሡ ላይ ዐደመ፤ አንድ ቀን ኤላ በቲርጻ ከተማ የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ በሆነው አርጻ ተብሎ በሚጠራው ባለሟሉ ቤት ብዙ መጠጥ ጠጥቶ ሰክሮ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የእ​ኩ​ሌ​ቶቹ ፈረ​ሶች አለቃ ዘም​ሪም አሽ​ከ​ሮ​ቹን ሁሉ ሰብ​ስቦ ዐመፀ፤ ኤላም በቴ​ርሳ ነበረ፤ በቴ​ር​ሳም በነ​በ​ረው በመ​ጋ​ቢው በአሳ ቤት ይሰ​ክር ነበር።

参见章节 复制




1 ነገሥት 16:9
28 交叉引用  

አብራምም፤ አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፥ ምንን ትሰጠኛለህ? እኔም ያለ ልጅ እሄዳለሁ፤ የቤቴም መጋቢ የደማስቆ ሰው ይህ ኤሊዔዘር ነው አለ።


ሎሌውም ከጌታው ግመሎች መካከል አሥር ግመሎችን ወስዶ ከጌትውም ዕቅ መልካም መልካሙን ይዞ ተነሣ፤ ተነሥቶም ወደ መስዼጦምይ ወደ ናኮር ከተማ ሄደ።


አብርሃምም ሎሌውን የቤቱን ሽማግሌ የከብቱን ሁሉ አዛዥ አለው፦


ዮሴፍም በጌታው ፊት ሞገስን አገኘ እርሱንም ያገለግለው ነበር በቤቱም ላይ ሾመው ያለውንም ሁሉ በእጁ ሰጠው።


ለዚህ ቤት ከእኔ የሚበልጥ ሰው የለም፤ ሚስቱ ስለ ሆንሽ ከአንቺም በቀር ያልሰጠኝ ነገር የለም፤ እንዴት ይህን ትልቅ ክፋ ነገር አደርጋለሁ? በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ኃጢአትን እሠራለሁ?


ከይሳኮርም ቤት የሆነ የአኪያ ልጅ ባኦስ ተማማለበት፤ ናዳብና እስራኤልም ሁሉ ገባቶንን ከብበው ነበርና ባኦስ በፍልስጥኤም አገር ባለው በገባቶን ገደለው።


በይሁዳም ንጉሥ በአሳ በኻያ ሰባተኛው ዓመት ዘምሪ ገብቶ መታው፤ ገደለውም፤ በፋንታውም ነገሠ።


በይሁዳም ንጉሥ በአሳ በኻያ ስድስተኛው ዓመት የባኦስ ልጅ ኤላ በእስራኤል ላይ በቴርሳ ሁለት ዓመት ነገሠ።


አክዓብም የቤቱን አዛዥ አብድዩን ጠራ፤ አብድዩ እግዚአብሔርን እጅግ ይፈራ ነበር።


የጾም አዋጅ ነገሩ፤ ናቡቴንም በሕዝቡ ፊት አስቀመጡት።


አክዓብም ናቡቴ እንደ ሞተ በሰማ ጊዜ ይወርሰው ዘንድ ወደ ኢይዝራኤላዊው ወደ ናቡቴ ወይን ቦታ ሊወርድ ተነሣ።


የቀረውም የኢዮአስ ነገር፥ የሠራውም ሥራ ሁሉ፥ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?


የኢያቤስም ልጅ ሰሎም ተማማለበት፤ በይብልዓም መትቶ ገደለው፤ በእርሱም ፋንታ ነገሠ።


የሠራዊቱም አለቃ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ተማማለበት፤ በሰማርያም በንጉሡ ቤት ግንብ ውስጥ ከአርጎብና ከአርያ ጋር መታው፤ ከእርሱም ጋር አምሳ የገለዓድ ሰዎች ነበሩ፤ ገደለውም፤ በእርሱም ፋንታ ነገሠ።


በዖዝያንም ልጅ በኢዮአታም በሀያኛው ዓመት የኤላ ልጅ ሆሴዕ በሮሜልዩ ልጅ በፋቁሔ ላይ ተማማለ፤ መትቶም ገደለው፤ በእርሱም ፋንታ ነገሠ።


እንዲሁም የናሜሲ ልጅ የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዩ በኢዮራም ላይ ተማማለ። ኢዮራምና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ከሶርያ ንጉሥ ከአዛሄል የተነሣ ሬማት ዘገለዓድን ይጠብቁ ነበር።


መሳፍንቶችዋንና ጥበበኞችዋንም፥ አለቆችዋንና ሹማምቶችዋን ኃያላኖችዋንም አሰክራለሁ፥ ለዘላለምም አንቀላፍተው አይነቁም፥ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የተባለው ንጉሥ።


በዚያ ሌሊት የከለዳውያን ንጉሥ ብልጣሶር ተገደለ።


ነገር ግን ልባችሁ በመጠጥ ብዛትና በስካር ስለ ትዳርም በማሰብ እንዳይከብድ፥ ያ ቀንም በድንገት እንዳይመጣባችሁ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤


跟着我们:

广告


广告